መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ “መቶ አለቃ ፍቃደ ዳኞችን ከጎረቤት እናስመጣለን በሚል የተናገሩት የሀገራችን ዳኞን ዝቅ ያደረገ ለመንገደኛ ሰው እንኳን የማይመጥን ነው” ኢንተ. ረዳት አርቢትር ትግል ግዛው
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

“መቶ አለቃ ፍቃደ ዳኞችን ከጎረቤት እናስመጣለን በሚል የተናገሩት የሀገራችን ዳኞን ዝቅ ያደረገ ለመንገደኛ ሰው እንኳን የማይመጥን ነው” ኢንተ. ረዳት አርቢትር ትግል ግዛው

አጋራ
አጋራ

የወልዋሎ ቡድን መሪ ማሩ ገ/ፃዲቅ
አርቢትር እያሱ ፈንቴን ከደበደበ በኋላ
የዳኞች የተቃውሞ መንገድ የመገናኛ ብዙኃን
ትኩረት ስቧል፡፡ ዳኞች በቃን አናጫወትም
ብለው አቋም ይዘዋል፡፡ 10 ቅድመ ሁኔታ
ይሟላ ካልተሟላ አናጫውትም ሲሉ
ክለቦችና ፌዴሬሽኑ ግን ውድድር መቋረጥ
የለበትም የሚሉ አቋሞችን እያራመዱ ነው፡
፡ ከሰሞንኛው ትኩረት ሳቢ ጉዳይ በኋላ
የዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ፕሬዚዳንት
የሆኑት አቶ ትግል ግዛው ከሀትሪኩ
ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ ስለ
አቋማቸው፣ አመፁ አያስጠይቅም ወይ?፣
ስለ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ አማራጮች፣
ዳኞች ብር ይቀበላሉ ስለሚባለው፣ ፌዴሬሽን
አካባቢ ዳኞችን ማባበል አለ ስለተባለውና
ሌሎች ጉዳዮች ፕሬዝዳንቱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ፡- ፌዴሬሽኑ ረቡእ እንወያይ
ብሎ ቀጠሮ ይዟል… ተስማማችሁ?
ትግል፡- የጥሪ ደብዳቤውን ወደ
ጉባኤ ስገባ ወስጃለሁ ምንም ሊፈጠር ግን
አይችልም፡፡ በተለይ ፌዴሬሽኑ የኛን ጠቅላላ
ጉባኤ የመጥራት መብቱ የለውም፡፡ ስራ
አስፈፃሚው መክሮበት ለግንቦት 4/2010 እሺ
ብለናል፡፡ ሰኞና ማክሰኞ አዳማ በሚካሄደውና
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጠራው ጉባኤ ላይ
ተካፍለን ገና ረቡዕ ነው የምንመለሰው፡፡
ለረቡዕ አንደርስም አርብ አ/አ ተገናኝተንና
ተነጋግረን ለቅዳሜ እንገኛለን፡፡ ከዚያ
ውጪ አማራጭ የለም፡፡ የተመልካቹን የኳስ
ፍቅር ስለምናውቅ ከግንቦት 20 እንዳያልፍ
አድርገናል፡፡ ፌዴሬሽኑ የተጠየቀውን
እናሟላለን ብሏል ይህን የሚያሟሉ ከሆነ
ቅዳሜ በተግባር ያሳዩናል፡፡

ሀትሪክ፡- ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ
ሰኞ ሲጠራ እሺ ብላችሁ ለፌዴሬሽኑ ጥሪ
አንደርስም
አይመስልም?
ማለት የመንግሥት ፍራቻ
ትግል፡- አይ! አይ! ለኛ ብቻ ሳይሆን

420 አካላትን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ
የጠራው፡፡ ከዚያ ውጭ ደብዳቤው ከደረሰኝ
ሳምንት አልፎኛል፡፡ እውቅና የሰጠኝ በዚያ
ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመሆኑ
መከበር አለበት በሙያ ደረጃ ከፌዴሬሽኑ
ጋር እንሰራለን እንጂ የኛ የበላይ ወጣቶችና
ስፖርት ሚኒስቴር ነው፡፡
ሀትሪክ፡- እስከ ግንቦት 20/2010 ድረስ
ያልነውን ካላሟላችሁ እናቆማለን ቢሉ
ይሻል ነበር አሁን ከሚያቆሙት የሚል
ነገር ሰማሁ… እናንተ ይህን መስመር
አላያችሁም?
ትግል፡- ይሄ የስህተት ሃሳብ ነው፡
፡ ከግንቦት 20 በፊት ዳኛ ቢሞትስ? ማን
ሊመልስ ይችላል ዳኛ ቢሞት ግንቦት 20
ይመልስልናል እንዴ? ይሄ ቀልድ ነው
ከለላዎቹ ከተስተካከሉ በህግ ጥላ ውስጥ
ስለምንሆን ስጋት አይኖርም፡፡
ሀትሪክ፡- ክለቦች የፋይናንስ መናጋት
ያመጣል እያሉ ነው?
ትግል፡- ክለቦች ያነሱት የበጀት ጥያቄ
ብዙም አስገራሚ አይደለም በፋይናንስ
አሰራር የማይዘጋ አካውንት የሚባል አለ፡
፡ እዚህ ውስጥ ከተው ሃምሌና ነሀሴ
መጫወት ይችላሉ፡፡ ከመጀመሪውኑ የከፍተኛ
ሊግ መዝጊያው ሀምሌ 7 ነው ይላል፡፡
በፌዴሬሽኑ አቆጣጠር ሰኔ 30 ከሀምሌ 7
ይቀድማል አይቀድምም የሚለውን እናንተ
መስክሩ (ሳቅ)
ሀትሪክ፡- መቶ አቃ ከውጪ ሀገራት
ዳኛ ይምጣ ያሉትን እንዴት አገኘኸው?
ትግል፡- በውጪ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ
እንኳን ዳኛ ለማስመጣት የመድሃኒት
ችግርን ለመፍታት አልቻልንም በሚባልበት
ሰዓት ከውጪ ላምጣ ካሉ ይሞክሩት፡፡ ይሄን
ግን የሌሎች ክለቦችን አይወክልም፡፡ ቤቱም
በዳኞች ላይ የደረሰውን በደል ተቃውሟል፡፡
ነገር ግን መቶ አለቃ ዳኞችን ከጎረቤት ሃገር
እናስመጣለን በሚል የተናገሩት የሃገራችን
ዳኛን ዝቅ ያደረገ ለመንገደኛ ሰው እንኳን
የማይመጥን ነው ነገር ለነገሩ ብዙም ይሳካል
ብለን አንጠብቅም፡፡
ሀትሪክ፡- የፈለገው ነገር ቢስተካከል
ዳኛን መቃወም ወይም መግፋት…ይቀራል
ብለን መናገር እንችላለን?
ትግል፡- ዳኛ በኢትዮጵያ እግር
ኳስ ውስጥ እንደሚያስፈልግ የታወቀው
ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ነው፡፡ የጨዋውን
ደጋፊ ስሜት ላለመግፋት ስንል ነው እኛም
ደግመን እናየዋለን ያልነው፡፡ የምንታገለው
የዳኞች ሰብዓዊ መብትም እንዲከበር ነው
የምንችለው ሁሉ ለማድረግ ተዘጋጅተናል፡፡

ሀትሪክ፡-
አይቀበሉም
ዳኞች
የሚለው
ብር
ጉዳይ
ይቀበላሉ
እንዴት

መጥፋት ይችላል?
ትግል፡- በወሬ አናምንም፡፡ ሰው
ለመያዝ ተገቢ የሆነ መረጃ ያስፈልጋል፡፡
መረጃ እስከሌለ ድረስ ማንንም አንናገርም
ይቀበላሉ ብለንም አናስብም፡፡ በሀገሪቱ
ሕግ ሰጪም ተቀባይም ወንጀለኛ ናቸው፡
፡ ስለዚህ የወንጀሉ መነሻ ክለቦች ናቸው
ማለት ነው እነርሱም እጃቸውን ይሰብሰቡ፡፡
ሀትሪክ፡- ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ
ዳኞችን ከመደበ በኋላኮ የሚቀይረው
በመሞዳሞድ የታሙትን ነው… ይሄንንስ
እንዴት አየኸው?
ትግል፡- ዳኞች የመቀየራቸው ነገር
ከመታማት ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ አምና
ቡናና ጊዮርጊስ እንዲያጫውት በአምላክ
ተመድቦ ተቀየረ፡፡ ከላይ ባልከው ተራ ጉዳይ
ላይም አይገባም፡፡ ዘንድሮም ተቀይሯል፡፡
ሁሉም በሙስና ሳይሆን ከክለቦች አካባቢ

ግፊት ሲመጣ ኮሚቴው አስተናግዶ ካልሆነ
በቀር በሙስና የተቀየረ የለም፡፡
ሀትሪክ፡- ማህበራችሁ ኮሚቴው
ዳኞችን በተገቢው መንገድ ተንከባክብቧል
ብለህ ታምናለህ?
ትግል፡- አዎ! ዳኞች ሲቀየሩ ለምን
ብለን ጠይቀን አጥጋቢ ምላሽ አግኝተናል፡
፡ አሳምነውናል፡፡ እንድጫወት ተመድቤ
ስቀየር እንደማንኛውም ሰው ቅር ይለኛል፡
፡ ግን አሳማኝ ምላሽ ይሰጣል ከዚህ አኳያ
እንክብካቤው በተገቢ መንገድ አለ ብለን
እናምናለን፡፡
ሀትሪክ፡- ኢንሹራንስ አላችሁ ይባላል…
እውነት አለ?
ትግል፡- ተረቱ ጠፋብኝ እንጂ መጥፎ
አጋጣሚዎች ለጥሩ ነገር መነሻ ይሆናሉ
ይባላል፡፡ አጓጉል ነገሮች ሲመጡ ዝም
አይባልም ኢንሹራንስ፣ ትራንስፖርት፣…
የተባለው በኖርማል ጊዜ ቢሆን የተጠየቀው
ትኩረት አይሰጠውም ነበር፡፡ እስካሁን ግን
ችለን መኖራችንን ፌዴሬሽኑ ያውቃል ነገር
ግን መጥፎው ገጠመኙ ይህንን አስከተለ
ካሁን በኋላ አናጫውትም ስንል እንደራደር
የሚል ሃሳብ መጣ፡፡ ለዚህ ነው መጥፎ
አጋጣሚዎች ለጥሩ ነገር መነሻ ይሆናል
ያልኩህ፡፡
ሀትሪክ፡- ያላችሁት ነገር እስከ ግንቦት
20 ባይሟላ በአቋማችሁ ትፀናላችሁ…
ከኮማንድ ፖስቱ ጋር አያጋጫችሁም?
ትግል፡- በፍፁም አያገናኘውም፡፡
ዓላማውም ሆነ ያቀረብነው ነፃ ጥያቄ ነው፡
፡ በውስጡ ሌላ አጀንዳ የለንም ያቀረብነው
ጥያቄ ይመለስ የሚል አቋም ነው የያዝነው፡
፡ ይሄ ደግሞ ተገቢ ነው ያቀረብነውን ጥያቄ
በተመለከተ ለህዝቡ መጠይቅ ቢቀርብ 95
በመቶ ድጋፍ እናገኛለን፡፡ ከሌላ ነገር ጋር
አልተያያዘምኮ፡፡
ሀትሪክ፡- 50 በመቶው ቢፈፀምስ… ወደ
ውድድር ትመለሳላችሁ?
ትግል፡-10ሩ አቋሞቹኮ የጠቅላላ ጉባኤው
ነው፡፡ እነርሱ ካሉ ይቆማል ካላሉ ይቀጥላል፡፡
ለድርድር ከፈለጉ ጉባኤው የሚወስነው ይሆናል
ለዚህ ደግሞ ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተናል ያኔ
የሚወስን ይሆናል፡፡ ይሄ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡
ሀትሪክ፡- ኢንተርናሽናል ጨዋታ እንዳታ
ጫውቱ ፌዴሬሽኑ እገዳ ቢጥልስ?
ትግል፡- ውድድሩኮ ሁሉም ነገር ተሟልቶ
የሚደረግ ነው ስለዚህ የምንቀርበት ምክንያት
የለም፡፡ አንተ እንዳልከው ግን ፌዴሬሽኑ
ከኢንተርናሽናል ውድድር ካገደን ከኛ በላይ
ያመፀው እራሱ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ የሚከለክለኝ
ከተቀጣሁ ብቻ ነው ይህን ተራ ውሳኔ ፌዴሬሽኑ
ይወስናል ብዬ አላምንም ከመጣ ደግሞ በኋላ ላይ
እናየዋለን፡፡
ሀትሪክ፡- ከውሳኔያችሁ በኋላ ሊያጫውቱ
ወደ ተለያዩ ስታዲየሞች የሄዱ ዳኞች አሉኮ…
ይሄ ከናንተ አቋም እንደወጡ አያሳይም?
ትግል፡- ዳኞቻችን ከኛ ጎን እንደሚቆሙ 100
በመቶ እርግጠኛ ነን፡፡ ምናልባት ወረቀቱን ስንበትን
ዘግየት ብለናል፡፡ ለጨዋታው ዳኞቹ ከቤታቸው
ከተንቀሳቀሱ በኋላ ነው የሰሙት፡፡ ሃሳባችንን
ቢቃወሙ ኖሮ ያጫወቱ ነበር፡፡ ስላልሰማን ነው
ብለው ባለፈው አርብ ወደየመጡበት ተመልሰዋል፡

ሀትሪክ፡- ከፌዴሬሽኑ አካባቢ ዳኞችን
የመለየት ተንኮል ተሰርቶ ነበር የሚባል ነገር
ሰምቻለሁ…. መረጃው አላችሁ?
ትግል፡- አንዳንድ ዳኞችን ትቀጣላችሁ ወደ
ስራችሁ ተመለሱ ብለው አቶ ጁነዲን እንዳስፈራሩ
ሰምተናል፡፡ ዳኞችን የመለያየት ስራ ተሰራቷል፡
፡ በኛ በኩል ግን አንድም ዳኛ ሆነ ኮሚሽነር
እንደማይጠየቅ አንድ ነገር ቢፈጠር ማህበሩ ከዚህ
በላይ እንደሚጓዝና ፌዴሬሽኑ እንደሚታገሉ
ነግረናቸው ተስማምተናል፡፡ በዚህ በኩል ስጋት
የለብንም፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...