መነሻ ገጽ ቅድመ ዳሰሳ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ወልዲያ ከተማ ከ ደደቢት
ቅድመ ዳሰሳወልዲያዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግደደቢት

ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ወልዲያ ከተማ ከ ደደቢት

አጋራ
አጋራ

በ14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ  መርሃ ግብር ወልዲያ ላይ  ወልዲያ ከተማ ከደደቢት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ወልዲያ ከተማ ስፖርት ክለብ አጋጥሞት በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት የእግር ኳስ ፌዴሬሺኑ ከክለቡ ጋር በመነጋገር ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ የሚታወስ ሲሆን፡ይሄው በይደር የቆየው ጨዋታ  ወልዲያ ላይ በሼህ ሙሀመድ ሁሴን  አሊ አላሙዲን ስታዲዬም ዛሬ በዕለተ ሰኞ ከቀኑ በ9:00 ሰዓት የሚካሄድ ሲሆን በቅድመ ጨዋታ ዳሰሳችን እንደሚከተለው  ተመልክተነዋል፡፡

ባለሜዳው ወልዲያ ከተማ የሊጉን 14ኛ ሳምንት ጨዋታ  የሚያከናውንሲሆን ፡እንግዳው ደደቢት የሊጉን የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ  ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ወደ ወልዲያ አቅንቶ ከወልዲያ ከተማ ጋር ይጫወታል፡፡

በዘንድሮው የሊጉ ጉዞ  በነባርና በታዳጊ ወጣት ተጨዋቾች ከጥሩ ጨዋታ ጋር ጥሩ ጊዜን  በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ደደቢት ፡በርካታ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችን  በክረምቱ የዝውውር መስኮት ካዛዎረውና የተጨዋቾችን ሙሉ ግልጋሎት  በጉዳትና በቅጣት ከላገኘው ወልዲያ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በአንደኛው በኩል የስኬት ጎዳናውን ሩጫ ለማፍጠን  ሌላኛው ወደ ስኬት ጎዳና ለመግባት የሚያደርጉት  ፍክክር ከወዲሁ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል ፡፡

ወልዲያ ከተማ ባለፈው ሳምንት በሜዳው መከላከያን 2ለ0 አሸንፎ ለዚህ ጨዋታ  ሲቀርብ ተጋጣሚው ደደቢት  በዝናብ በታጀበው ጨዋታ  ከፈረሰኞቹ ጋር  ያለ ግብ ነጥብ ተጋርቶ ለዚህ ጨዋታ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ 
ባለሜዳዎቹ ወልዲያ ከተማዎች ተጋጣሚያቸውን በማሸነፍ  1 ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታ ከወላይታ ዲቻ እያላቸው ነጥባቸውን ከ15 ወደ 18 በማድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ ከ12ኛነት እስከ  8ኛ ደረጃ ከፍ ለማለት የሚጫዎቱ ሲሆን፡፡

 ደደቢት ነጥባቸውን ከ29 ወደ 32 በማድረስ  መሪነታቸውን ከማጠናከር ባሻገር ከተከታዬቹ ጅማ አባቡና እና መቆለ ከተማ ያለውን የነጥብ ልዩነት ከ4 ወደ 7 በማስፋት የመጀመሪያውን ዙር ለማጠናቀቅ  ለጨዋታው የተለየ ትኩረት ሰጥተው የሚጫዎቱ ይሆናል፡፡
የቅጣትና የጉዳት ዜና ስንመለከት በእንግዳው ቡድን ደደቢት በኩል ጎል አዳኙ ጌታነህ ከበደ እና አማካኙ አስራት መገርሳ በቅጣት ተከላካዩ ከድር ኩሊባሊና ግብ ጠባቂው ክሌመንት አዞንቶም በጉዳት አለመሰለፋቸው ተረጋግጧል፡፡
በባለሜዳው ወልዲያ ከተማ በኩል ዛሬም  የ9 ተጨዋቾችን ግልጋሎት አያገኝም፡፡አዳሙ ሙሀመድ ለህክምና ወደ ጋና አምርቷል፡፡ታደለ ምህረቴ፡ፍፁም ገ/ማርያምና ያሬድ ብርሃኑ ወደ ክለቡ ያልተመለሱ ሲሆኑ ነጋ በላይ ፡ሰለሞን ገ/መድህን እና ተስፋሁን ሸጋው በጉዳት፡  በዛሬው ጨዋታ እንደማይደርሱ የተረጋገጠ ሲሆን ፡ተስፈዬ አለባቸው ለጨዋታው መድረሱም አጠራጣሪ ሁኗል፡፡

ወልዲያ ከተማ ከ13 የሊግ ጨዋታ በሜዳው ካደረጋቸው 7 ጨዋታዎች 3ሲያሸንፍ፡በ3አቻ ሲለያይ፡በ1ተሸንፎ 7 ጎል ሲያስቆጥር 2 ጎል ሲቆጠርበት፡ከሜዳው ውጭ ያደረጋቸውን 6 ጨዋታዎች ስንመለከት በ3 ጨዋታ የአቻ ውጤት ሲያስመዘግብ በ3ጨዋታ ተሸንፈው፡ከሜዳቸው ውጭ 8ጎል ሲያስተናግዱ 2ጎል አስቆጥረዋል፡፡በአጠቃላይ ወልዲያ ከተማ 10 ጎል ሲቆጠርበት 9ጎል አግብተው በ15 ነጥብና በ1 የግብ ዕዳ 12ደረጃ ተቀምጠዋል፡፡
ደደቢት ካደረጋቸው 14 ጨዋታዎች 8 ጨዋታ በሜዳው ሲያደርግ 6 ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ተጫውተዋል፡፡በሜዳቸው ካደረጓቸው 8 ጨዋታዎች 5ቱን በማሸነፍ 2አቻ ሲለያዩ በ1ተሸንፈው፡17 ጎል ሲያስቆጥሩ 6ጎል ተቆጥሮባቸው፡ከሜዳቸው ውጭ በ6ጨዋታ 3አሸንፈው 3አቻ ሲለያዩ ያለሺንፈት 7ጎል ሲያስቆጥሩ 2 ጎል ተቆጥሮባቸው በአጠቃላይ በ14 ጨዋታ፡24 ጎል ሲያስቆጥሩ 8ጎል ተቆጥሮባቸው በ29 ነጥብና በንፁህ 16 ጎል በሊጉ አናት ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የሁለቱን ክለቦች የቆየ ግንኙነት ስንመለከት 

4ጊዜ ተገናኝተው፡ በ2 ጨዋታ ደደቢት በሜዳው አዲስ አበባ ስታዲዬም 2ቱንም ሲያሸንፍ፡፡ወልዲያ ከተማ በሜዳው   በ2ጨዋታ በ1 ሲሸነፍ ከደደቢት ጋር ባለው ግንኙነት ትልቁ ውጤት በሜዳው ያስመዘገበው የአቻ ውጤት ነው፡፡
ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ ኢብራሂም አጋዥ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...