መቐለ 70 እንደርታ የሶስት ተጨዋቾቹን ውል አራዝሟል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን በ2011 ላይ ያነሳው የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌው መቐለ 70 እንደርታ የሶስት ተጨዋቾቹን ውል ማለትም በሊጉ የተካበተ የመጫወት ልምድ ያለውን የስዩም ተስፋዬን እንደዚሁም ደግሞ ከቅርብ ዓመታቶች ወዲህ ከጨዋታ ወደ ጨዋታሲያመራ ከፍተኛ መሻሻል ያሳየውን የዮናስ ገረመውን /አላባ/ እና የወጣቱ ተጨዋች የአሚን ነስሩን ውል ለአንድ ዓመት አራዝሟል።

መቐለ 70 እንደርታ የሶስቱ ተጨዋቾችን ውል ለማራዘም የቻለው
በክለቡ የፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ቆይታቸው ጥሩ ግልጋሎትን ከመስጠት ባሻገር ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ ባነሳበት ሰዓትም ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማሰብ እንደሆነም ታውቋል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team