መነሻ ገጽ ሪፖርት ​ሪፖርት | መከላከያ ከሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ።
ሪፖርትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

​ሪፖርት | መከላከያ ከሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ።

አጋራ
አጋራ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት የእሁድ  የሊጉ ጨዋታ አ/አ ላይ ተደርጎ መከላከያ ከሲዳማ ቡና ተገናኝተው ጨዋታቸውን ያለገብ 0-0 ፈፅመዋል። 
በጨዋታው መከላከያ በ4-4-2 የጨዋታ ዘይቤ ይዞ ወደ ሜዳ ሲገባ ሲዳማ ቡና በአንፃሩ በ4-4-2 የጨዋታ ዘይቤ ይዞ መግባት ችሏል። በመጀመሪያው አጋማሽ ሲዳማ ቡናዎች ጫና ፈጥረው ለመጫወት ጥረት ሲያደርጉና ወደ መከላከያ ግብ ክልል በመድረሱ ረገድ የተሻሉ ቢሆንም ኳስና መረብን ማገናኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።

15ኛው ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናው ሀብታሙ ገዛኸኝ የመታው ኳስ ወደ ውጭ ወጥቷል። በመጀመሪያዎቹ 25 እና 30ደቂቃዎች ውስጥ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ሀይል የተቀላቀለበት ጨዋታ ሲጫወቱ ተስተውሏል። 31ኛው ደቂቃ ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት ተከትሎ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮት ኳሱ በርቀት ወደ ውጭ ወጥቷል። ከዚህች ሙከራ ፫,3ደቂቃዎች በኋላ 34ኛው ደቂቃ ላይ የመከላከያ የግብ ክልል ውስጥ ኳስ በእጅ ተነክቷል በማለት ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም የዕለቱ ዳኛ ጨዋታው እንዲቀጥል አድርገዋል። 42ኛው ደቂቃ ላይ የመከላከያው ሳሙኤል ሳሊሶ የመታው ቅጣት ምት የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ወደ ውጭ ወጥቷል። ይህች አጋጣሚ በጨዋታው ከታዩት አጋጣሚዎች ሁሉ የተሻለች ነበረች። ከ1ደቂቃ በኋላ የመከላከያው ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ የሰራውን ስህተት ተከትሎ የተገኘውን ድንቅ አጋጣሚ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ ሳይጠቀምበት የቀረው ኳስ በሲዳማ ቡና በኩል እጅግ የምታስቆጭ አጋጣሚ ነበረች። በዚህም የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ 0-0 ተጠናቋል። 

በሁለተኛው አጋማሽም እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ ተደጋጋሚ ረጃጅም ኳሶችና ጉሽሚያዎች የበዙበት ነበር። 67ኛው ደቂቃ ላይ የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ 69ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ሳሙኤል ታዬ የሞከሯቸው ኳሶች ወደውጭ ወጥተዋል። 78ኛው ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናው ሀብታሙ ገዛኸን የመታው ኳስ ወደውጭ  ወጥቷል። ከዚህ በኋላም የረባ እንቅስቃሴ ሳይስተዋልበት 0-0 ተጠናቋል።

የአሰልጣኞች አስተያየት

አሰልጣኝ ምንያምር ፀጋዬ ~ መከላከያ

“በጨዋታው ከነበረብን እንቅስቃሴ አንፃር አንድ ነጥብ ማግኘት ያንሰናል። አሸንፈን መውጣት ነበረብን። ከእረፍት በፊት እና በኃላ ያገኘናቸው አራት እና አምስት የሚሆኑ አጋጣሚዎች ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ነበሩ። ጊዜ ቢፈጅም ይህን ችግራችንን እናሻሽላለን።”

አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ ~ ሲዳማ ቡና

“በመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጥንቃቄ ላይ ያመዘነ ጨዋታ ነበር። ብዙም ውበት አልነበረውም። በ2ኛ አጋማሽ መጨረሻ አካባቢ የመስመር ዳኛው ከጨዋታ ውጪ የነበሩ ኳሶችን በመፍቀድ ጫና አሳድሮብን ነበር።”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...