የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከብራዚል ኤምባሲ አምባሳደር ሉዊስ ኤድዋርዶ ደ አጉኤር ቪላሪኒሆ ጋር በእግር ኳስ ልማት ላይ በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ዙሪያ ትላንት ጥር 21/2012 ተወያዩ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ ብራዚል እግር ኳስ ማህበር ጋር በጋራ መስራት በሚችሉበት እንዲሁም በብራዚል የሚገኙ ትልልቅ ክለቦች በኢትዮጵያ የእግር ኳስ አካዳሚ በሚከፍቱበት እና ኢትዮጵያዊያን የእግር ኳስ አሰልጣኞች ከብራዚል አሰልጣኞች ልምድ በሚወስዱበት እና ተጨማሪ የአሰልጣኝነት ስልጠናዎችን በሚያገኙበት ሀሳቦች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፤ የብራዚል የእግር ኳስ ልማት ስትራቴጂ ምን እንደሚመስል እና ልምድ በሚገኝበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
የፍላሚንጎ እግር ኳስ ክለብ ቀደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የገለጹት የብራዚል ኤምባሲ አምባሳደር ሉዊስ ኤድዋርዶ ደ አጉኤር ቪላሪኒሆ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በፓርላማ ባአንድ ወቅት ያደረጉት ንግግርን በጋዜጣ ባነበቡት ጊዜ ኢትዮጵያን በምን መልኩ ማገዝ እንዳለባቸው ሲያስቡ መቆየታቸውን ለኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ገለጸውላቸዋል።
በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ የጋራ እቅድ እንዲዘጋጅ እና የማቴሪያልም ሆነ የስልጠና እገዛ በሚደረግበት ዙሪያ ወደፊት እንደሚማከሩ ገልጸው ውይይታቸው ተጠናቋል።
አስተያየት ይስጡ