መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ።
መቐለ ከተማሪፖርትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ።

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መቐለ ላይ መቐለ ከተማ ና ጅማ አባጅፋር ተገናኝተው ባለሜዳው መቐለ ከተማ ያሬድ ከበደ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1-0 ማሸነፍ ችሏል።

የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ብልጫ መውሰድ የቻሉት መቐለ ከተማዎች ግብ ለማስቆጠር 12 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የፈጀባቸው። ከአማኒኤል ገብረሚካኤል የተሻገረለትን ኳስ ያሬድ ከበደ በ12ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ወደ ግብነት ቀይሮታል። ከግቡ መቆጠር በኀላ ብዙም ማራኪ እንቅስቃሴ ሳይስተዋልበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

ከእረፍት መልስ ግቡን ለመቀልበስ ተጭነው የተጫወቱት ጅማ አባጅፋሮች በተሻለ የኳስ ቁጥጥርና በተደጋጋሚ ወደ መቐለ ከተማ ግብ ክልል መድረስ ቢችሉም በእለቱ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየውን የመቐለ ከተማ ግብ ጠባቂ ፍሊፕ ኦቦኖ ማለፍ ተስኗቸው ለመሸነፍ ተገደዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...