መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ ሪፖርት | መቐለ 70 እንደርታ ወደ ዋንጫ የሚያደርገውን ግስጋሴ ያስቀጠለበት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል
መቐለ 70 እንደርታመቐለ ከተማሪፖርትአዳማ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | መቐለ 70 እንደርታ ወደ ዋንጫ የሚያደርገውን ግስጋሴ ያስቀጠለበት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል

አጋራ
አጋራ

በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ በሜዳው ትግራይ ስታድየም አዳማ ከተማን ያስተናገደው መቐለ 70 እንደርታ በአማኑኤል ገብረሚካኤል እና ያሬድ ከበደ አማካኝነት ባስቆጠርዋቸው ሁለት ግቦች ጣፋጭ ሥስት ነጥቦችን ማሳካት ችልዋል።

በ20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ በባህርዳር ከተማ ከተሸነፈው ቡድን ሥስት ቅያሬዎችን ማለትም ቢያድግልኝ ኤልያስን በስዩም ተስፋዬ፣ሄኖክ ኢሰያስን በአንተነህ ገብረክርስቶስ፣ጅብሪል መሐመድን በዮናስ ገረመው ሲቀይሩ አዳማዎች በኩላቸው በሃዋሳ ከተሸነፈው ቡድን ከንአን ማርክነህን በቡልቻ ሹራ፣ሱሌይማን መሐመድን በሱራፌል ዳንኤል በመቀየር ወደ ጨዋታው ገብተዋል።

ብዙ ሙከራዎች ባልታዩበት የመጀመርያው እጋማሽ በ4-4-2 ዳይመንድ አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት መቐለዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው ተጫውተዋል።መሃል ሜዳ ላይ ተደጋጋሚ የኳስ ቅብብሎችን ያደረጉት መቐለዎች ኳሶችን የሜዳው መጨረሻ ክፍል ላይ ማድረስ ሲቸግራቸው ታይቷል።የዚህም ማሳያ መጀመርያው 45 ላይ የፈጠርዋቸው የግብ ዕድሎች የተገኙት ከቆሙ ኳሶች ነበር፤ሚኪኤሌ ደስታ ከማአዘን ምት ያሻማው ኦሰይ ማውሊ በግምባሩ ገጭቶት ወደ ውጭ የወጣው በተመሳሳይ ሃይደር ሸረፋ ከቅጣት ምት በቀጥታ መትቶት ሮበርት ኦዱንካራ የያዘበት ተጠቃሽ የመቐለ ሙከራዎች ናቸው።የጨዋታ ብልጫቸውን ያስቀጠሉት ምዓም እናብሶቹ በ13ኛው ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ሳጥን ላይ ምኞት ደበበ በኦሰይ ማውሊ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት አማኑኤል ገብረሚካኤል እስቆጥሮ መቐለን መሪ ማድረግ ችልዋል።በ4-2-3-1 እሰላለፍ ቡልቻ ሹራን በእጥቂነት ያሰለፋት አዳማዎች የመጀመርያው እጋማሽ መጨረሻ ላይ በበረከት ደስታ እማካኝነት ያደረጓቸው ሙከራዎች በመቐለ 70 እንደርታው በረኛ ፊሊፕ ኦቮኖ ተመልሰዋል።

ድራማዊ ክስተቶችና ተደጋጋሚ ጥፋቶች በታየበት ሁለተኛው እጋማሽ እሁንም በተመሳሳይ መልኩ የመቐለ 70 እንደርታ ብልጫ የታየበት ነበር።በ4 ደቂቃ ልዩነት ውስጥ በተመለከቷቸው ሁለት ቢጫ ካርዶች የግራ መስመር ተመላላሹ ሱሌይማን ሰሚድን በ74ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ሊሰናበት ችሏል።ከቀይ ካርዱ ክስተት ሁለት ደቂቃዎች በኃላ ከግራ መስመር በኩል የተገኘውን ቅጣት ምት ወደ መቐለ የፍጹም ቅጣት ሳጥን ውስጥ አዳማዎች በአዲስ ህንጻ አማካኝነት እስቆጥረው አቻ መሆን ችለዋል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ሙሉ ሀይላቸውን ማጥቃት ላይ ያሰማሩት መቐለ 70 እንደርታዎች በኦሰይ ማውሊ እና ያሬድ ከበደ እማካኝነት ሙከራዎችን ቢያደርጉም የአዳማን መረብ መድፈር አልቻሉም።

ሆኖም መደበኛው 90 ደቂቃ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ሲቀሩት በአዳማ የፍፁም ቅጣት ሳጥን በግራ በኩል ዮናስ ገረመው ያሾለከውን ኳስ ኦሰይ ማውሊ መሬት ለመሬት ወደ ውስጥ ሲሻግረው ነጻ አቋቋም ላይ የነበረው የፊት መስመር ጥቂው ያሬድ ከበደ በቀላሉ አስቆጥሮ ሙሉ ስታድየሙን በደስታ አስፈንጥዟል።

ውጤቱን ተከትሎ መቐለ 70 እንደርታ ነጥቡን 45 በማድረስ ከተከታዮቹ ያለውን ነጥብ ልዩነት እስጠብቆ ወጥቷል።


[team_standings 17713]

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ በመድን ሲሸነፍ የጣና ሞገዶች እና ሰጎኖቹ ድል ቀንቷቸዋል

በሊጉ የሳምንቱ የማሳረጊያ ቀናት ሦስት ጨዋታዎች በኢትዮጵያ መድን ፣ ባህርዳር ከተማ እና...