በውጤት ቀውስ ውስጥ ሚገኝው አርባምንጭ ከተማ በአዲስ አሰልጣኙ እዮብ ማለ እየተመራ ከብዙ ሽንፈት በሃላ በሜዳው አዳማ ከተማን አስተናግዶ ፀጋዬ አበራ ባገባት ብቸኛ ግብ ማሸነፍ ችሏል፡፡
ባለሜዳዎቹ አርባምንጮች ጥሩ ሆነው በቆዩበት የመጀመርያው አጋማሽ ጫና ፈጥረው በመጫወት በ2 እና በ9 ደቂቃ በአዳማ የግብ ክልል ውስጥ ቢወድቁም ዳኛው በዝምታ አልፈውታል፡፡ በተደጋጋሚ ጫና የፈጠሩት አዞዎቹ በ19 ደቂቃ ከአንበሉ አማኑኤል ጎበና የተላከለትን ኳስ ተመስገን ካስትሮ ወደ ግብ ሞክሮት በረኛው ሲተፋው በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ፀጋዬ አበራ ወደ ግብ በመቀየር ባለሜዳዎቹን አርባምንጮችን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡
ከዚች ግብ መቆጠር በሃላ አዳማ ከተማወች መጠነኛ እንቅስቃሴ ማድረግ ሲችሉ አቻ የሚሆኑበትን እድል ከግራ ክንፍ የተሻማችሁን ኳስ አጥቂው ዳዋ እጢሶ በግንባሩ ቢሞክረውም ቋሚ ብረቱን ታካ ወታለች፡፡
ከዚች ሙከራ በሃላ እንቢዛም እንቅስቃሴ ባይደረግም ባለሜዳወቹ አርባምንጮች በአለልኝ አዘነ ከርቀት በሚመቱ ኳሶች ሁለተኛ ጎል ለማግኝት ሲሞክሩ ተስተውለዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተቀዛቅዘው የታዩበት ጨዋታን ስንመለከት አልፎ አልፎ በ 54 ደቂቃ አማኑኤል ጎበና እንዲሁም 64 ደቂቃ ወርቅይታደስ አበበ ከአርባምንጭ በኩል እንዲሁም 61 ደቂቃ ዳዋ ኢጢሶ ከአዳማ ከሞከርዏቸው ለጎል የቀረቡ ኳሶች ውጪ በአርባምንጭ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ በሜዳ ውስጥ በመውደቅ ከመሀል ዳኛው የቢጫ ካርዶችን ሲመለከቱ ቆይተዋል፡፡
በዚህም የተነሳ እንግዳዎቹ አዳማዎች የአቻ ጎል ለማግኝት ሲቸገሩ ታይተዋል፡፡
በዚህም ውዝግብ የታጀበው ሁለተኛው አጋማሽ በቂ የሆነ የኳስ ፍሰት ሳንመለከትበት በመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠረችው ጎል አርባምንጭ ከተማ 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡
ይህንንም ድል ተከትሎ አዞዎቹ ነጥባቸውን ከፍ ማድረግ ሲችሉ፡፡ አዳማ ከተማዎች ከመሪዎቹ ተርታ መሰለፍ የሚችሉትን እድል ሳይጠቀሙ ቀርተዋል፡፡
አሰልጣኝ እዮብ ማለ – አርባምንጭ ከተማ
“በመጀመሪያ ጨዋታ ቡድኑን እየመራሁ በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በቀጣይ እሚኖረን ከሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በዚሁ የአሸናፊነት መንፈስ እንጫወታለን፡፡ ጨዋታው ውጤቱን ይገልጸዋል ፡፡ አርባምንጭ ከተማ ሊወርድ ነው እየተባለ በአንዳንድ ሚዲያዎች እሚወራው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው፡፡አርባምንጭ ከተማ ትልቅ ቡድን ነው አይወርድም”
አሰልጣኝ ተገኔ ነጋሽ -አዳማ ከተማ“ጨዋታው ፈታኝ እንደሚሆን ጠብቀን ነበር፡፡ በሜዳው እንደመጫወቱ አርባምንጭ ከተማ ካለበት የውጤት ቀውስ አንጻር ለማሸነፍ አሊያም አቻ ውጤት ይዘን ለመውጣት ነበር፡፡ ወደ ሜዳ የገባነው ሆኖም ሳይሳካልን ተሸንፈን ወጥተናል፡፡በጨዋታው ጫና ፈጥረን ለመጫወት ችለናል፡፡ ሆኖም በውጤቱ አልተከፋሁም:: የዳኝነቱ ነገር አሁንም ይታሰብበት”
አስተያየት ይስጡ