መነሻ ገጽ ዜናዎች ለከፍተኛ ሊግ አሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ለከፍተኛ ሊግ አሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

አጋራ
አጋራ

 

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣እንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር አማካኝነት ተዘጋጅቶ ለከፍተኛ ሊግ ክለቦች አሰልጣኞች ከሰኞ ጥር 18/2012ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዛሬው እለት ጥር 22/2012ዓ.ም ተጠናቀቀ።

ስልጠናው ከእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር በመጡ አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናው በክፍል ውስጥ የንድፈ ሀሳብ ትምህርት እና በሜዳ ተግባራት የታገዘ ነበር፡፡
በስልጠናው ወቅት የብሪቲሽ ኢምባሲ አምባሳደር በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት የስልጠናውን ሂደት በመከታተል ሰልጣኞችን አበረታተዋል።

እንዲሁም በትናንትናው እለት ጥር 21/2012ዓ.ም አምባሳደሩ ሰልጣኞችን ብሎም ሌሎች እንግዶችን በኢንባሲያቸው በመጥራት የኮክቴል ግብዣ በማድረግ ስልጠናው ቀን ከመጠናቀቁ አስቀድሞ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ለሰልጣኞች ሰተዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአምባሳደሩ ያዘጋጀውን የብሄራዊ ቡድን ማለያ በስጦታ መልክ የኢ.እ.ፌ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የህክምና ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ በማበርከት መሰል የስልጠና ግንኙነቶች መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸው ስልጠናውን ለሰጡት አሰልጣኞች እና ለእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

ሰልጣኞቹም ለአሰልጣኝ መምህሮቻቸው የኢትዮጵያ ባህላዊ አልባሳትን በስጦታ ያበረከቱ ሲሆን፤ አሰልጣኞቹም ከእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የማህበሩ አርማ የታተመበትን ኳስ በስጦታ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አበርክተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...