መነሻ ገጽ Uncategorized በከፍተኛ ሊግ ሱሉልታ ከተማ ከ መቐለ ከተማ የሱሉልታ ደጋፊዎች በፈጠሩት ጫና ጨዋታው ተቋረጠ
Uncategorizedየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

በከፍተኛ ሊግ ሱሉልታ ከተማ ከ መቐለ ከተማ የሱሉልታ ደጋፊዎች በፈጠሩት ጫና ጨዋታው ተቋረጠ

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 29ኛ ሳምንት በተከታታይ በሜዳ እና፡በሌሎች ችግሮች ሲንከባለል ለሶስተኛ ቀን፡የደረሰው የሱሉልታ እና መቐለ ከተማ ጨወታ ዛሬ 5ሰዓት ላይ፡በአዲስ አበባ እስታዲየም የተካሄደ ሲሆን የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ብዙ ሳቢ ባለሆነ መልኩ ነበር የተጠናቀቀው፡፡ 

በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታዉ  እንደ ተጀመረ ሱሉልታ ከተማ የመጀመሪያውን ጎል ሲያስተናግዱ ፡፡  በዙም ሳይቆይ በ66ኛ ደቂቃ  የጨዋታው አርቢትር ለመቀለ ከተማ የፍፁም ቅጣት ምት ሲሰጡ የሱሉልታ ተጨዋቾች የተሰጠው ፍፁም ቅጣት ምት ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውሞ በማሰማት ሜዳውን ለቀው ሊወጡ ችለዋል በዚህም የሱሉልታ ተጨዋቾች በደጋፊዎቻቸው  ወደሜዳ እዳትመለሱ በሚሉ ድምጾች ጫና ውስጥ ሲገቡ ለመታዘብ ተችሏል፡፡ 


ከ25ደቂቃዎች በኃላ የጨዋታው አርቢተር ጨዋታው መቋረጡን አውጀዋል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት 

ዳዊት ፀኃዬ(መቐለ ከተማ)


ጨዋታው በመረሀ ግብሩ መሠረት አልተካሄደም ፡፡ሱሉልታዎች ይሄን ጨዋታ ለማድረግ ተቸግረዋል ቢይንስ ሶስት ግዜ ወደ ሜዳቸው ተመላልሰናል፡፡ ለአንድ ጨዋታ ከአዲስአበባ ሱልልታ ድረስ ሶስት ጊዜ ተመላልሰናል፡፡ ይሄን ጨዋታ ለማድረግ በብዙ ጫናዎች ውስጥ ማለፍ ነበረብን፡፡ለዚህ ሁሉ የኛ ጫና ውስጥ መግባት የፌዴሬሽኑ ጠንካራ የአመራር ውሳኔ አለመታየቱ ነው፡፡እስከ 66ኛ ደቂቃ የተቋረጠበት ደቂቃ ደረስ እየመራን ነበር፡፡ማሸነፍ መሸነፈ ያለ ነው ሱልልታዎች የኛን አሸናፊነት መቀበል አለባቸው፡፡ደኛው የሰጠን የፍፁም ቅጣት ምት ተገቢ ነው፡፡

ታደሰ ጥላሁን (ሱልልታ ከተማ)


ዳኝነቱ በተወሰነ መልኩ ፍትሀዊ አይደለም እላለሁ፡፡ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የተሰጠብን ፍፁም ቅጣት ምት ተገቢ አይደለም አያሰጥም እላለሁ ፡፡ለዛም ነው በደጋፊዎቻችን እና በተጫዋቾቻችን ላይ ቅሬታ ያሳደረው ፡፡ ተጫዋቾቼ ተመልሰው ገብተው ጨዋታውን እንዲያደርጉ ለማግባባት ከፍተኛ ጥረት አድርጊያለሁ ሆኖም ተጨዋቾች ከደጋፊዎች ጋር አለመግባባት በመፍጠራቸው ጨዋታውን መልስን ለመቀጠል ሳንችል ጨዋታው ሊቋረጥ ችሏል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

አሰልጣኝ ጳውሎስ (ማንጎ) ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ተሰናበቱ

አዲስ የተቀጠሩት እና ዛሬ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ቡድኑን በአንድ ጨዋታ...

Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...