ሀትሪክ 13ኛ ሳምንት ዕይታ ( የተቆጠሩ ግቦች እና የተመዘገቡ ውጤቶች)

 

በ13ኛ ሳምንት የተመለከትናቸውን ዋና ነጥቦች አንስተናል።

የተቆጠሩ ግቦች

የ13ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዳሜ ጅማሮውን አድርጎ ዛሬ ጨዋታዎች ፍፃሜያቸውን ሲያገኙ። በዚህ ሳምንት በጠቅላላ 23 ግቦች ተቆጥረዋል ይህ ማለት ደግሞ ባለፈው ሳምንት ከተቆጠሩ ግቦች በ1 ዝቅ ብሏል። 19 ተጫዋቾች ግብ ሲያስቆጥሩ 15ቱ ግቦች በተለያዩ ተጫዋቾች የተቆጠረ ሲሆን ሙጂብ ቃሲም፣አቤል ያለው፣ጌታነህ ከበደ፣ስንታየሁ መንግስቱ ሁለት ሁለት ግቦችን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። አቤል ያለው 2ኛ እና 90ኛ ደቂቃ ያስቆጠራቸው ግቦች በሳምንቱ በፍጥነት ብሎም ዘግይቶ ያስቆጠራቸው ግቦች ናቸው። አራት ግቦች በፍፁም ቅጣት ምት የተቆጠሩ ሲሆን። በዚህ ሳምንት የተቆጠሩ ሁሉም ግቦች ደግሞ በኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ብቻ የተቆጠሩ ናቸው። ደጉ ደበበ ከረጅም ግዜ በኋላ ሀድያ ላይ ግብ አስቆጥሮ ድቻ ሙሉ ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሏል። ሙጂብ ቃሲም አሁንም የኮከብ ግብ አግቢነቱን ያጠናከረበትን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል።

የተመዘገቡ ውጤቶች

ሀትሪክ 13ኛ ሳምንት ዕይታ ( የተቆጠሩ ግቦች እና የተመዘገቡ ውጤቶች)

በዚህ ሳምንት ከተደረጉጨዋታዎች ስድስቱም በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ ። ሁለቱም በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። በዚህ ሳምንት ሶስት ቡድኖች ብቻ ግብ ሳያስቆጥሩ ሲወጡ። ፈሲል ከተማ።፣ወላይታ ድቻ፣ ሀዋሳ ከተማ ግብ ሳይቆጠርባቸው የወጡ ናቸው። በዚህ ሳምንት በሶስት ጨዋታዎች አምስ ግቦች በጠቅላላ ተቆጥረዋል። ወልቂጤ ከተማ ትላንት ነጥብ ቢጋራም አሁንም በተከታታይ አራት ጨዋታዎች ሽንፈት ያላስተናገደ ቡድን ሆኗል። ኢትዮጵያ ቡና።፣ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ድሬዳዋ ከተማ አሁንም ሶስት ነጥብ ለማግኘት ከባድ ሆኖባቸዋል። ወላይታ ድቻ ተከታታይ ሁለኛ ማስመዝገብ ሲችል። ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁንም አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ በአልሸነፍ ባይነቱ ቀጥሏል። ፋሲል ከተማ በዚህ አመት ለመጀመሪያ ግዜ መቐለ 70 እንደርታን ከሜዳው ውጭ ማሸነፍ ችሏል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor