መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ “በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሪነቱን ዙፋን እንረከባለን፣ ሻምፒዮናም እንሆናለን”አቡበከር ሳኒ (ቅ.ጊዮርጊስ)
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣቅዱስ ጊዮርጊስብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

“በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሪነቱን ዙፋን እንረከባለን፣ ሻምፒዮናም እንሆናለን”አቡበከር ሳኒ (ቅ.ጊዮርጊስ)

አጋራ
አጋራ

​በመሸሻ ወልዴ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የ7ኛ ሳምንት የሊግ
ጨዋታውን ከአርባምንጭ ከተማ ጋር አከናውኖ
የ3-0 ድል ቀንቶታል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
ጨዋታውን ሲያሸንፍም የሊጉን ግቦች አብራሂም
ፎፎና አብዱልከሪም ኒኪማና ምንተስኖት አዳነ
ግቦቹን አስቆጥረዋል፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
ይህን ጨዋታ ማሸነፉን ተከትሎም ሁለት
ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት ከመሪው
ደደቢት በሁለት ነጥብ ብቻ በመበለጥ የሁለተኛ
ደረጃን ሊይዝም ችሏል፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ
ክለብን በተመለከተ ቡድኑ ከአርባምንጭ ከተማ
ጋር ተጫውቶ ድል ስላደረገበትና በሌሎች
ጥያቄዎች ዙሪያ ከቡድኑ ተጨዋቾች መካከል
ጥሩ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘውን ወጣቱን
ተጨዋች አቡበከር ሳኒን ጠይቀነው ምላሹን
እንደሚከተለው ሰጥቶናል፤ ተከታተሉት፡፡


ሀትሪክ
፡- የአርባምንጭ ከተማን በሰፊ ግብ
ማሸነፍ ችላችኋል፤ ጨዋታው ምን ይመስላል?
በምን መልኩስ ማሸነፍ ቻላችሁ…

አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስና የአርባምንጭ
ከተማ የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ለክለባችን ኢትዮጵያ
ቡናን ከተፋለምንበትና ነጥብ ከተጋራንበት የሸገር
ደርቢው ፍልሚያ በኋላ ያከናወንነው ስለነበርና
ለጨዋታው ወደሜዳ የገባነው የግድ ወደ አሸናፊነት
መንፈሱም መግባት ስላለብን ከግጥሚያው 3
ነጥብን ይዘን ለመውጣት እስከመጨረሻው ሰዓት
ድረስ ጠንክረን ስለተጫወትን የድል ውጤቱን
ልነሳካ ችለናል፤ እንደዚያም ሆኖ ግን
በጨዋታው ቡድናችን ምንም እንኳን ድልን
ቢጎናፀፍም ጨዋታውን ያሸነፍነው በቀላሉ
አልነበረም፤ በመጀመሪያው አጋማሽ እነሱ ላይ
ጎል ለማስቆጠር ብዙ ተቸግረን ነበር፤ ወደ
ኋላ ያፈገፈጉበት እንቅስቃሴም ስለነበራቸው
ወደ እነሱ የሜዳ ክልል ለመግባት በጣሙን
እንድንቸገር አድርጎንም ነበር፤ በኋላ ላይ
ግን የመጀመሪያውን ግብ ካስቆጠርን በኋላ
ነገሮች የሁለተኛው አጋማሽ ላይ እየተስተካከሉ
በመምጣታቸው የምንፈልገውን ድል ልንጎናፀፍ
ችለናል፡፡


ሀትሪክ
፡- የቅ/ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና
የሳምንቱ ታላቅ የሸገር ደርቢ ጨዋታ አንተን
አምልጦህ ነበር ተቆጭተሃል?


አቡበከር
፡- የሀገሬን ብሄራዊ ቡድን
ለማገልገል ስለተመረጥኩና በኬኒያው ውድድር
ላይም ለመጫወት ወደ ስፍራው ስለተጓዝኩ
እንጂ እንደእውነቱ ከሆነ አዎን የሸገር ደርቢው
ጨዋታ ስላመለጠኝና ስላልተጫወትኩ በጣም
ተቆጭቻለሁ፤ የሸገር ደርቢ ጨዋታ እኮ
ሁሉም ተጨዋች ሊጫወትበት የሚመኘው
ግጥሚያ ነውና እኔም ልቆጭ ችያለሁ፡፡

ሀትሪክ
፡-የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ አርባምንጭ
ከተማን ድል ባደረገበት ፍልሚያ ጠንካራ
ጎናችሁ ምን ነበር.. ተጋጣሚያችሁስ የነበረው
አቋም?


አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
የአርባምንጭ ቡድንን ሲፋለም የመጀመሪያው
አጋማሽ ላይ እነሱ ወደኋላ አፈግፍገው
ለመጫወት በመሞከራቸው ጎል
እንዳይቆጠርባቸውና ለእኛም አጨዋወት
እንድንቸገር ቢያደርጉም በኋላ ላይ ግን
ቀዳሚውን ጎል ስናገባና እነሱም ወደፊት
ለመጫወት ጥረትን ሲያደርጉ ፍሊሚያው
ክፍት ሊሆን በመቻሉ ለእኛ የማጥቃት
እንቅስቃሴ አመቺ ሆኖልን ጨዋታውን
በጥሩ መልኩ አከናውነን በሰፊ ግብ ልናሸንፍ
ችለናል፤ ዋናው የዕለቱ ጥንካሬያችን የነበረውም
ጨዋታውን ለማሸነፍና ግብ ለማስቆጠርም
የነበረን ትዕግስተኝነትና እናሸንፋለን የሚልም
መርህ በውስጣችን ውስጥም ስለነበርም ነው፡
፡ የአርባምንጭ ከተማ ክለብን በተመለከተ
እነሱን በሰፋ ግብ ብናሸንፋቸውም ጠንካራ
ተፋላሚያችን ነበሩ፡፡


ሀትሪክ
፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ የአርባምንጭ
ላይ በመጀመሪያው አጋማሽ ቀዳሚውን ጎል
ያገባው የቅድሚያ ሙከራውን እንዳደረገ ነበር፤
በዕለቱ ሌሎች የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ
እንዳትችሉ ያስቻላችሁ ዋናው ምክንያት መን
ነበር?


አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ አስቦ የነበረው
አጨዋወት ኳስን ረጋ ብሎ በማንሸራሸር ወደ
እነሱ ሜዳ ለመግባትና ጥቃትን ለመፈፀም
ነበር፤ ያም ሆኖ ግን በኳስ ውስጥ አንዳንዴ
ያሰብከው ነገር እንደጠበቅከው ስለማይሆንና
ለእኛም የእነሱ እንቅስቃሴም ብዙ ቸግሮን
ስለነበር ነው እንደሌላው ጊዜ በመጀመሪያው
አጋማሽ ተደጋጋሚ ሙከራን ለማድረግ ሳንችል
የቀረነው፡፡


ሀትሪክ
፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ አሁን ላይ
ባለው ወቅታዊ አቋም በሚፈለገው ደረጃ ላይ
ነው የሚገኘው?

አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
የሊጉ የውድድር ተሳትፎው ላይ ያለውን
አቋም እንደተመለከትኩት ኳስን ተቆጣጥሮ
በመጫወቱም ሆነ በማጥቃቱ ረገድ ከዚህ
ቀደም ከነበረው ቡድን በተሻለ ሁኔታ ለመቅረብ
የተዘጋጀ ቡድን እንደሆነ ብናውቅም ያንን
አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ እየተገበርነው ነው
ማለት አልችልም፤ እንደዚያም ሆኖ ግን
አሁንም ቢሆን ጥሩ ቡድን እንዳለን አምናለሁ፡
፡ ለእዚያም ነው ተጋጣሚዎቻችን በሁሉም
አይነት የጨዋታ እንቅስቃሴ ወደሜዳ ሊገቡ
ቢችሉም ያንን እኛ በመስበር ከእነሱ ነጥቦችን
እየወሰድን ያለነው፡፡

ሀትሪክ
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
አርባምንጭ ከተማን ማሸነፍ መቻሉ ወደ ሊጉ
መሪ ደደቢት በነጥብ እንዲጠጋ አድርጎታል፤
ይህንን እንዴት ተመለከትከው?

አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የሊጉ
ውድድር ላይ የአርባምንጭ ከተማን በማሸነፍ
መሪውን ደደቢት በነጥብ ሊጠጋ የቻለው
ገና ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት
ነው፤ አሁን ባለን ልዩነት ደደቢት እኛን
በሁለት ነጥብ ብልጫ ይመራናል፤ ስለዚህም
በተስተካካይ ጨዋታዎች የምናስመዘግበው
ውጤት ሳይደመር ያለን ልዩነት በጣም ጠባብ
ስለሆነና የሊጉ ውድድር ደግሞ ገና በርካታ
ጨዋታዎችም ያሉት ስለሆነ የአጭር ጊዜ
ውስጥ ወደለመድነው የመሪነት ዙፋናችን ላይ
እንቀመጣለን፡፡

ሀትሪክ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የዓመቱ መጨረሻ ላይ በሊጉ ምን ውጤት ያስመዘግባል?


አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
ሁልጊዜም የሊግ ውድድሮችን የሚያከናውነው
የአመቱ መጨረሻ ላይ የሚዘጋጁትን ዋንጫዎች
ለማነሳት ነው፤ ስለሆነም ክለባችን ወደ
ውድድሩ ሲገባ ማንኛውንም ዋንጫ የሚመርጥ
ክለብ ስላልሆነም ዘንድሮም የሊጉም የሌሎችም
ውድድሮች ሻምፒዮና እንሆናለን፡፡


ሀትሪክ
፡-የቶታል አፍሪካ ካፍ ቻምፒዮንስ
ሊግ ጨዋታችሁን ከደቡብ ሱዳኑ ክለብ አል
ሰላም ዋኡ ጋር ታደርጋላችሁ ይህንን ጨዋታ
በተመለከተ ምን ትላለህ?


አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የቶታል
ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የዘንድሮው ጨዋታውን
የሚያደርገው እስከዛሬ በተደጋጋሚ ከአንዴም
ሁለት እና ሶስት ጊዜ ከጫፍ ደርሰን
የነበርንበትን የ2ኛው ዙርና በአዲሱ የውድድር
ፎርማትም ገብቶበት ከነበረው የ16 ክለቦች
ከሚሳተፉበት ውድድር በላይ በማለፍ ወደ
ሩብ ፍፃሜ የሚያስገባውን ውጤት ለማግኘት
ነውና ይህንን ውጤት ለማግኘትና የሀገረቱ
የመጀመሪያ ቡድንም ለመሆን ከፍተኛ ጥረት
እናደርጋለን፡፡


ሀትሪክ
፡-የእናንተ ተጋጣሚ የደቡብ ሱዳን
ክለብ ከመሆኑ አኳያ ግጥሚያው ለእናንተ
ቀላል ነው ማለት ይቻላል?


አቡበከር
፡- በፍፁም፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ
ክለብ ውስጥ ባለው አስተሳሰብ ሁሌም
የተጋጣሚ ቀላል ፈፅሞ የለም፤ ስለዚህም የእኛ
ቡድን የደቡብ ሱዳን ጋር ጨዋታውን ሲያደርግ
ለጨዋታው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን በመግባት
ነው ጨዋታውን ማሸነፍ የምንፈልገው፡፡


ሀትሪክ
፡-የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ
ጥሩና አበረታች እንቅስቃሴን ብታሳይም አሁን
ላይ በጅማሬው ጎል ማስቆጠሩ ላይ ራቅ
ወደማለቱ መጥተሃል?


አቡበከር
፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
ውስጥ በሊጉ ጅማሬ አሁን ያለኝን አቋም
በጣም እየወደድኩት ነው ያለው፤ በቀጣይ
ጊዜ ከእዚህ የበለጠም ተሸዬ እንደምቀርብና
በውስጤ ያለውንም እምቅ ችሎታዬን አውጥቼ
በመጫወት ክለቤን እንደምጠቀምም አምናለሁ፡
፡ የጎል ማስቆጠሩ ላይ ለተባልኩት አሁን ብዙ
ጎሎችን ማስቆጠር እፈልጋለሁ፡፡ ደግሞም
እነዚህን ወደፊት ማሳካቴ የማይቀር ነው፤
እስከዚያው ግን ለቡድን አጋሮቼ ኳሶችን
የማቀበል ሁኔታ ላይ ስላለሁም ያም እኔን
በጣሙን እያስደሰተኝም ነው የሚገኘው፡፡


ሀትሪክ
፡- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
የሴካፋ ተሳትፎን አድርጎ ውጤት አላመጣም፤
ችግሩ ምን ነበር፤ ስለ አጥቂው አቤልስ ምን
ትላለህ?

አቡበከር፡-የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
የሴካፋ ተሳትፎው ላይ ውጤት ያጣው ከልምድ
ማነስ ችግር ነው፤ ለዋልያዎቹ የተመረጡት
አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች በእንዲህ ያለ የውድድር
መድረክ ላይ የአገራቸውን ማሊያ ለብሰው
ያልተጫወቱ መሆኑ ሊጎዳን ችሏል፡፡ አቤልን
በተመለከተ ጥሩ ብቃት ያለው የአጥቂ ስፍራ
ተጨዋች ነው ወደፊት የተሻለ ቦታ ላይም
መድረስ ይችላል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቢጂአይ ኢትዮጵያ ስፖንሰር ሊደረግ ነው

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀድሞው አጋሩ ጋር በድጋሚ ለመጣመር ውይይት አድርጓል። አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስን...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞው ተጫዋቾች ማህበር አቋቋሙ

የቅዱስ ጊዮርጊስን ችግር ለመቅረፍ ያለመ በቀድሞው ተጫዋቾች የተሰየመ ማህበር በዛሬው ዕለት በይፋ...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የሽግግር ኮሚቴ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ መረጠ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ካጋጠመው ውስጣዊ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተቋቋመው የሽግግር ኮሚቴ...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የፈረሰኞቹ የሰላም ውይይት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል…..

... ከሳሹ ወገን ዛሬ ቦርዱ ሃላፊነቱን መልቀቁን በይፋ ማሳወቅ አለበት እያለ ነው...