መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ ቅድመ ጨዋታ ዕይታ| ወልቂጤ ከ ባህርዳር ከተማ
ባህርዳር ከተማወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ቅድመ-ዕይታ

ቅድመ ጨዋታ ዕይታ| ወልቂጤ ከ ባህርዳር ከተማ

አጋራ
አጋራ

12ኛው ሳምንት የኢትዮጰያ ፕሪምየር ሊግ ከድል የተመለሱት ሁለቱም ቡድኖች ያገናኘው ይህ ጨዋታ። ከጨዋታ በፊት የሚከተሉትን ነጥቦችን አንስተናል።

ሀድያ ሆሳዕናን ከሜዳቸው ውጭ በማሸነፍ ተከታታይ ሁለተኛ ድላቸውን ያሳኩት የደግአረግ ይግዛው ወልቂጤ ከተማዎች። ባህርዳር ከተማን የሚያሰተናግዱበት ጨዋታ ተጠባቂ ያደርገዋል። ሁለቱም ቡድኖች ኳስ ተቆጣጥረው የሚጫወቱ እንደመሆናቸው መጠን ለተመልካች አዝናኝ እግር ኳስ ያስመለክታሉ ተብሎ ይጠበቃል። ያገኙትን የግብ አጋጣሚ ወደ ግብነት የመለወጥ ችግር ሲስተዋልባቸው የነበሩት ክትፎዎቹ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አሻሽለው በአሸናፊነት ጎዳና እንዲራመዱ አድርጓቸዋል። ክትፎዎቹ ይህን ጥንካሪያቸው ማስቀጠል የሚችሉ ከሆነ ደግሞ ግብ አግብተው ግብ የሚያተናግዱት የጣናው ሞገዶች ሲጋት በቀላሉ ግብ ሊያስተናግዱ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠሩ ይችላል። ካላቸው ጥሩ አጨዋወት ጋር ታግዘው አጋጣሚዎችን መፍጠር የማይሳናቸው ባህርዳሮች። ክትፎዎቹ ለሚሰሩት ስህተት ምላሽ ከመስጠት ወደኋላ ሳይሉ ኳስ እና መረብን ሊያገናኙ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ ሊሆኑ ይችላል። በጣናው ሞገዶች በኩል ወሳኝ ተጫዋቻቸው ፍፁም አለሙ፣አዳማ ሲሶኮ፣ወሰኑ አሊና አቤል ውዱ በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በሁለት ቢጫ ካርድ ምክንያት በቀይ ካርድ ከሜዳ የተወገደው ሳሙኤል ተስፋየ ቅጣቱን ጨርሶ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ሆኗል። ተመልባለሜዳዎቹ በቅጣት እና በጉዳት የሚያጡት ተጫዋች አይኖርም።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

ሁለቱም ቡድኖች ዛሬ ሲገናኙ ይህ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ግዜ ሲሆን። ነገ 9:00 ወልቂጤ ላይ በፌደራል ዳኛ ኢሳያስ ታደስ እየተመራ ይደረጋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...