በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በትግራይ ደርቢ በጉጉት የተጠበቀው የወልዋሎ አ.ዩ. እና የመቐለ ከተማ ጨዋታ በደጋፊዎች ረብሻ ተቋረጧል።

ልክ 9:00 ሰአት ሲል በፌዴራል ዳኛ ይርጋለም ወልደጊዮርጊስ ፊሽካ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ወልዋሎ 4-5-1 አሰላለፍ ይዘው የገቡ ሲሆን መቐለዎች ደግሞ 4-3-3 የጨዋታ ዘይቤ መርጠው ወደሜዳ ገብተዋል። የጨዋታው እንቅስቃሴ ተመጣጣኝ የሚባል የነበረ ሲሆን ባለሜዳዎቹ ወልዋሎዎች ኳስን መስርቶ ቶሎ ቶሎ ወደ መቐለ ሜዳ ሲደርሱ በአንፃሩ መቐለ ከተማዎች በመልሶ ማጥቃት በአማኑኤል ገብረሚካኤል እና ቢስማርክ ኦብያማንግ ለግብ የቀረቡ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ግብ በማግባት ረገድ ግን ባለሜዳዎቹ ቀዳሚ ነበሩ።

በ33ኛ ደቂቃ ላይ በጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ ከነበረው የወልዋሎ ጋናዊው ተጫዋች ሪችሞንድ ኦዶንጎ የተላከለትን ኳስ 5ቁጥሩ አሳሪ አልማህዲ ጨርፎ ወደ ግብነት ከቀየረው በኋላ መቐለዎች ወደ ጨዋታ ለመመለስ ትንሽ መደናገጥ የታየባቸው ይመስሉ ነበር። በዚህም በሁለቱም ቡድኖች መካከል ይሄ ነው የሚባል ሙከራ ሳይደረግ ዋና ዳኛው በመጀመርያ 45ደቂቃ ተጠናቆ 3ደቂቃ በመጨመር ጨዋታው ተጠናቋል።

ከዚህም በኋላ ተጫዋቾች እረፍት እንደወጡ ማን እንደጀመረው በማይታወቅ ሁኔታ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው በነበሩ የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች ድንጋዮች ሲወራወሩ ቁጥራቸው ምንያክል እንደሆነ እማይታወቅ የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች ላይ ጉዳት ሊደርስባቸው ችሏል። በዚህ ምክንያት ጨዋታው ከእረፍት በኋላ ሊቀጥል አልቻለም። የእለቱም ኮምሽነርና ዳኛው ጨዋታውን እንደማይቀጥል በማሳወቅ የሁለተኛ አጋማሽ ጨዋታ ሊቋረጥ ችሏል።
*በኢትዮጵያ የሊግ ጨዋታዎች በክለብ በደጋፊዎች መካከል እሚፈጠሩ ግጭቶች በመቀነሱ ፋንታ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱ በማነቃቃት ላይ እሚገኘው እግርኳሳችንን ማቀጨጩ እማይታበለ ሀቅ ነው። ባለድርሻ አካላትም እሚገባውን መፍትሔ እንዲፈጥሩለት ሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ መልእክቷን ታስተላልፋለች።
አስተያየት ይስጡ