መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድመ ዳሰሳ | ቅ/ጊዮርጊስ ከ ደደቢት
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችደደቢትዳሰሳ

ቅድመ ዳሰሳ | ቅ/ጊዮርጊስ ከ ደደቢት

አጋራ
አጋራ

የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ተስተካካይ የመጨረሻ አንድ ጨዋታ ዛሬ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይጠናቀቃል።

አ/አ ላይ በሚደረገው በዕለተ ቅዳሜ ብቸኛ የሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ 10፡00 ሲል ቅ/ጊዮርጊስን ከ ደደቢት የሚያገናኝ ይሆናል።

በሊጉ ሊጠቀሱ ከሚችሉት ትልልቅ ጨዋታዎች አንዱ በሆነው ይህ ጨዋታ በእግር ኳስ አፍቃሪው ዘንድ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ቅ/ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ ጋር አድርጎት በነበረው ጨዋታ ላይ በተነሳው ረብሻ እና የደጋፊዎች ስርዓት አልበኝነት ምክንያት ጥፋተኛ ተብሎ የነበረው ቅ/ጊዮርጊስ የ180,000 ብር ቅጣት እና አንድ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ ያለተመልካች በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ተወስኖበት የነበረ ሲሆን ይህም በደጋፊው ዘንድ መደናገጥን ፈጥሮ ነበር። ሆኖም ግን ቅ/ጊዮርጊስ ይግባኝ በማስገባቱ ምክንያት የይግባኙ ሂደት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ክለቡ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ጨዋታ በተመልካች ታጅቦ የሚያደርግ ይሆናል። ይህንንም ተከትሎ የዛሬው ጨዋታ በሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች ታጅቦ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለቱም ቡድኖች በዘንድሮው የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ ሁለት ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀራቸው ሲሆን የዛሬውን የእርስ በእርስ ጨዋታ ካደረጉ በኋላ ቅ/ጊዮርጊስ ሀሙስ የካቲት 22/2010 ወደ ሀዋሳ ተጉዞ ሀዋሳ ከተማን ሲገጥም ደደቢት ደግሞ የካቲት 22/2010 ወደ ወልድያ አቅንቶ ወልድያ ስፖርት ክለብን የሚገጥም ይሆናል።

የሁለቱ ቡድኖች የእርስ በእርስ ግንኙነት፦

ደደቢት በ2002 ዓ.ም ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደገ በኋላ ላለፉት 8ዓመታት ሁለቱ ቡድኖች 16 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ 11 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይወስዳል ደደቢት በአንፃሩ 3 ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ቀሪዎቹን 2ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። በነዚህ 16 ጨዋታዎች 45 ግቦች የተቆጠሩ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ 28ቱን ተጋጣሚው መረብ ላይ ሲያሳርፍ ደደቢት ደግሞ 17ቱን ማስቆጠር ችሏል። የመጀመሪያ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው 0-0 የተጠናቀቀ ሲሆን የመጨረሻው ግንኙነታቸው ላይ ደግሞ 2009 ላይ በሁለተኛው ዙር ቅ/ጊዮርጊስ 3-2 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በ2005 ደደቢት 3-1 ያሸነፈበት ጨዋታ ደደቢት ቅ/ጊዮርጊስ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ያስመዘገበው ድሉ ሲሆን በ2006 3-3 የተጠናቀቀው ጨዋታ ደግሞ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ከተደረጉት ጨዋታዎች ከፍተኛ የግብ ብዛት የተስተናገደበት ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል።

የሜዳ ላይ ትንተና፦

በቅ/ጊዮርጊስ በኩል አሁንም በአጥቂ ስፍራው ላይ ትልቅ ችግር ይስተዋላል። የክለቡ ወሳኝ አጥቂ ሰልሀዲን ሰዒድ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ቡድኑ ቢመለስም ለዛሬው ጨዋታ የመግባቱ ነገር አጠራጣሪ ነው። በሌላ በኩል በርካታ ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት እስካሁን የመሰለፍ እድል አላገኙም፤ ይህም ቡድኑ ውጤት ለማጣቱ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ይነሳል። በዘንድሮው የቅ/ጊዮርጊስ ቡድን ውስጥ ከተስተዋሉት ተጨማሪ ችግሮች መካከል የሜዳው የመሀል ክፍል ላይ ኳስ ተቆጣጥሮ የሚጫወት ተጫዋች አለመኖሩ እንዲሁም በተደጋጋሚ ከመስመር ወደ ግብ ክልል ኳሶች ቢላኩም ሁነኛ አጥቂ ባለመኖሩ ማንም ሲጠቀምባቸው አይስተዋሉም።

በደደቢት በኩል እንደሚታወቀው በዚህ ጨዋታ በቅጣት ምክንያት ያለ ድንቁ አጥቂ ጌታነህ ከበደ እና አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ወደ ሜዳ የሚገባ ሲሆን ቡድኑ በሊጉ ካስቆጠራቸው 24 ግቦች 9ኙን ያስቆጠረውን የቡድኑን አምበል እና ድንቅ አጥቂ ሳይዝ ወደ ሜዳ መግባቱ ለደደቢት ጥሩ ዜና አይሆንም። በተቃራኒው በደደቢት በኩል እንደ መልካም ዜና ሊነሳ የሚችለው ነገር የአክዌር ቻሞ የጌታነህ ከበደን ሚና የመሸፈን አቅሙ እንዲሁም መከላከያን 4-0 ባሸነፈበት ጨዋታ በጉዳት ምክንያት ያልተሰለፈው ወጣቱ አጥቂ አቤል ያለው ወደ ሜዳ መመለሱ ለደደቢት እፎይ የሚያሰኝ ዜና ነው። ከዚህ በተጨማሪ የመሀል ሜዳ ተጫዋቾቹ አንጋፋው አስራት መገርሳ የአብስራ ተስፋዬ እና አቤል እንዳለ እያሳዩ ያሉት አስደናቂ ጥምረት በዛሬው ጨዋታ ለደደቢት እንደ ጥንካሬ ሊነሳ የሚችል ነው።

በሊጉ ያላቸው አቅም፦

በአጠቃላይ በዘንድሮው በሊጉ ደደቢት ካደረጋቸው 13ጨዋታዎች በ8ቱ አሸንፎ በ4ቱ አቻ ተለያይቶ በ1ብቻ ተሸንፎ ማግኘት ከሚገባው 39 ነጥቦች 28ቱን አሳክቶ የሊጉ አናት ላይ መቀመጥ ሲችል ቅ/ጊዮርጊስም በተመሳሳይ 13 ጨዋታዎችን አከናውኖ 5ጨዋታዎችን አሸንፎ በ7ቱ አቻ ወጥቶ እንደ ደደቢት ሁሉ በ1ብቻ ተሸንፎ ከመሪው ደደቢት በ6ነጥቦች በማነስ በ22 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ኢንተርናሽናል አርቢትር ለሚ ንጉሴ የሚመሩት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ልክ 10:00 ሲል በአ/አ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አብዱላጢፍ ባምባ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...