ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን በተለያዩ ክለቦች ማሊያ ቢታይም በኢትዮዽያ ቡና ማሊያ የሚታወቀውና ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ጋቶች ፓኖም እንግዳችን ነው… በርካታ ጉዳዮችን ከይስሃቅ በላይ ጋር ያወጋው የጋምቤላው ጥቁር ወርቅ ጋቶች “ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጣሁት አዲስ ታሪክ የማጻፍ ትልቅ ህልም ሰንቄ ነው”ሲል ተናግሯል…

*…..ከኢትዮዽያ ቡና ጋር ሊለያይ ነው ተብሎ ደጋፊዎቹን ለሁለት የከፈለው አስራት ቱንጆ “በምርጡ ኢትዮዽያ ቡና ስር ሆኖ ዋንጫ አለማንሳት በጣም ይቆጫል ከዚህ ቡድን ጋር ሻምፒዮን መሆን ትልቁ ምኞቴ ነው” ብሏል።

*… በውዝግብ በታመሰውና አለመግባባቱ የተፋፋመበት አዲስ አበባ ተጀምሮ ቶኪዮ የደረሰው የኢትዮዽያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዙሪያ እየጋመ በመጣው እሳት ላይ ውሃ የቸለሰ ሁሉን አንድ ያደረገ የድል ብስራት በ10 ሺህ ሜትር ቶኪዮ ላይ ተከስቷል። አትሌት ሰለሞን ባረጋ ባስመዘገበው የኦሎምፒክ ድልና ሌሎች የአትሌቲክስ ዜናዎችን ይዘናል….

*……. አቤል እንዳለና ነስረዲን ሃይሉ ኢትዮዽያ ቡናን ተቀላቅለዋል ከሌሎች ክለቦች የተሻለ ገንዘብ ቀርቦላቸው ኢትዮዽያ ቡናን እንዴት መረጡ? ለሚለው ምላሹን ይዘናል….

*….የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ የ2014 እጣ ማውጣት ስነስርአት ሰኞ ይካሄዳል…ይሄ በሀገሪቱ እግርኳስ ላይ ባልታየው ክስተት ዙሪያ የተዘጋጀ ዘገባን አካተናል…

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*….. ” በኤሲሚላን ታሪክ ሰርቼ ማለፍ እፈልጋለሁ” ሲል የሮሲየነሮቹ አዲሱ ፈራሚ ኦሊቪዬ ዢሩ ተናግሯል…

*….የሊቨርፑሉ ዲያጎ ዦታ ” ለአዲሱ የውድድር ዘመን ፈተና ተዘጋጅቻለሁ” ሲል ፎክሯል..

*…..” አዲሱ የማን.ዩናይትድ ፈራሚ ጄደን ሳንቾ “የዚህን ታላቅ ክለብ መለያ መልበስ በመቻሌ ኩራት ተሰምቶኛል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

*…ኢሚል ስሚዝ ሮው በመድፈኞቹ ቤት የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል…” በአርሰናል 10 ቁጥር ማሊያ ትልቅ ቦታ አለው ስለዚህም ለተጨማሪ ፈተና መዘጋጀት አለብኝ” ብሏል ማሊያውን ከተረከበ በኋላ….

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team