ትግራይ ስታድየም ላይ የተካሄደው የመቐለ 70 እንደርታና ሃዋሳ ከተማ ጨዋታ በእንግዶቹ ሃዋሳ እሸናፊነት ተጠናቋል፤የሃዋሳን የማሸነፍያ ብቸኛ ግብ መስፍን ታፈሰ እስቆጥርዋል።መቐለ 70 እንደርታ ባሳለፍነው ሳምንት ሲዳማ ቡናን ከገጠመው ቡድን ፊሊፔ ኦቮኖን በሶፈንያስ ሰይፈ፣ኩዌኩ እንዶህን በእሚን ነስሩ እንዲሁም ሃይደር ሸረፋን በያሬድ ብርሃኑ ቀይረው ሲገቡ ሃዋሳ ከተማዎች በበኩላቸው ከጅማ እባጅፋር ግልር እቻ ከተለያየው ስብስብ ወንድማገኝ ማዕረግን በመስፍን ታፈሰ፣ዳንኤል ደርቤን በእስጨናቂ ሉቃስ በእጣቃላይ ሁለት ቅያሬዎችን በማድረግ ጨዋታውን ጀምረዋል።
ተመጣጣኝ በየጊዜው ሚቀያየር የኳስ ብልጫ በታየበት የመጀመርያ እጋማሽ ሁለቱም ቡድናች የግብ እድሎችን ፈጥረዋል።በ4-3-3 (እንደ እስፈላጊነቱ ወደ 4-2-3-1 ሚቀየር) የጨዋታ ስልት ወደ ሜዳ የገቡት ሃዋሳዎች ባለ ሜዳዎቹን መቐለ 70 እንደርታ ኳስ ከኃላ እንዳይመሰርቱ በማድረግ በሁለቱም መስመሮች በተለይ በግራ መስመር በተሰለፈው መስፍን ታፈሰ እማካኝነት ጥቃቶችን ሰፈጥሩ ታይቷል።መቐለዎች በበኩላቸው በ4-2-3-1 የተጨዋቾች እሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን ጨዋታው ላይ ትኩረት እድርገው የገቡትን የመስመር አጨዋወት መትግበር ተቸግረው ታይተዋል።የጨዋታው የመጀመርያ ጠንካራ ሙከራ መቐለ 70 እንደርታ በያሬድ ብርሃነ እማካኝነት እድርገዋል፤ በፍፁም ቅጣት ሳጥን ውስጥ በግራ በኩል ያገኘውን ኳስ ያሬድ በቀኝ እግሩ ቢመታውም ላውረንስ ላርቴ ተደርቦ እውጥቶበታል።እስራኤል እሸቱ ላይ ትኩረት ያደረገ ማጥቃትን ምርጫጨው ያደረጉት ሃዋሳዎች የጨዋታው የመጀመርያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራን ከመሃል ሜዳ የተላከውን ኳስ እስራኤል እሸቱ ከበረኛው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ከበረኛው እናት ለማሳለፍ ሲሞክር ሶፈንያስ ሰይፈ እድኖበታል።በእብዛኛው ግራ መስመር ላይ ትኩረት እድርገው ማጥቃታቸውን የቀጠሉት ሃዋሳዎች ጨዋታው በተጀመረ በ35ኛው ደቂቃ መሳይ ፓውሎስ ከግራ መስመር መሬት ለመሬት ያሻማውን ኳስ መስፍን ታፈሰ እስቆጥሮ ሃዋሳዎችን መሪ ማድረግ ችልዋል።ከግቡ መቆጠር በኃላ የእቻነትን ግብ ለማግኘት ሁለቱም መስመር እንዲሁም ከመሃል ሜዳ በሚላኩ ኳሶች በመጠቀም እድሎችን ለመፍጠር የሞከሩት ምዓም ኣናብስቶቹ ሙከራቸው ሊሳካ እልቻለም።በተለይም ያሬድ ከበደ ከሚኪኤለ ደስታ የተላከለትን ኳስ በመጠቀም ያሻማው ኳስ ሚኪኤለ በግምባሩ ቢመታውም ሶሆሆ ሜንሳህ ይዞበታል በተመሳሳይ እማኑኤል ገብረሚካኤል ከዮናስ ገረመው የተቀበለውን ኳስ ወደ ቀኝ እግሩ በመሳብ ቢመታውም ከግቡ እናት ወደ ላይ ወጥቷል።

ሁለተኛው እጋማሽ የመቐለዎች ሙሉ ብልጫ የታየበት ሃዋሳዎች ወደ ኃላ ማፈግፈግን መርጠው የታዩበት ነበር።መጀመርያ ኣጋማሽ ላይ እንደ ድሮው መንቀሳቀስ ያልቻለውን ያሬድ ከበደን በእንዳለ ከበደ በመቀየር የእጨዋወት ስልታቸውን ውደ 4-4-2 የቀየሩት ገብረመድህን ሃይለ ከመስመር በሚነሱ ኳሶች እድሎችን መፍጠር ችለዋል።ዮናስ ገረመው ከቀኝ መስመር እሻምቶት ያሬድ ብርሃነ በግንባር ቢገጨውም ለትንሽ ወደ ውጭ የወጣው የዚህ ለውጥ ማሳያ ነው።የጨዋታው ጊዜ በሄደ ቁጥር ጫና ውስጥ የገቡት የመቐለ ተጨዋቾች የሃዋሳን የተደራጀ መከላከልን መስበር ተቸግረዋል።መሃል ላይ ሚኪኤለ ደስታን በሃይደር ሸረፋ እንዲሁም እንተነህ ገብረክርስቶስን በሳሙኤል ሳሊሶን የቀየሩት መቐለዎች ሙከራዎች ቢያደርጉም የሃዋሳን የግብ መርበብ መድፈር ሳይችሉ ቀርተዋል።በሃይደር ሸረፋ፣እንዳለ ከበደና ያሬድ ብርሃነ እማካኝነት ወደ ግብ የቀረቡ መከራዎችን ያደረጉት መቐለዎች ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።መደበኛ ሁለተኛው እጋማሽ ተጠናቆ ዳኛው በጨመሩት 5 የባከኑ ደቂቃዎች ሳሙኤል ሳሊሶ ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት እማኑኤል ቢመታውም ሶሆሆ ሜንሳህ እድኖበታል።በዚህም መሰረት ጨዋታው በሃዋሳ ከተማ እሸናፊነት ተጠናቋል።
ውጤቱን ተከትሎ መቐለ 70 እንደርታ መሪነቱን ለፋሲል ከነማ ሲያስረክብ ሃዋሳ ከተማ ነጥባቸውን ወደ 34 በማድርስ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
አስተያየት ይስጡ