መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ ቅድመ ዳሰሳ | የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የግንቦት 10 ተስተካካይ ጨዋታዎች
መቐለ ከተማቅዱስ ጊዮርጊስወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግድሬዳዋ ከተማ

ቅድመ ዳሰሳ | የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የግንቦት 10 ተስተካካይ ጨዋታዎች

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ ዛሬ ክልል ላይ በትግራይ እና ድሬድዋ ስታዲዮም ከቀኑ 9:00 በሚካሄዱ 2 ተስተካካይ ጨዋታዎች ቀጥሎ ይከናዎናል ፡፡እነዚህ ጨዋታዎች ፈረሰኞቹና የጦና ንቦቹ በአህጉራዊ ውድድር ተሳትፎ ምክንያት ሳይደረጉ በይደር ተይዘው የቆዩ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

መቐለ ከተማ ከ ቅ/ጊዮርጊስ

ይህ ጨዋታ በ18ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ መካሄድ የነበረበት ቢሆንም ፈረሰኞቹ ሲካፈሉበት በነበረው የአህጉራዊ ጨዋታ ተሳትፎ ምክንያት በይደር ተይዞ የቆየ የጨዋታ መርሃ ግብር ነው፡፡ዛሬ በትግራይ ስታዲዮም በርካታ ደጋፊዎች እንደሚታደሙበት የሚጠበቀው ይህ ጨዋታ ለፈረሰኞቹም ሆነ ለባለሜዳዎቹ መቀለዎች ውጤቱ እጅጉን ያስፈልጋቸዋል፡፡በመሀከላቸው ባለ የ1 ነጥብ ልዩነት ምክንያት በሰንጠረዡ 2ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ፈረሰኞቹ ሆኑ ባለሜዳዎቹ መቐለዎች በዋንጫ ፉክክሩ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደመሆናቸው ዛሬ የሚያስመዘግቡት ውጤት እጂጉን ወሳኝ ነው፡፡

በመጀመሪያው ዙር ሁለቱ ክለቦች አዲስ አበባ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ በነበራቸው ታሪካዊ ግንኙነት ባለሜዳዎቹ ፈረሰኞቹ በጨዋታው ማገባጃ ባስቆጠሯት ብቸኛ ግብ ከሽንፈት ተርፈው ነጥብ መጋራታቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ትግራይ ላይ የሚገናኙት ሁለቱ ክለቦች ትልቅ ፍክክር የሚስተናገድበት ፡የጨዋታው ውጤት ከመቼውም በላይ ትልቅ ትርጉም ያለው ከወዲሁ የደጋፊዎችን ትኩረት የሳበ ጨዋታ ነው፡፡በሜዳቸው ካደረጓቸው 9 ጨዋታዎች እስካሁን በደደቢት ብቻ ሽንፈት ያስተናገዱት መቐለዎች፡በሜዳቸው 3 ግብ ብቻ ተቆጥሮባቸዋል፡፡ይህም ዛሬ ፈረሰኞቹ ግብ ለማስቆጠርም ሆነ ለማሸነፍ ትልቅ ፈተና ከባለሜዳዎቹ እንደሚጠብቃቸው አመላካች ነው፡፡

በዛሬው ጨዋታ በፈረሰኞቹ ቤት የፊት መስመር ተሰላፊዎቹ ሪቻርድ አፒያና አማራ ማሌ በጉዳት ከጨዋታው ውጭ ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት ፈረሰኞቹ ባለሜዳውን ኢሌክትሪክ 2-1 በረቱበት ጨዋታ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የወጣው አቡበከር ሳኒም ጨዋታው የሚያልፈው መሆኑ የፊት መስመሩ በትንሹም ቢሆን መሳሳት በማሳየቱ የሚና ለውጥ በማድረግ የተጨዋቾች የቦታ ሽግሽግ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡በባለሜዳዎቹ መቀለዎች በኩል የጉዳት ዜና እስካሁን የተነገረ ነገር የለም፡፡

በተለይም በዚህ ጨዋታ በባለሜዳዎቹ አሸናፊነት ጨዋታው የሚደመደም ከሆነ የተጋጣሚያቸውን የብርቱካናማዎቹን ቦታ መቀለዎች የመረከብ ዕድል በእጃቸው ነው፡፡ፈረሰኞቹም ቢሆኑ ወደ ለመዱት የሻምፒዮንነት ጉዟቸው ለመገስገስ ይህን ጨዋታ ከሜዳቸው ውጭ ቢጫዎቱም ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ የሚጠበቅ ነው፡፡ባለሜዳዎቹ ይህን ጨዋታ አሸንፈው ከሊጉ መሪ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት አጥበው ከወልዋሎ ጋር ያላቸውን ተስተካካይ ቀሪ 45ደቂቃ ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ የሊጉን መሪነት ከጅማ ከመረከባቸውም ባለፈ በ2 ነጥብ ርቀት መምራት የሚያስችላቸው አጋጣሚ ለማመቻቸት ዛሬ በሜዳቸውና በደጋፊዎቻቸው ፊት ፈረሰኞቹን ለማሸነፍ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም፡፡
ፈረሰኞቹም ቢሆኑ በጨዋታው ከ4 ግብ በላይ አስቆጥረው የሚያሸንፉ ከሆነ በቀጥታ ወደ ሊጉ አናት ተመልሰው ሊጉን መምራት የሚያስችላቸውን አጋጣሚ መፍጠር የሚችሉ ቢሆንም ፡በሊጉ በተለይም በመከላከል ረገድ በጥንካሬ ቀዳሚ የሆኑት ባለሜዳዎቹ መቐለዎች በዚህ ጨዋታ በርካታ ግቦችን ያስተናግዳሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡በ20 የሊግ ጨዋታዎች 8ግቦችን ብቻ ያስተናገዱት መቀለዎች የመከላከል ጥንካሬያቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ፈረሰኞቹም ቢሆኑ ከሜዳቸው ሲዎጡ ግብ የማስቆጠር ችግር ባይኖርባቸውም፡የሚቆጠሩባቸው ግቦች ዋጋ ሲያስከፍላቸው ተመልክተናል፡፡በተለይም ለአብነት ሀዋሳና አርባ ምንጭ ላይ ሲሸነፉ የተቆጠሩባቸው ግቦች ድምር 7 መሆኑ ቡድኑ ከሜዳው ሲወጣ የተከላካይ ክፍሉ እንደሚቸገር የሚያሳይ ቢሆንም ጉዳት ላይ የነበሩ ተጨዋቾች መመለሳቸውን ተከትሎ በባለፈው ሳምንት ጨዋታ መሻሻልን አሳይቷል፡፡

በዛሬው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ጥንቃቄ የበዛበትና በአግድሞሽና ፡ቀጥተኛ ተሻጋሪ ኳሶች ግብ ለማግኘት እንደሚጫዎቱ የሚጠበቅ ነው፡፡በግልም ሆነ በቡድን የቦታም ሆነ የጨዋታውን የበላይነት ለመውሰድ የሚደረገው ትንቅንቅ ለተመልካች ማራኪም ተጠባቂም ይሆናል፡፡

በቀጣይ ሳምንታት እውነተኛው የዋንጫ ተፎካካሪ ባለሜዳዎቹ ወይስ ፈረሰኞቹ ይሆናሉ ? ዛሬ ፍንጭ ከትግራይ ስታዲዮም የጨዋታው ውጤት ይነግረናል፡፡ጨዋታው በአቻ የሚጠናቀቅ ከሆነ የሊጉ መሪ ጅማ አባጅፋር ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

ድሬድዋ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

በወላይታ ድቻ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ መድረክ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳትፎ ምክንያት በይደር ተይዞ ዛሬ በ9:00 ድሬድዋ ላይ ድሬድዋ ከተማ ከ ወላይታድቻ የሚያደርጉት ጨዋታ ለዋንጫ የሚደረግ ፉክክር ባይሆንም ባለሜዳዎቹ ድሬዎች በወራጂ ቀጠናው ግርጌ ተቀምጠው የሚያደርጉት ጨዋታ እንደመሆኑ ከወዲሁ በርካቶች በትኩረት የሚጠብቁት ጨዋታ ሁኗል፡፡

የጨዋታው ውጤት ከወላይታ ድቻዎች ይልቅ ለጊዜውም ቢሆን ከወራጂ ቀጠናው ለመላቀቅ ለባለሜዳዎቹ ድሬድዋ ከተማዎች እጁጉን የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም የጦና ንቦቹ ድቻዎች ጨዋታውን አሸንፈው ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ቀጥተኛ ተሳታፊ ለመሆን ባያስችላቸውም ከመሀል ሰፋሪነት ወጥተው ከሊጉ መሪዎች በቅርብ ርቀት ለመቀመጥ ያስችላቸዋል፡፡ባለፈው ዓመት በመጨረሻዎቹ ሳምንታት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ከመውረድ የተረፉት ድሬዎች ዘንድሮም የባለፈው ፈተና እንዳይገጥማቸው ከወዲሁ ነጥብ መሰብሰብ የግድ ይላቸዋል፡፡በተለይም በሜዳ የሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ ሙሉ ነጥብ ማስመዝገብ ከሜዳ ወጥቶ ሲጫዎቱ ያለውን ጫና በመጠኑም ቢሆን ይቀንሰዋል፡፡በሌላ በኩል በተጨዋቹ ያለውን የስነ ልቦና ጫና ከማቅለሉም ባሻገር የአሸናፊነት ስነ ልቦናን ለማጎልበት ጠቃሚ ነው፡፡

ሁለቱ ክለቦች ከሽንፈት ተመልሰው በተመሳሳይ በአዳማ ከተማ ሽንፈት አስተናግደው መገናኘታቸው አስገራሚ ሲሆን በዛሬው ጨዋታ ድሬድዋ ከተማ አሸንፎ ከወራጂ ቀጠና ይወጣል ወይስ ድቻ ከመሀል ሰፋሪነት ይላቀቃል ምላሹ አመሻሹን የሚታወቅ ይሆናል፡፡ሁለቱም ቡድኑች ኳስን ተቆጣጥረው ለመጫወት የሚሞክሩ ቡድኖች እንደመሆናቸው ጨዋታው ጥንቃቄ የበዛበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

በ21 ጨዋታዎች 19 ነጥቦችን የሰበሰቡት ባለሜዳዎቹ ድሬድዋ ከተማዎች ይህን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ ነጥባቸውን 22 በማድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ ወራጂ ቀጠናውን ለቀው እስከ 12ኛ ደረጃ ከፍ የሚሉበት አጋጣሚ የሚፈጠር ሲሆን፡ እንግዳዎቹ ድቻዎች በበኩላቸው ጨዋታውን አሸንፈው ነጥባቸውን ወደ 30 በማድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ 8ኛ ከፍ ለማለት ይጫዎታሉ፡፡በዚህ ጨዋታ የድቻው ግብ ጠባቂ ወንደሰን ገረመው ክለቡ በጣለበት የ1 ዓመት ዕገዳ ምክንያት የማይኖር ሲሆን ሌላ የቅጣትም ሆነ የጉዳት ዜና በሁለቱም ቡድኖች በኩል ስለመኖሩ የነገረ ነገር የለም፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...