ቅድመ ጨዋታ ዕይታ| ድሬዳዋ ከተማ ከ ስሑል ሽረ

 

በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ስሑል ሽረን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ከጨዋታው በፊት አንዳንድ ነጥቦችን አንስተንላቹሀል።

በወረጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ቡርቱካናማዎቹ በውጤት እጦት ምክንያት አሰልጣኛቸውን ካሰናበቱ በኋላ። በምክትል አሰልጣኛቸው ፍስሀ ፆመልሳን እየተመሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ነገ በጥሩ ወቅታዊ አቋም ላይ የሚገኘውን ስሑል ሽሬ አስተናግደው ይገጥማሉ። ድሬዳዋዎች በአዲስ አሰልጣኝ እየተመሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከማድረጋቸው አኳያ አጨዋወቱን ለመተንበይ ቢከብድም ቡድኑ አዘውትሮ የሚጠቀምባቸው አጨዋወት ሊከተል ይችላል ተብሎ ይገመታል። በተለይም ደግሞ ቡድኑ ብትንትን ያለ የሚከተለው አጨዋወቱ እና በቀላሉ የሚረበሸው የተከላካይ መስመር ለበርካታ ነጥብ መጣሎች ያዳረገው ቡድኑ አሁንም ስጋት እንዳይሆንበት ይፈራል። ከፊት መስመር ያሉት ሙህዲን ሙሳ አና ሪችሞንድ አዶንጎ ወደ ግብ የመቀየር አቅም ለቡድኑ የነጥብ ማግኛ መንገድ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። በጥሩ ወቅታዊ አቋም የሚገኙት ተጋባዦቹ ግብ አይምሬው የፊት መስመራቸው በቀላሉ የሚፍረከረከው የጋባዦቹ መከላከል ሰብረው ለመግባት ይቸገረሉ ተብሎ የማይጠበቅ ሲሆን። ቡርቱካናማዎቹ ጠንካራውን የተከላካይ ስፍራ የማስከፈት ፈተና ይጠበቅባቸዋል።

ቅጣት እና ጉዳት

በድሬዳዋ ከተማ በኩል በጉዳት ያሬድ ታደስ ሲያጡ በስሁል ሽረ በኩል በጉዳት ዮናስ ግርማይ እና  በቅጣት ዲዲዬ ሊብሬን እሚያጡ ይሆናል።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

በ2011 የጀመረው የሁለቱም ቡድኖች ግንኙነት። ሁለት ግዜ ተገናኝተው ሁለቱንም በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። አንድ አቻ የተጠናቀቀው የሁለተኛው ዙር ጨዋታ ብቸኛው ግብ ያስተናገደው ጨዋታ ነበር። ይህ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ በኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ እየተመራ 9:00 ይጀመራል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor