መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሙሉአለም መስፍን ውል ሲያራዝም ደስታ ደሙን አስፈርሟል
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የሙሉአለም መስፍን ውል ሲያራዝም ደስታ ደሙን አስፈርሟል

አጋራ
አጋራ

የተጨዋቾች ውል በማራዘምና አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈረም የተጠመዱት ፈሩሰኞቹ የክረምቱ ሥስተኛ ፈራሚያቸውን ከቢጫ ለባሾቹ ወልዋሎ አድርገዋል።በመቐለ 70 እንደርታ አሸናፊነት በተጠናቀቀው የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ዘንድሮ ካሳያቸው ተስፈኛ ተጨዋች አንዱ የሆነው ደስታ ደሙ የፈረሰኞቹ የክረምቱ ሶስተኛ ፈራሚ በመሆን ተቀላቅሏል።

በብዙ ታላላቅ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው ደስታ በዘንድሮ ዓመት ከወልዋሎ ውጪ ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሄራዊ ቡድን እና ለቻን ብሄራዊ ቡድን ተመርጦ መጫወት ችሏል።በተጨማሪም የኦሎምፒክ ቡድኑ አዲስ አበባ ላይ ማሊን በገጠመበት ጨዋታ በብሄራዊ ቡድኑ መለያ የመጀመርያ ግቡን ማስመዝገብ ችሏል።

በተያያዘ ዜና ጊዮርጊስ ቤትን ከተቀላቀለ 3 ዓመታትን የደፈነው አማካዩ ሙሉአለም መስፍን ከፈረሰኞቹ ጋር ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል።በ2009 ከሲዳማ ቡና ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፈረመው ጠንካራው የአማካይ ክፍል ተጨዋች ባለፋት 4 ዓመታት በብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ጥሪ ቀርቦለት ሃገሩን በማገልገል ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያን በፕሪምየር ሊግን ካነሱ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠሩት ጊዮርጊሶች የቀጣዩን ዓመት ዋንጫ ወደ ጊዮርጊስ ለማምጣት ከደስታ ደሙ በተጨማሪ የአብስራ ተስፋዬን እና እቤል እንዳለን ከደደቢት ሲያስፈርሙ፤ የአብዱልከሪም መሐመድ፣ሳላዲን በርጌቾ፣ለዓለም ብርሃኑ፣ጋዲሳ መብራቴ፣አሜ መሐመድ ና ናትናኤል ዘልቀን ውል ለሁለት ዓመት ማራዘማቸው ሚታወስ ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...