በ4ተኛው ሳምንት ቅዳሜ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጭዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን አስተናግዶ ሶስት ለባዶ አሸንፏል።ባለ ሜዳዎቹ ፋሲል ከነማዎች ወደ ወልቂጤ ተጉዞ 1-0 ከተሸነፈው ስብስብ ውስጥ ኢዙ አዙካ እና ያሬድ ባየህን በኦሲ ማውሊ እና አለምብርሀን ይግዛው ተክተው ገብተዋል፡፡
በርካታ ሙከራ በታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ ፋሲል ከነማዎች ገና እንደተጀመረ ነበር በሱራፌል ዳኛቸው(ነብሮ) አማካኝነት ሙከራ ማድረግ የጀመሩት፡፡የመጀመሪያ 10 ደቂቃዎች በሁለቱም ቡድን ተደጋጋሚ ሙከራ ያየንበት ነበር፡፡ በ አስራ አንድኛው ደቂቃ ኡሲ ማውሊ ከሽመክት ጉግሳ የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ሆሳህና መረብ ላይ አሳርፏታል፡፡ፋሲል ከነማውች ጎሉን ካስቆጠሩ በሁዋላ ተቀዛቅዘው ታይተዋል በአንፃሩ ሀድያ ሆሳዕና ተደጋጋሚ ሙከራ እና ማራኪ ጨዋታ ለተመልካች አሳይተዋል።

ከመጀመሪያው አጋማሽ በተቃራኒ ብዙም ማራኪ ያልነበረው እና የሀድያ ሆሳህና ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ከ ጨዋታው መሃል ዳኛ ጋር ሰጣገባ ሲገቡ ያየንበት ነበር።ጅብሪል አህመድ በሳጥን ውስጥ ያገኘውን ኳስ አክርሮ መቶ እና በረኛው ያዳነበት ግሩም ሙከራ የተጀመረው ሁለተኛው አጋማሽ ፋሲሎች በሙጅድ ቃሲም እና ሱራፌል ዳኛቸው ተደጋጋሚ ሙከራ መሪነታቸውን የሚያጠናክሩበት አጋጣሚ አግኝተው ነበር።በተለይም ሙጅብ ቃሲም ሽመክት ጉግሳ አክርሮ የመታውን ኳስ በረኛው ሲተፋው ያገኘውን ግልጽ አጋጣሚ ያመከነበት ተጠቃሽ ነበር፡፡በስልሳ ሰባተኛው ደቂቃ ላይ ሙጅብ ቃሲም ሳጥን ውስጥ በመጠለፉ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝተዋል።ሆኖም የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾች የተሰጠብን ፍፁም ቅጣት ምት ተገቢ አይደለም በማለት ያልተገባ ፀባይ አሳይተዋል በዚህም የተነሳ አንድ ተጫዋች ከሜዳ ተወግዶባቸዋል እና ሙጅብ ቃሲም ያገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት በሚገባ አስቆጥሮ የፋሲል ከነማን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡መደበኛው ደቂቃ ተጠናቆ በተጨማሪ ደቂቃ ላይ አምሳሉ ጥላሁን(ሳኛ) ያሻማውን ኳስ በሱራፌል ዳኛቸው ተቀይሮ የገባው በዛብህ መለዮ በግንባር በመግጨት አስቆጥሩዋል፡፡ጨዋታውም በፋሲል ከነማ 3-0 ተጠናቋል።
ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 7 በማሳደግ ወደ መሪዎች ተርታ ተመድቡዋል በአንፃሩ እንግዳው ቡድን ሀድያ ሆሳዕና 1 ነጥብ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ተቀምጧል፡፡
አስተያየት ይስጡ