መቐለ 70 እንደርታ ምንይሉ ወንድሙን ለአንድ ዓመት ውል አስፈረመ

የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ከተተኪው አንስቶ እስከዋናው
ቡድን ድረስ በስኬታማ ተጨዋችነቱ ያገለገለውና በአንድ ወቅት
በደረሰበት ጉዳት ደግሞ ከሜዳ ርቆ የነበረውና በአሁን ሰዓት ላይም
ወደ መልካም ጤንነቱ በመመለስ እና የቀድሞ ድንቅ ብቃቱን ዳግም
ለማሳየት ዝግጁ የሆነው ምንይህሉ ወንድሙ በከፍተኛ ሊግ ላይ
የሚጫወተውን መከላከያ ክለብ በመልቀቅ ለአንድ ዓመት ለሚደርስ
የውል ጊዜ አዲሱ ክለቡን መቀለ 70 እንደርታን ሊቀላቀል ችሏል።
የመከላከያ እግር ኳስ ክለብን ከትውልድ ክልሉ ጅማ ከተማ
ከመጣበት ጊዜ አንስቶ ክለቡን እስከለቀቀበት ድረስ   በታማኝነት አገልግሏል

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website