መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ​ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ህዳር 12/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

​ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ህዳር 12/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡

አጋራ
አጋራ
    ​ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ህዳር 12/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡

    ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?

    -ከሀገር ውስጥ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ጨዋታዎች በተመለከተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቐሌ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ለሽንፈት ተቃርቦ በመጨረሻው ሰዓት ላይ የአቻነትን ግብ በማስቆጠር ነጥብ ስለተጋራበት ጨዋታና ወሳኟንም ግብ በማስቆጠር የቡድኑን ደጋፊዎች ካስደሰተው ምንተስኖት አዳነ ጋር ቃለ- ምልልስን ያደረግን ሲሆን ሌላው ደግሞ በእዚሁ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ ጋር የመጀመሪያውን ግጥሚያ በማድረግ ውድድሩን በድል ስለከፈተበትና ጨዋታውንም በማሸነፋቸው ስለተፈጠረባቸው የደስታ ስሜት የኢትዮጵያ ቡናውን ተከላካይ ኤፍሬም ወንደወሰንን አናግረን ምላሻቸውን ሰጥተውናል፡፡

    -‘‘Oldies but Goodies” በሚለው ተወዳጅ አምዳችን ላይ እንግዳችን በመሆን ወደ ኋሊት ወስዶ ትዝታውን የሚያስቃኘን ባለተረኛ የቀድሞ ተጨዋች ደግሞ የም/ጦር፣ የአዲስ አበባ ሲሚንቶ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የብርሃንና ሰላም፣ የትራንስ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ወጣት ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂና የዋናው ብሔራዊ ቡድንም ተጨዋች የነበረው ተስፋዬ አድማሱ /ኦስትሪች/ ነው፡፡ በጨዋታ እያዋዛ ታሪኩን ያስኮሞኩመናል፤ እንዳያመልጦት፡፡

    ከባህር ማዶ፡- በአርሰናል የደርቢ ድልን አስመልክቶ ሽኮድራን ሙስታፊ፣ መሱት ኦዚልና ቤለሪን ከጨዋታው በኋላ የሰጡት አስተያየት፣ የወቅቱ የዓለም ኮከብ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ልዩ ቃለ- ምልልስ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ የተመለሱት የማን. ዩናይትዶቹ ፖል ፖግባና ዝላታን ኢብራሂሞቪች የሰጡት ያልተሰማ ቃለ-ምልልስና ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡

    በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ይጎብኙን፡፡

    ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

    መልካም ንባብ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...