በመጀመሪያው ዙር የኢትዬጵያ ኘሪሚየር ሊግ ውጤት አልባ ጉዞ በማድረግ በ15 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ወራጅ ቀጠናውን ተጠግተው በ13ኛነት ያጠናቀቀው መከላከያ አሰልጣኝ ምንያምር ፀጋዬን ካሰናበተ በሇላ በምትኩ አሰልጣኝ ስዩም ከበደን መቅጠሩ ታውቋል ፡፡
ከሰበታ ከተማ ጋር የቆዩት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ክለቡን ወደ ኘሪሚዬር ሊጉ ያሳድጉታል ቢባልም በጉዞ ላይ እያሉ መለያየታቸው ታውቋል፡፡አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከዚህ ቀደም በኘሪሚዬር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣አዳማ ከተማ፣የመኑንን ክለብ (አል-ሳክር) ባለፈው አመት አዲስ አበባ ከተማን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡
በውጤት ማጣት ላይ ያሉት መከላከያዎች የመውረድ ስጋት የተጋረጠባቸው ሲሆን ክለቡን ከመውረድ ሊታደገው የሚችለው ሁነኛ አሰልጣኝ ስዩም ስለመሆኑ የተማመኑ ይመስላሉ፡፡አሰልጣኙና ክለቡ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው መከላከያን በሁለተኛው ዙር ይዘው እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ