“መቐለ 70 እንደርታን ጠንካራ ያደረጉት ኳስን በእውቀት የሚደግፉት ደጋፊዎቻችን ናቸው”ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ /መቐለ 70 እንደርታ/ (ክፍል-2)

ሙሉጌታ፡- አዎ… አሰልጣኙ እድል ሰጥቶኝ ጥሩ ግልጋሎት እየሰጠሁ ነው…የምታገለውም ይህን ለማስቀጠል ነው…. የሚሳካልኝ ይመስለኛል፡፡ ክለቤን በመሀል ስፍራ መጥቀሜን
እቀጥላለው በማጥቃት ጨዋታ ላይ ስገኝ ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን አሰልጣኜ በሚሰጠኝ ቦታ ላይ ለመሰለፍ ደግሞ ዝግጁ ነኝ… በ1ኛ ዙር ወደ 11 የሚጠጉ ጨዋታዎች ላይ ክለቤን በመሀል ቦታ
በደንብ ጠቅሜያለው ብዬ አምናለው፡፡

ሀትሪክ፡- ከኳስ ውጪ የሚያዝናናህ ምንድነው?

ሙሉጌታ፡- መዝናኛዬም ስራዬም ኳስ ነው… ከዚያ ውጪ የውጪ ተከታታይ ፊልሞችን ማየት ደስ ይለኛል፡፡ በተለይ ሹተር (Shooter) የተሰኘው ተከታታይ ፊልም አስደስቶኝ
እየተዝናናሁበት እገኛለው….. ከዚያ ውጭ ሌሎች የስለላ ፊልሞችም ያዝናኙኛል፡፡

ሀትሪክ፡- እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለሀገርህ ምን ትመኛለህ?

ሙሉጌታ፡- እድገት ፍቅርና ሠላም ለምወዳት ሀገሬ እመኛለው… ዋናው ግን ሠላም ነው… ሠላም ከሌለ ምንም ማድረግ አይቻልምና ሁሉም ሠላም ላይ ቢያተኩር ደስ ይለኛል፡፡ በሀገር
ደረጃ ማየት የማልፈልገው መጥፎ አስተሳሰብ ቢወገድ ደስ ይለኛል፡፡ ሰው ለሰው የሚያስብ ቢሆን ራሱን ብቻ ባይወድ ደስ ይለኛል፡፡ ከምንም በላይ ዘረኝነት ከኢትዮጵያ ላይ ጠፍቶ ማየት
እመኛለሁ፡፡ 16ቱ ክለቦችን ስታይ ከመላው የሀገሪቱ ከተሞች የተሰባሰቡ ናቸው፡፡ ዝም ብለህ ስብጥሩን ስታየው ኢትዮጵያዊ ህብረት ይታያል፡፡ ክለቦቻችን ውስጥ የሚታየው ኢትዮጵያዊነት
ሰፍቶ ዘረኝነት ከምድሪቱ ተወግዶ ማየት እመኛለው፡፡

ሀትሪክ፡-የመጨረሻ ጥያቄ… የምታመሰ ግነው ካለ እድሉን ልስጥህ?

ሙሉጌታ፡- በመጀመሪያ በጤናና በሠላም እዚህ ያደረሰኝ አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን…… ከዚያ ውጪ ቤተሰቦቼ፣ ክለቤ መቀለ 70 እንደርታ፣ ደጋፊዎቻችንን፣ አመራሮቹን፣ በኳስ
ተጨዋችነት ደረጃ ላመነብኝና እድሉን ለሰጠኝ አሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌ፣ ለጓደኞቼ በአጠቃላይ በኔ ጉዳይ ላይ መልካም አስተዋፅኦ ላደረጉ በሙሉ በእግዚአብሔር ስም ማመስገን
እፈልጋለው፡፡

ሀትሪክ፡-በ8 አመት የኳስ ተጨዋችነት ቆይታህ ስለአንተ መረጃ ሳሰባስብ በሚዲያ ደረጃ የሰጠኸው ቃለ ምልልስ አጣሁ ሀትሪክ የመጀመሪያ ናት ልበል?
ሙሉጌታ፡- /ሳቅ በሳቅ/ አዎ በጣም እፈራለው ገና ነኝ ብዬ አስብ ስለነበር ቃለ ምልልስ ማድረግ አይመቸኝም በታሪክ አጋጣሚ ሀትሪክ ለዚህ ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ በመሆኗ
ማመስገን እፈልጋው፡፡
ሀትሪክ፡- አመሰግናለው.. ሙሌ መልካም የጨዋታ ጊዜ እንመኛለን፡፡

የመጀመሪያውን ክፍል ለማግኘት ምስሉን  ይጫኑ 👇

 

https://www.hatricksport.net/መቐለ-70-እንደርታን-ጠንካራ-ያደረጉት-ኳስ/

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport