ባህርዳር ከተማ ወጣቱን ተከላካይ ሰለሙን ውዴሳን ከመድን አስፈርሟል።ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በግሉ ከመድን ጋር የተሳካ ጊዜ ያሳለፈው ሰለሙን ውዴሳ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል።
ወንድሜነህ ደረጄን እና አስናቀ ሞገስን ያጣው የባህርዳር ተካላካይ ክፍል ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን በአብርሃም መብራህቱ ጥሪ የቀረበለትን ሰለሙን ውዴሳን ማስፈረማቸው ተከትሎ በሁለቱ ተጨዋቾች መልቀቅ ሊፈጠር ሚችለውን ክፍተት ለመድፈን ሊያግዛቸው እንደሚችል ይገመታል።
ባህርዳር ከተማ ሰለሙን ውዴሳን ማስፈረሙን ተከትሎ በክረምቱ ያስፈረማቸው ተጨዋቾች ቁጥር 6 አድርሷል።
አስተያየት ይስጡ