ባህር ዳር ከተማዎች የኮከብ ተጫዋቻቸውን ውል ማራዘማቸውን ለማወቅ ተችሏል ።
ፍፁም ዓለሙ በጣና ሞገዶቹ ቤት ለቀጣይ ዓመታት ለመቆየት ከስምምነት እንደ ደረሰ ይፋ ሆኗል ።
ፍፁም ዓለሙ ከፋሲል ከነማ የጣና ሞገዶቹን ከተቀላቀለ በኋላ አስደናቂ ብቃቱን ሲያሳይ ሲቆይም በተለይም ለቡድኑ ውጤት ቁልፍ ሚናን ሲጫወት ማሳለፉ ይታወሳል ።
- ማሰታውቂያ -
በተለይም ከሊጉ ጅማሮ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጎልቶ መውጣት ሲቻል የጨዋታ ኮከብ በመባል መመረጡ የሚታወስ ነው ።
በተለይም ከሳምንታት በፊት መቐለ 70 እንደርታን መቀላቀሉ ቢገለፅም በመጨረሻ ሰዓት ዝውውሩ እንከን እንደገጠመው እና ሊሳካ አለመቻሉ ለማወቅ ተችሏል ።