ቅድመ ጨዋታ – እይታ | ጅማ አባጅፋር ከ ኢትዮጵያ ቡና

ነገ ከሚደረጉ የ17ኛ ሳምንት መርሀ ግብር መካከል የጅማ አባጅፋር እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ እንደሚከተለው አይተነዋል።

በከፍተኛ መነቃቃት የሚገኙት ቡናማዎቹ ወደ ጅማ በማቅናት ጠንካራውን ሆኖም ግን በወራጅ ቀጠናው የሚገኘው ጅማ አባጅፋርን የሚገጥም ይሆናል። ወደ ባህርዳር አቅንተው ሽንፈት አስተናግደው የተመለሱት ጅፋራውያኑ ስሑል ሽረን በሰፊ የግብ ልዩነት 6-1 ያሸነፋት ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳቸው ያስተናግዳሉ። ባለሜዳዎቹ ምንም እንኳን በወራጅ ቀጠናው ይገኙ እንጂ በሜዳውም ከሜዳውም ውጪ በጣም ፈታኝ ቡድን እንደሆነ በተደጋጋሚ አስመስክሯል። ጅፋራውያኑ በሜዳቸው እንደሚጫወት ቡድን በብዛት በሚዳቸው በሚያደርጉት ጨዋታ አጥቅተው ከኤልያስ አህመድ የሚነሱ ኳሶች ሁለቱንም የማጥቃት መስመሮች ለተጋጣሚ ፈታና እንደሚሆኑ ይጠበቃል። በአንፃሩ ተጋባዦቹ ኳስን ተቆጣጥሮ የሚጫወት ቡድን መሆኑን ተከትሎ ጠንቃቄ የተሞላበት የማጥቃት መንገድ ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል። ጅማዎች በሜዳቸው ካለቸው ጥንካሬ አንፃር የአሸናፊነቱ ግምት ወደ ጋባዦቹ ቢያጋድልም እንግዳዎቹ ያላቸው ሰሞንኛ መነቃቃት በቀላሉ የሚቀመሱ አይደሉም።

ጉዳት ቅጣት –  

በጅማ አባጅፋር በኩል ለእረፍት ሄደው ባሳለፈነው ሳምንት ከቡዱኑ ጋር ያልነበሩት ዜጋ ተጫዋቾች ሁሉም የተመለሱ ሲሆን በቅጣት ከዚህ በፊት ያጧቸው ተጫዋቾችም መመለሳቸው ሲሰማ በ ኢትዮጵያ ቡና በኩል እስካሁኑ ሰዓት ድረስ የተሰማ የጉዳት ዜና የለም።

ይህን ጨዋታ በኢንተርናሽናል አርቢትር አማኑኤል ኃይለስላሴ እየተመራ 9:00 የሚጀምር ይሆናል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor