በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን 6ቱ በክልል አንዱ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ ተደርገዋል። ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል ሁለቱን በዚህ ሪፖርት ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን አቅርበንላችኋል።
ጨዋታ 1 አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ
9:00 ሲል አዳማ ላይ የጀመረው የአዳማ ከተማና የወላይታ ድቻ ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። ግብ በማስቆጠሩ አዳማ ከተማዎች ቀዳሚ የነበሩ ሲሆን 11ኛው ደቂቃ ላይ ዳዋ ሁቴሳ ግብ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ በአዳማ ከተማ መሪነት መጠናቀቅ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ቀሪዎቹ ሶስት ግቦች በሁለተኛው አጋማሽ የተቆጠሩ ሲሆን የወላይታ ድቻው ባዬ ገዛኸኝ 55ኛው ደቂቃ ላይ ከፍ.ቅ.ም ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። ከዚህች ግብ መቆጠር 4ደቂቃዎች በኋላ 59ኛው ደቂቃ ላይ እድሪስ ሰዒድ እንግዳውን ወላይታ ድቻን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር። ሆኖም ከ3ደቂቃዎች በኋላ የአዳማ ከተማው ዳዋ ሁቴሳ በፍ.ቅ.ም ቡድኑን አቻ አድርጎ ጨዋታው 2-2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ውጤቱንም ተከተሎ አዳማ ከተማ በ6ነጥቦች 7ኛ ወላይታ ድቻ ደግሞ በ5ነጥቦች 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ጨዋታ 2 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ስሑል ሽረ
በተመሳሳይ 9:00 አ.አ ስታዲየም ላይ በተደረገ ጨዋታ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳነውን ቅዱስ ጊዮርጊስን ከ ስሑል ሽረ ያለ አገናኝቶ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ እስካሁን በሊጉ 1ጨዋታ ብቻ ሲሆን ማሸነፍ የቻለው ማስቆጠር የቻለውም 1ግብ ብቻ ነው በቡድኑ እንደ መልካም ነገር ሊገለፅ የሚችለው አንድ ነገር ቢኖር በሊጉ እስካሁን ግብ ያልተቆጠረበት ቡድን መሆኑ ብቻ ነው። ይህንን አቻ ውጤት ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ6 ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ስሑል ሽረ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ2 ነጥቦች ዝቅ ብሎ በ4 ነጥቦች 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሊጉን ወልዋሎ አ.ዩ. በ10 ነጥቦች ሲመራ ፋሲል ከተማ፣ ባህርዳር ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ በእኩል 7ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኮከብ ጎል አግቢነቱን ደግሞ የፋሲል ከተማው ሙጂብ ቃሲም በ4 ግቦች ሲመራ አዲስ ግደይ፣ ዳዋ ሁቴሳ እና ሰመረ ሀፍተይ በእኩል 3ግቦች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።