አጋራ

👉👉 ጎሎች

👉👉 ውጤቶች

👉👉ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ

👉👉 የአሸናፊነት ጉዞው የተገታው መቀለ 70 እንደርታ

👉👉 ወደ ድል የተመለሱት አዳማ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ

👉👉 ወድ ግብ የተመለሰው ሙጂብ ቃሲም

👉👉 ጉዳት በተደጋጋሚ እያስተናገደ ያለው ወጣቱ ተጫዋች

👉👉 የሊጉን ፈጣኗ ቀይ ካርድ ያስተናገደው የባህርዳር ግብ ጠባቂ

👉👉 ለፌደሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ ያስገባው የመጀመሪያው ክለብ


10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትላንት በተደረጉ አምስት ጨዋታዎች ፍፃሚያቸውን ሲያገኙ። በዚህ ሳምንት የተመለከትናቸው ዓበይት ጉዳዮች እንደሚከተለው ለናንተ በሚመች መልኩ አቅርበንላችኋል።

ጎሎች

በዚህ ሳምንት በጠቅላላ 13 ግቦች ተቆጥረዋል ይህም ባለፈው ሳምንት ከተቆጠሩ ግቦች መሀከ በ13 ዝቅ ብሏል። 13ቱ ግቦች ደግሞ በተለያዩ 13 ተጫዋቾች ነው የተቆጠሩት። ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ሙጂብ ቃሲም ሲዳማ ቡና ላይ በ 10ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የዚህ ሳምንት ፈጣኗ ግብ ስትሆን። ፈአድ ፈረጃ ሀድያ ሆሳዕና ላይ በ90ኛው ደቂቃ ያገባት ግብ ደግሞ በዚህ ሳምንት ዘግይታ የተቆጠረች ነበረች።

ውጤቶች

ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ። ሌሎች ቀሪውቹ ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተቋጭተዋል። ከምስት ቡድኖች ደግሞ በተቃራኒ ቡድን ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል።

 

ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ

በ 8ኛው ሳምንት በሜዳቸው በስሁል ሽረ የ2-0 ሽንፈት ከቀመሱ በኋላ። ከአሰልጣኛቸው ጋር የተለያዩት የጦና ንቦች በምክትል አሰልጣኛቸው ሳሙኤል ደቻሳ እየተመሩ ዛሬ የሊጉን መሪ መቐለ 70 እንደርታ በማሸነፍ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አሳክቷል።

 

የአሸናፊነት ጉዞው የተገታው መቀለ 70 እንደርታ

የሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ከተከታታይ ድሎ በኋላ በወላይታ ድቻ ጉዞው ተገቷል። መቐለም ካለፉት ጨዋታዎች ግብ ሳያስቆጥር የወጣበት ሳምንት ሆኗል።

 

ወደ ድል የተመለሱት አዳማ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ

ካልተፈታው እንቆቅልሹ ጋር ለብዙ ሳምንታት ከድል ርቆ የነበረው አዳማ ከተማ አሁንም ከነችግሮቹ ሀድያ ሆሳዕናን 2-0 በማሸነፍ የድል ጉዞውን
ጀምሯል። ሌላኛው ተመሳሳይ የውጤት እጦት ውስጥ የነበረው በአሰልጣኝ ደግአረግ የሚመራው ወልቂጤ ከተማ በሳዲቅ ሴቾ ብቸኛ ግብ ከተከታታይ ነጠብ መጣል ወድ ድል መመለስ ችለዋል።

 

ወድ ግብ የተመለሰው ሙጂብ ቃሲም

ለፋሲል ከተማ ግቦች በማስቆጠር እና ክለቡ ከጨዋታዎች ነጥብ ይዞ እንዲወጣ እያደረገ ያለው አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ባለፈው ወድ መቐለ አቅንተው ስሑል ሽረን በገጠሙበት ጨዋታ ግብ ሳያስቆጥር የወጣበት ጨዋታ ሆኖ ማለፉ አይዘነጋም። ዛሬ ሲዳማ ቡና ላይ ያስቆጠራት ግብ ክለቡ ነጥብ ይዞ ለመውጣት አስተዋፅኦ ከማድረጓም በላይ። ለግሉ ወደ ግብ አስቆጣሪነት መንገድ የተመለሰበት እና በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ከተከታዮቹ የራቀበት ነበር። ሙጂብ በ10 ግቦች ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።

ጉዳት በተደጋጋሚ እያስተናገደ ያለው ወጣቱ ተጫዋች

በተደጋጋሚ ጉዳቶችን እያስተናገደ የሚገኘው የሀዋሳ ከተማው ወጣት አጥቂ መስፍን ታፈሰ ከጉዳቱ አገግሞ በሰበታው ጨዋታ ተሰለፎ መጫወት ቢችልም በጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ አግሩ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ በአምቡላንስ ለተጨማሪ እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። የጉዳቱ መጠን ምን ያክል እንደሆነና ለስንት ግዚያት ከሜዳ እንደሚያርቀው የታወቀ ነገር የለም።

የሊጉን ፈጣኗ ቀይ ካርድ ያስተናገደው የባህርዳር ግብ ጠባቂ

ባህርዲር ከተማ በ10ኛ ሳምንት ጨዋት ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ገጥሞ 1-0 መሸነፉ ይታወሳል። ታዲያ ከጨዋታ ጅማሮ አስቀድሞ በሊጉ እንግዳ የሆነ ነገር ተከስቷል። የባህርዳሩ ግብ ጠባቂ ሀሪትሰን ሄሱ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ቢካተትም አሟምቀው ወደ መልበሻ ክፍል ካመሩ በኋላ ወደ ጨዋታ ለመግባት ዝግድት በሚያደርጉበት ወቅት የእለቱ ዳኛ ቴዎድርስ ምትኩ በውስጥ የለበሰውን ማሊያ እንዲያወጣ ቢነግሩትም እሰጣ ገባ ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ከጨዋታ ጅማሮ በፊት የቀይ ካርድ ሰላባ ሆኗል። በህጉ መሰረትም በምትኩ ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ እሱን ተክቶ በመግባት ወደ ቋሚ አሰላለፍ ተካቷል።

ለፌደሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ ያስገባው
የመጀመሪያው ክለብ

ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ በ9ኛው ሳምንት ጨዋታ ባህርዳርን ገጥሞ 3-2 በሆነ ውጤት መሸነፉ አይዘነጋም። ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ በዳኝነት እና በስፖርታዊ ጭዋነት በደል ደርሶበኛል ሲል በዚህ አመት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የቅሬታ ደብዳቤ ከላኩ ከለቦች መካከል ቀዳሚው ሆኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...