መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ስሑል ሽረ ወደ አሸናፊነት መንገድ የተመለሰበትን ድል ሰበታ ላይ አስመዝግቧል
ሪፖርትሰበታ ከተማስሁል ሽረዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ስሑል ሽረ ወደ አሸናፊነት መንገድ የተመለሰበትን ድል ሰበታ ላይ አስመዝግቧል

አጋራ
አጋራ

 

ስሑል ሽረ በ28ኛው ደቂቃ በሀብታሙ ሸዋለም በኩል ባስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ከ5 ጨዋታዎች በኃላ ወደ አሸናፊነት መንገድ ተመልሷል።የሳምሶን አየለ ስብስብ ስሑል ሽረዎች በ6ተኛው ሳምንት ወልቂጤ ከተማን ከገጠመው ቀዋሚ 11 ብሩክ ሓዱሽ በሳሊፍ ፎፎና፣ሸዊት ዮሐንስ በረመዳን ናስር፣አክሊሉ ዋለልኝን በያሰር ሙገርዋ ቀይረው ወደ ሜዳ ሲገቡ ሰበታዎች በበኩላቸው ወላይታ ድቻን ካሸነፈው ቡድን አስቻለው ግርማ፣ሲይላ ዓሊባድራና ኢብራሂም ከድር ወጥተው ናትናኤል ጋንጁላ፣በኃይሉ አሰፋ ና ዳዊት እስጢፋኖስ ገብተዋል።

የሰበታዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ፣የስሑል ሽረዎች የተሻሉ የግብ እድሎች የታዩበት የመጀመርያ አጋማሽ፤ተመልካቹን ያዝናና ጥሩ ፍሰት ያለው ቅብብል በሰበታዎች በኩል ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ በስሑል ሽረዎች ተመልክተናል።ሰበታዎች ኳስን ከኃላ ለመመስረት በሚሞክሩበት ጊዜ አማካዩ ያሰር ሙገርዋ ከመስኡድ የነጠቀውን ኳስ በመጠቀም የበረኛው ዳንኤል አጃይ መውጣትን ተመልክቶ ከርቀት የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።ሙሉ በሙሉ መስመር ላይ ትኩረት ያደረገው የስሑል ሽረ አጨዋወት አልፎ አልፎ የሰበታን ተከላካይ ክፍልን ሲያስቸግር ነበር።የዚህ ማሳያ ዲድየር ሌብሪ ከግራ መስመር እየገፋ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን በመግባት መሬት ለመሬት የላከው ኳስ ወንድይፍራው ጌታሁን በጥሩ ሁኔታ መልሶበታል።መሀል ላይ መስኡድ መሀመድ፣ዳዊት እስጢፋኖስና ታደለ መንገሻ ያጣመሩት ሰበታዎች በጥሩ አጫጭር ቅብብሎሽ ወደ ሜዳው የመጨረሻ ክፍል ቢደርሱም መጨረሻ ላይ በነበራቸው የውሳኔ ችግር የጠሩ የግብ እድሎችን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።

በ27ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታውን መልክ የቀየረ ክስተት ተከሰተ፣ያሰር ሙገርዋ ከፍፁም ቅጣት ሳጥን ውጭ የመታው ኳስ በሰበታ ተጨዋቾች በእጅ መነካቱን ተከትሎ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ሀብታሙ ሸዋለም አስቆጥሮ ስሑላውያንን መሪ ማድረግ ችሏል።ወደ ኃላ አፈግፍገው መከላከልና በመልሶ ማጥቃት ምርጫጨውን ያደረጉት ስሑል ሽረዎች አብዱልለጢፍ መሀመድ ከግራ መስመር በረጅሙ በማሻማት ሳሊፍ ፎፎና ብቻውን ከበረኛው ጋር ቢያገናኘውም አይቮሪካስታዊው አጥቂ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።በአጫጭር ቅብብሎች ሜዳውን በማስፋት መጫወታቸውን የቀጠሉት ሰበታዎች ከቀኝ መስመር ጌቱ ሀይለማርያም ያሻማውን ኳስ ለግቡ ቅርብ የነበረው በኃይሉ ቱሳ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ጌቱ ሀይለማርያምን አስወጥተው ባኑ ዲያዋራን ያስገቡት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የጨዋታ ስልታቸውን ወደ 3-5-2 ቀይረው ከመጀመርያው አጋማሽ በተሻለ መልኩ እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ሙሉ ሀይላቸውን ማጥቃት ላይ ማተኮራቸው ለስሑል ሽረዎች ፈጣን መልሶ ማጥቃት አጋልጥዋቸው ታይቷል።መጀመርያ አጋማሽ ላይ በብቸኛ አጥቂነት የተሰለፈው ፍፁም ገብረማርያም ከዳዊት እስጢፋኖስ የተቀበለውን ኳስ በመጠቀም መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ከግቡ ጎን ለትንሽ ወጥቷል።መስመር ላይ ትኩረት ያደረገ ፈጣን መልሶ ማጥቃትን ምርጫጨውን ያደረጉት ስሑል ሽረዎች በሳሊፍ ፎፎና፣አብዱልለጢፍ መሀመድ ና ዲድየር ሌብሪ አማካኝነት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ቢያደርጉም እድሎቻቸውን ሳይጠቀሙ ቀርተዋል።በተለይ ሳሊፍ ፎፎና ያመከናቸው ኳሶች ለማመን ሚከብዱና የስሑላውያንን መሪነት ከፍ ማድረግ ሚችሉ ነበር።እንግዶቹ ሰበታዎች አቻ ሚያደርጋቸውን ግብ ለማግኘት ናትናኤል ጋንቹልን በ ፍርዳወቅ ሲሳይ፣ታደለ መንገሻን በሳሙኤል ታዬ በመቀየር የጨዋታ ስልታቸውንወደ 4-4-2 በመለወጥ ግብ ለማግኘት ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቶ ጨዋታው በባለ ሜዳዎቹ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ ስሑል ሽረዎች ነጥባቸውን 9 አድርሰው ደረጃቸውን ወደ ሰባተኝነት ከፍ አድርገዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...