በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት 1 ጨዋታ ዛሬ መቐለ ላይ ተከናውኖ መቐለ ከተማ እና ሲዳማ ቡና በግዙፉ መቐለ ስታድየም ተገናኝተው ባለሜዳዎቹ የጨዋታው መገባደጃ ላይ ባስቆጠሩት ግብ ማሸነፍ ችለዋል።

ይህ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት መቐለ ከነማ ደጋፊዎች በስቴድየሙና በከተማው ዙርያ በተተከሉ የደም መለገሻ ድንኳኖች ደም ለግሰው ወደ ሜዳ ገብተዋል።
በጠቅላላ ከእረፍት በፊት በሲዳማም በመቐለም ይሄነው የሚባል አሰደንጋጭ ሙከራና ቶሎቶሎ ወደ ግብ መድረስ ያልታየበት ጨዋታ ነበር። ሲዳማ ቡናዎች እንደ ቡድን በመጀመርያው 45ኛ ደቂቃ ታክቲካል ዲስፒሊን ሲያከብሩና ተጠንቅቀው ሲጫወቱ በመቐለ በኩል ደሞ የተቆራረጠ ሶስቱ ክፍሎች ማለትም ተከላካይ እና አማካይ ብሎም አጥቂ ክፍላቸው በመሃል ተለያይተው ነበር። በዚም በ43ኛው ደቂቃ ከያሬድ ከበደ የተላከለተን ኳስ 11ቁጥሩ የመቐለ ከተማው አማኒኤል ገብረሚካኤል የሞከራት ኳስ በመጀመርያው 45 ከታዩ ሙከራዎች ለግብ የቀረበች ነበረች ፡፡ በዚች ሙከራ ወደ መልበሻ ለእረፍት ወጥተዋል
ከእረፍት በኋላ ሲዳማዎች ከእረፍት በፊት የነበረባቸው ብልጫ ሳያሳዩ በአንፃሩ ውጤት ለማስጠበቅ በሚመስለው መልኩ ወደ ኋላ አፈግፍገው እንደ ሞሪንሆ ባስ ማስቆም የመረጡ ሲሆን በአንፃሩ መቐለዎቹ ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ለመድረስ(fast break) ፈጣን የማጥቃትና ፕሬሲንግ ፉትቦል ተጭነው የተጫወቱ ሲሆኑ የሲዳማ ቡና ተከላካይ መስመር ሰብረው ግብ ለማስቆጠር ግን 87 ደቂቃ ግድ ብላቸዋል። በዚ ላይ የሲዳማዎቹ ተከላካዮች በጣም የሚገርም መናበብ የሚገርም መረዳዳት እና ደስ የሚል ፍጥነት ነበራቸው። በተለይ በሲዳማዎቹ በኩል ሃብታሙ ገዛሃኝና 4ቁጥሩ ክፍሌ ካዎ ያሬድ ከበደና አማኒኤል ገብረሚካኤል እንደፈለጉ እንዳይጫወቱ መፈናፈኛ አሰጥተዋቸው ውለዋል።
በእለቱ በመቐለ በኩል አጥቂዎቹ አማኒኤልና ያሬድ ከበረኛ ጋር አንድ ለአንድ እየተገናኙ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን ሲያባክኑ ታይተዋል።
በሲዳማ ቡና በኩል ግብ ጠባቂው መሳይ አያና እና ተከላካይ ክፍላቸው በጣም ጥሩ በሚባል መረጋጋት የነበረ ቢሆኑም በመጨረሻ ትኩረት የማጣት ችግር ግብ እንዲያስተናግዱ አድርጓቸዋል። የመደበኛው ጨዋታ ሊጠናቀቅ 3ደቂቃዎች ሲቀሩት 87ኛው ደቂቃ ላይ ጋናዊው ጋይስ አፖንግ በግምት ከግቡ 32ሜትር በግምት ርቀት ላይ መሬት ለመሬት አክርሮ የመታው ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ መቐለ ከተማን ባለድል ማድረግ ችሏል።
ውጤቱንም ተከትሎ 1ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው መቐለ ከነማ በ21 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
የአሰልጣኞች አስተያየት
አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ—መቐለ ከተማ
“የምንፈልገውን አግኝተናል፤ 3 ነጥብ ያስፈልገን ነበር ግዜ ፈጀብን እንጂ ምንፈልገው አግኝተናል፡፡ ለኔ የዛሬ ኮኮብ ያለ መሰልቸት እስከ 87ኛ ደቂቃ ድረስ በሞራል ከጎናችን ላልተለየው ደጋፊ ክሬዲቱን እሰጣለው እነሱ ናቸው የዛሬ man off the match እናመሰግናለን።”
አለማየሁ አባይነህ—ሲዳማ ቡና
“ጨዋታው ጥሩ ነበር፤ በመጀመሪያው አጋማሽ እኛ የተሻልን ነበርን፤ በሁለተኛው አጋማሽ ግን እነርሱ የተሻሉ ነበሩ፤ ወደፊት ግብ የማግባት ችግራችንን እና ስህተቶቻችንን አርመን ወደ አሸናፊነት እንመለሳለን።”
አስተያየት ይስጡ