መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ራምኬል ሎክ የ2 ጨዋታ ቅጣት ተነሳለት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

ራምኬል ሎክ የ2 ጨዋታ ቅጣት ተነሳለት

አጋራ
አጋራ

 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲዬም  ፋሲል ከተማ በኢትዮጵያ ቡና 3ለ2 በተሸነፈበት ጨዋታ ራምኬል ሎክ ተገቢ ያልሆነ ጥፋት አጥፍተሃል በሚል ከሜዳ በቀይ ካርድ  መውጣቱ የሚታወስ ነው።
የእግር ኳስ ፌደሬሺኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጨዋቹ ብር (4000,00)አራት ሺ እንዲከፍልና የ 4 ጨዋታ ቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ለተጫዋቹ የተሰጠው ቀይ ካርድ አግባብነት የሌለው መሆኑን በመግለፅ በቁጥር 

ፋ/ከ/እ/ክ 444/09 በቀን 15/06/10 ዓ/ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  ባስገቡት የይገባኝ ደብዳቤ መሰረት ጉዳዩን የእግር ኳስ ኳስ ፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ተመልክቶ በ26/06/10ዓ/ም የእግር  ኳስ ፌዴሬሽኑ ለክለቡ በፃፈው  ደብዳቤ ራምኬል ሎክ ከተቀጣው የ4 ጨዋታ ቅጣት ላይ 2ቱን ማንሳቱን ገልጿል።
በመሆኑም  ተጨዋቹ  ከዚህ በፊት ክለቡ ፋሲል ከነማ በሜዳው አርባምንጭ ከነማን 1ለ0 ያሸነፈበት ጨዋታ ያለፈው ሲሆን የ2ኛው ዙር የፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ  ጨዋታ ፋሲል ከነማ  ከ ወልዋሎ አ.ዩ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ የሚያልፈው ሲሆን  በ17ኛው ሳምንት የሊግ ጨዋታ አፄዎቹ ከሜዳቸው ውጭ በአዲስ አበባ ስታዲዬም  ከፈረሰኞቹ ጋር በሚያደርጉት  ጨዋታ ራምኬል ሎክ ወደ ሜዳ ተመልሶ  የቀድሞ ክለቡን  የሚገጥም ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...