መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ የፕሪሜየር ሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ በድል ጀምሯል
መቐለ ከተማሪፖርትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግድሬዳዋ ከተማ

መቐለ 70 እንደርታ የፕሪሜየር ሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ በድል ጀምሯል

አጋራ
አጋራ

በትግራይ ኢንተርናሽናል ስታድየም የተካሄደው የመቐለ 70 እንደርታና የደደቢት ጨዋታ በምዓም እምበሳዎቹ ሁለት ለዜሮ ኣሸናፊነት ተጠናቋል።የዋልያዎቹ ኣሰልጣኝ ኢንስትራክተር ኣብርሃም መብራህቱ በተገኙበት ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች የክረምት ፈራሚዎቻቸውን ወደ ሜዳ ይዘው ገብተዋል ።

መቐለዎች በክረምቱ ካስፈረምዋቸው 12 አዳዲስ ተጨዋቾች አሚን ነስሩ፣ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ሳሙኤል ሳሊሶ፣ዮናስ ገረመው፣ሻይቡ ጅብሪል ና ሃይረዲን ሸረፋን ቋሚ ኣስራ እንድ ውስጥ ይዘው ሲገቡ ደደቢቶች በበኩላቸው አንዳለ ከበደ፣እብዱልአዚዝ ዳውድ፣ኩማ ደምሴ ና ኤፍሬም ጌታቸውን ተጠቅመዋል።

መቐለ 70 እንደርታዎች በላይ ሆነው በታዩበት የመጀመርያው ኣጋማሽ በኤፍሬም ጌታቸውና እንዶህ ኩዌክ ሚመራውን የደደቢት ተከላካይ መስመር ለመስበር ሥስት ደቂቃዎች ወስዶባቸዋል፤ ከግራ መስመር በረጅሙ የተላከው ኳስ ፊት አጥቂ ላይ የተሰለፈው አማኑኤል ኳሱን በሚገባ በመቆጣጠር ግብ ጠባቂውን በማለፍ በቀጥታ ለዮናስ ገረመው ኣቀብሎት ዮናስ በቀላሉ ሊያስቆጥረው ችሏል።ከመቐለ ጋር በተመሳሳይ 4-2-3-1 ኣሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት ደደቢቶች በራሳቸው ሜዳ ላይ በሚቀባበሉዋቸው ኳሶች በቀላሉ በመቐለ የመሃል ተጨዋቾች ሲነጠቁ ነበር የዚህም ማሳያ ደደቢቶች በ22 ደቂቃ በቀኝ መስመር ተመላላሹ አብዱልአዚዝ ዳውድ አማካኝነት ካካሄዱት ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ውጭ ይህ ነው ሚባል ሙከራ ማድረግ ኣልቻሉም።

ከመጀመርያው ኣጋማሽ ጋር በተመሳሳይ የመቐለ 70 እንደርታ በላይነት በቀጠለበት ሁለተኛው ኣጋማሽ፤መቐለዎች ከመሃል ሜዳ ከሚኪኤለ ደስታና ሃይደር ሸረፋ በሚላኩ ኳሶች የግብ እድልን ለመፍጠር ሲሞክሩ ታይቷል።የዚህ ኣጨዋወት ውጤትም መሃል ላይ በእስር ቁጥር ሚና የተሰለፈው ሃይደር ሸረፋ ያሾለከውን ኳስ ፍጹም ቅጣት ሳጥን ውስጥ በቀኝ መስመር የተሰለፈው ሳሙኤል ሳሊሶ በሚገባ በመጠቀም የመቐለ 70 እንደርታ ግብን ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ ችሏል።ደደቢቶች ሥስት የተጨዋች ቅያሪ በማድረግ የተሻለ ከመጀመርያው ኣጋማሽ የተሻለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም የመቐለን ተከላካይ ክፍልን ሚረብሽ እንቅስቃሴ ማድረግ ኣልቻሉም።

በዚህም መሰረት መቐለ 70 እንደርታ በመጀመርያው ና በሁለተኛ ኣጋማሽ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ታግዞ ደደቢትን በማሸነፍ ሙሉ ሥስት ነጥቦችን ማሳካት ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...