የፋሲል ከተማ እግር ኳስ ክለብ በቀጣይ አመት ተጠናክረዉና ተፎካካሪ ሁኖ ለመቅረብ በዝዉዉር ገበያው ላይ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
አፄዎቹ እስካሁን 6 ያህል የሀገር ዉስጥ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የዉጭ ተጫዋቾች ዝዉዉር ነሐሴ 25 መከፈቱን ተከትሎ ክለቡ በዛሬዉ እለት የኡጋንዳ ዜግነት ያለዉን ሮበርት ሴንቴንጎ እና ናይጄሬያዊዉን ክርስቶፈር አሞሶቢ ለሙከራ ክለቡን ተቀላቅለዋል፡፡
ሁለቱም ተጫዋቾች የፊት አጥቂ ሚና ያላቸዉ ተጫዋቾች ሲሆኑ ሴንቴንጎ ከዚህ ቀደም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለሁለት አመታት መጫዎት ችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተጫዋቹ በአሰልጣኝ ሚቾ በሚመራዉ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አባል የነበረና የኡጋንዳ ፕሪምየር ሊግን ለ4 አመት ያህል በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ማጠናቀቅ የቻለ ተጫዋቾች ነዉ፡፡ ቁመተ ለግላጋዉ ክርስቶፈር በበኩሉ በተለያዩ ሊጎች በፊት አጥቂነት እና በመስመር አማካይነት ተጫዉቷል፡፡ እኛም ክለባችን ለተቀላቀሉት አዲስ ተጫዋቾች እንኳን ደህና መጣህ እያልን መልካም ጊዜን እንድታሳልፉ እንመኛለን፡፡
አፄዎቹ የመጀመሪያ ግብ ጠባቂን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ የቀላቀሉ ሲሆን ከታዳጊ ቡድኑ ደግሞ 5 ያህል ወጣት ተጫዋቾችን በክለቡ አካትተዋል፡፡
source-offical fasil kenema fb page