ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

*……መደሰቻ አጥቶ ለነበረው ህዝብ የደስታ
ምንጭ በመሆናችን ክብር ይሰማናል የሚለው የፋሲል ከነማው ታጋይ ሽመክት ጉግሳ “ባለፉት 2 አመታት የሊጉን ዋንጫ ባንወስድም ትልቅ ነበርን ዘንድሮ ግን ዋንጫውን በመውሰድ ትልቅነታችንን እናሳያለን” ሲል ዝቷል።

*…የኢትዮጵያ ቡናን በእምበልነት እየመራ ያለው ኢያሱ ታምሩ ደግሞ ” ፕሪሚየር ሊጉ አልተጠናቀቀም ተስፋ አንቆርጥም” ብሏል….”ደጋፊዎቹን ባበረታታበት ምላሹ በአፍሪካ መድረክ ጠብቁን”ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

*…የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛውና የብሄራዊ ቡድኑ አምበል የነበረችው የረሂማ ዘርጋ እንካ ሰላንቲያ ዛሬም ቀጥሏል…
አሰልጣኝ ብርሃኑ” ከብሄራዊ ቡድኑ ውጪ ያደረኳት ጉዳት ስላለባትና ጫና ላለመፍጠር ነው” ቢልም ከአምበሉ ቀጥተኛ ተቃውሞ ቀርቦበታል …” ምንም ጉዳት የለብኝም የኢትዮጵያ ህዝብን ለማታለል ነው”ስትል በነገር ሸንቆጥ አድርጋዋለች።

ከውጪ ዘገባዎቻችን:-

*…. ቅዳሜ ምሽት ስለሚደረገውና አጓጊ ስለሆነው ተጠባቂው የኤልክላሲኮ የምንላችሁ አለ….

*….ሽንፈትን አምርሮ የሚጠላው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ….. የኦሌጉናር ሶልሻየርን ማን.ዩናይትድን ለዩሮፓ ሊግ ክብር ለማብቃት እየተጋ ስለመሆኑ የሚገልጽ ዘገባም ይዘናል…

*…የቸልሲው አለቃ ቶማስ ቱሄል ስኬታማ ስለሆነው የሻምፒየንስ ጉዟቸው የሚሉትን ሁሉ አካተናል…

*….ቅሬታ ውስጥ ያለው የመድፈኞቹ አለቃ ሚካኤል አርቴታ “ትልልቅ እድሎችን መጠቀም የማትችል ከሆነ ዋጋ መክፈልህ አይቀርም” በማለት በአርሰናል ተጨዋቾች አቋም ደስተኛ አለመሆኑን የሚገልጽ አስተያየት ሰጥቷል።

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

https://www.Hatricksport.net

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team