ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያገኛሉ
*…..የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ “መላው ኢትዮዺያዊያንን በአንድነት የሚያስተሳስር ድል በመመዝገቡ ተደስቻለሁ” ሲል ከ4 ለ 0 የዋሊያዎቹ ድል በኋላ ለሀትሪክ ተናግሯል።
*… ኮከቡ አጥቂ አቡበከር ናስር ድል ድል ይሸተኛል እያለ ነው… “በአቢጃን አዲስ ታሪክ እናጽፋለን የኮትዲቯር ተጨዋቾች መጎዳት ለኛ ጥቅም የለውም ሁሉም ባሉበት አሸንፈን ነው ማለፍ የምንፈልገው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል
*…ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እሁድ በስካይ ላይት ሆቴል ትሞገሳለች…. ኮማንደር ደራርቱ ቱሉና ዶክተር አሸብር
ወ/ጊዮርጊስ የሚመሯቸው አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሎምፒክ ኮሚቴ መሃል ያለው ልዩነት ጦዟል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲስ አበባ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሀዋሳ ላይ ድግስ ደግሰዋል…ማን ያሸንፍ ይሆን?
*…የፈረሰኞቹ ተተኪ አማኑኤል ተርፉ
” ብዙ ለፍተናል ነገር ግን እንደ ቡድን ጥሩ ባለመሆናችን ውጤት አጥተናል”በማለት ለሀትሪክ ገልጿል።
ወደ ውጪ ዘገባዎቻችን ስንዞር:-
*…..የማን.ዩናይትድ የየካቲት ወር ኮከብ ሉክ ሾው “የዩሮፓ ሊግን ዋንጫ ማሳካት እፈልጋለሁ”ሲል የዘንድሮውን ህልሙን ተናግሯል።
*…..የመድፈኞቹን የፈጠራ ችግር ስለ ቀረፈው ኦዲጋርድ የምንለው አለ….
*……ፖርቱጋልስ ያለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ይሳካላት ይሆን? በሚል ጥያቄ የተዘጋጀ ዘገባንም ይዘናል….. እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል.....
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……