መነሻ ገጽ ottawa marathon ሀትሪክ በይፋ የተጋበዘችበት የኦቷዋ ማራቶን የፊታችን እሁድ በልዩ ድምቀት ይካሄዳል
ottawa marathonሀትሪክ ስፖርት አትሌቲክስሀትሪክ ስፖርትጋዜጣኦታዋ ማራቶን

ሀትሪክ በይፋ የተጋበዘችበት የኦቷዋ ማራቶን የፊታችን እሁድ በልዩ ድምቀት ይካሄዳል

አጋራ
አጋራ


“አሁንም የውድድሩን ሪከርድ ስለመስበር አልማለሁ፤ ኦቷዋ በጣም የተረጋጋች ለኑሮ የምትመች ሰላማዊ ከተማ ናት”

አትሌት የማነ ፀጋዬ

 

በይስሐቅ በላይ 

​አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ከፍ ብሎ 

ሲውለበለብ የሚታይበት፣ በህብረ ዝማሬ 

የታጀበ ቀልብን የሚስብ የድጋፍ አሰጣጥ 

የውድድሩ ድምቀት ሆኖ የሚደመጥበት፣ 

በመጨረሻም ለውድድሩ የተዘጋጁ ከፍተኛ 

ሽልማቶች በኢትዮጵያዊያን ተጠራርገው 

ሲወስዱ የሚታይበት ታላቅ ድግስ ቢኖር 

የኦቷዋ ማራቶን ብቻ ነው ቢባል ቃሉ ግነት 

የለውም፤ ምክንያቱም ላለፉት አመታት 

በወንድም በሴትም ኢዮጵያዊያን የአሸናፊነት 

ፈርጣማ ጡንቻቸውን በተፎካካሪዎቻቸው 

ላይ በማሳረፍ አሸናፊነቱን አላስቀምስ 

በማለት ውድድሩ ለእነሱ ብቻ የተዘጋጀ 

አስመስለውለታልና፡፡ 

…አዎን ለዚህም ይመስላል የፊታችን 

እሁድም ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ 

ኢተዮጵያዊያን አትሌቶች በኦቷዋ ሰማይ 

ስር ደምቀው ማምሸታቸው አይቀሬ ነው 

በማለት ከወዲሁ የካናዳና የሌሎች አገር 

የመገናኛ ብዙኃን ከወዲሁ የአሸናፊነቱን 

ቅድሚያ ግምት ያለስስት ሲሰጡ 

የሚደመጠው፡፡ 

ከ5ዐ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች፣ ከአስር 

ሺዎች በላይ በሚደርሱ ተመልካቾችና 

የአለማችን ምርጥ አትሌቶች ይደምቃል 

ተብሎ ከወዲሁ በጉጉት እየተጠበቀ ያለው 

44ኛው የኦቷዋ ማራቶን የፊታችን እሁድ 

ይካሄዳል፡፡ 

የዘንድሮው ውድድር ከእስከዛሬው 

ሁሉ በተለየ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደረገው 

በካናዳዊያን ምድር በሪከርድነት የተያዘ 

ሰዓት በ2ዐ14 ዓ.ም በወንዶችም በሴቶችም 

በማሸነፉ ሪከርዱን የግላቸው ያደረጉት 

ትዕግስት ቱፋና የማነ ፀጋዬ በዚህ ውድድር 

ላይ መሳተፋቸው ፉክክሩን ብቻ ሣይሆን 

የውድድሩ ተከታታዮችንና የሚዲያዎችን 

ትኩረት ይበልጥ ከፍ አድርጎታል፡፡ 

ከሁለቱ የውድድሩ የሪከርድ ባለቤት 

ከሆኑት አትሌቶች በተጨማሪ አትሌት 

አዱኛ፣ ድሪባ ቶላ፣ ኃይሌ ለሚ በተመሳሳይ 

የውድድሩ ድምቀት ከመሆናቸው 

በተጨማሪ ለአሸናፊነት ከፍተኛ ግምት 

የተሰጣቸው ሲሆን ከሁሉም ግን 

የአምናው የውድድሩ አሸናፊ የሆነው 

ኤልዮድ ኪፕታኑም ክብሩን ለማስጠበቅ 

ዘንድሮም መወዳደሩ የፉክክሩ ግለት 

ይበልጥ እንዲጨምር እንዳደረገው ነው 

በስፋት እየተዘገበ ያለው፡፡ 

የ2ዐ14ቱ የኦቷዋ ማራቶን አሸናፊና 

የውድድሩ ሪከርድ ባለቤት መሆኑን 

በውጤቱ ያስመሰከረው አትሌት የማነ 

ፀጋዬ የአዲስ አበባን መሬት ለቆ ወደ 

ካናዳ ከመብረሩ በፊት ከሀትሪክ ጋዜጣ 

ጋር ቆይታ ያደረገ ሲሆን ”አትላንቲክን 

አቋርጬ የምሄደው ሪከርድ ለመስበርም 

ድል ለማስመዘገብም ነው” ሲል ለጋዜጣው 

ማኔጂኒግ ኤዲተር ገልጾለታል፡፡ 

“ረዘም ላለ ጊዜ ከጉዳት ጋር ስታገል 

ቆይቻለሁ፣ አሁን ግን ጤንነቴ ወደ 

ቀድሞው ቦታ በመመለሱ ለራሴም 

ለሀገሬም የተለመደውን ድል ለማስመዝገብ 

ተዘጋጅቻለሁ” የሚለው የማነ ፀጋዬ 

“አየሩ ጥሩ ከሆነ፣ ወቅታዊ ብቃቴ 

ከጉዳትና መሰል ችግሮች የፀዳ ከሆነ 

በራሴ የተያዘውን ሪከርድ ራሴ ለመስበር 

ማለሜን አላቆምም” ሲል ተናግሯል፡፡ 

እ.ኤ.አ በ1975 ዓ.ም የተጀመረውና 

ሚሊዮኖችን በማሳተፉ የካናዳዊያን ትልቁ 

የማራቶን ውድድር የሆነው የኦቷዋ 

ማራቶን የአይ.ኤ.ኤፍ የወርቅ ደረጃ ያለው 

የማራቶን ውድድር ሲሆን በሁለት ቀናት 

የ1ዐ ኪ.ሜትርና የማራቶን ውድድሮችን 

በማካሄድ የአለማችን ብቸኛው ውድድር 

ሆኖም ተመዝግቧል፡፡

 

ኢትዮጵያዊያን በአቷዋ ማራቶን 

መንገስ የጀመሩት እ.ኤ.አ በ2ዐ11 

ከተካሄደው 36ኛው የማራቶን ውድደር 

ጀምሮ ሲሆን በዚህም ውድድር በሴቶች 

አሸናፊ የሆነችው መሪማ መሀመድ 

ለኢትዮጵያውያን ድል ፈር ቀዳጅ ሆና 

ተመዝግባለች፡፡ 

ከአትሌት መሪማ በኋላ ማለትም 

ከ2ዐ11-2ዐ17 በአጠቃላይ ለስድስት 

አመታት በተለይ በሴቶች ኢትዮጵያዊያን 

የአሸናፊነት ክብሩን ለሌላ ሳይሰጡ 

በተከታታይ በማራቶን በማሸነፉ በውድደሩ 

ስማቸውን በደማቅ ማስፃፍ የቻሉ ሲሆን 

በወንዶች ደግሞ ባለፈው አመት ኬንያዊው 

ኤልዮድ ኪፕታኑ ከማሸነፉ ውጪ 

ከ39ኛው እስከ 42ኛድረስ በተከታታይ 

በማሸነፉ ኢትዮጵያውያን የውድድሩ 

ድምቀቶች መሆናቸውን በውጤታቸው 

አስመስክረዋል፡፡ 

በዘንድሮው 44ኛው የአቷዋ ማራቶን 

በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን ይነግሳሉ 

ተብሎ የሚጠበቁ ሲሆን በተለይ የቦታው 

የሪከርድ ባለቤት የሆኑት ትዕግስት ቱፋና 

የማነ ፀጋዬ ከአራት አመት በኋላ ለአዲስ 

ድልና ሪከርድ መሮጣቸው የውድድሩ ትልቁ 

ዜና ተደርጎም ተወስዷል፡፡ የኦቷዋ ማራቶን 

የፊታችን እሁድ በኦቷዋ ሲካሄድ በየአመቱ 

ውድድሩን እንድትዘግብ በይፋ የምትጋብዘው 

ሀትሪክ ዘንድሮም በተመሳሳይ ከውድድሩ 

አዘጋጆች በስምዋ በቀጥታ በተላከለት 

ግብዣ መሰረት ይሄንን የካናዳዊያን ትልቁን 

የማራቶን ድግስ ከኢትዮጵያ በብቸኝነት 

በአካል ተገኝታ የምትታደም ይሆናል፡፡ 

አትሌት የማነ ፀጋዬ ከሀትሪክ ጋዜጣ 

ጋር ያደረገው ሙሉ ቃለ-ምልልስ ከዚህ 

በታች የቀረበ ሲሆን በውድድሩ ላይ ተካፋይ 

የሆነችውና ባለ ሪከርዷን አትሌት ትዕግስት 

ቱፍን በተመሳሳይ ለማነጋጋር ያደረግነው 

ጥረት ሊሳካልን ባለመቻሉ በዚህ ዘገባ ውስጥ 

ማካተት አልቻለም፡፡

ሀትሪክ፡- ከታላላቅ ውድድሮችና 

ድሎች ጋር ስምህ ተያይዞ ሲነሣ ከተደመጠ 

ሰነባበተ ምነው በሠላም …? 

የማነ፡- በ2ዐ17 የለንደን የዓለም 

ሻምፒዮና ላይ የገጠመኝ ጉዳት ትንሽ 

ከውድድርም ከውጤትም ውጪ አድርጎኝ 

ቆይቷል፤ ለንደን ላይ ውድድሩ ጥሩ 

አልነበረም፤ ትንሽ ከርቭ ምናምን ይበዛበት 

ነበር፤ በዚህ የተነሣ የጡንቻ መሳሳብ ገጥሞኝ 

ከውድድርም ከውጤትም ጋር ተቆራረጬ 

እንድቆይ የገጠመኝ ጉዳት አስገድዶኛል፤ 

በአጭሩ በዚህ ምክንያት ነው የጠፋሁት፡፡ 

ሀትሪክ፡- አሁን ያለው የጤንነትህ ሁኔታ 

ምን ይመስላል? ወደ ቀድም ጤንነትህስ 

ተመልሰሃል…? 

የማነ፡- አሁን እግዚአብሔር የተመሰገነ 

ይሁን በጤንነቴ ላይ ከፍተኛ መሻሻል 

ታይቷል፤ ልምምድም በበቂ ሁኔታ እየሰራሁ 

ነው፡፡ 


ሀትሪክ፡- የፊታችን እሁድ በIAAF 

የወርቅ ደረጃ የተሰጠውና የካናዳዊያን 

ታላቁ የማራቶን ውድድር ይካሄዳል፤ በዚህ 

ውድድር ላይ ይሳተፋሉ በሚል ብቻ ሣይሆን 

ለአሸናፊነት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው 

አትሌቶች ደግሞ አንዱ ነህና ውድድሩን 

ለማሸነፍ ምን ያህል ተዘጋጅተሃል…? 

የማነ፡- ሁሉም ሰው ለማሸነፍ 

ነው አገር አቋርጦ የሚሄደው፤ እኔም 

አትላንቲክን አቋርጬ ኦቷዋ ድረስ የምሄደው 

እንደማንኛውም ሰው ለማሸነፍ ነው፡፡ 

እስከአሁን ለማሸነፍ የሚረዳኝን በቂ ዝግጅት 

አድርጌያለሁ ብዬ አስባለሁ፤ የውድድር ነገር 

እንደምታውቀው ነው ሁላችንም አሸናፊ 

ለመሆን ነው የምንሄደው፤ የሚያሸንፈው 

ግን ያው አንድ ሰው ነው፡፡ በግሌ ለማሸነፍ 

ተዘጋጅቻለሁ፤ ትክክለኛው አሸናፊ ማን 

ይሆናል የሚለው እንግዲህ የፊታችን እሁድ 

የሚታወቅ ነው የሚሆነው፡፡ 

ሀትሪክ፡- በ2014ዓ.ም የኦቷዋ ማራቶን 

የውድድሩን ሪከርድ ሰብረህ HYUNDI SUV 

ዘመናዊ መኪና፣ ለሪከርዱ ተጨማሪ የገንዘብ 

ሽልማት አግኝተሃል፤ ዘንድሮስ ተጨማሪ 

መኪናና የገንዘብ ሽልማት ለማግኘት 

አላሰብክም…? 

የማነ፡- አሸንፎ መሸለምን ማን ይጠላል 

ብለህ ነው? እንዳልከው አንተ የ2ዐ14ቱን 

ስኬት ደግሜ ለሁለተኛ ጊዜ ለመሸለም 

አስቤያለሁ፤ የአየሩ ፀባይ ጥሩ ከሆነ 

ከጥረቴ በተጨማሪ እግዚአብሔር ከረዳኝ 

ለማሸነፍና ተሸላሚ ለመሆን አስቢያለሁ፡

፡ ግን የሚሆነውን ዛሬ ላይ እርግጠኛ ሆኖ 

መናገር አያስችልም፤ ምክንያቱም እኔ ብቻ 

ሣልሆን ለውድድሩ የሚሄዱትም ጥሩ ሩጫ 

ሮጠን ጥሩ ውጤት እናስመዘግባለን ብለው 

ነው፡፡ አብረውኝ የሚሮጡት የሀገሬ ልጆችም 

በጣም ጠንካሮች ናቸው፤ ከጓደኞቼ ጋር አብሬ 

ሆኜ ጥሩ ውጤት ለራሳችንም ለሀገራችንም 

የምናስመዘግብበት ጥሩ ውድድር እንደሚሆን 

ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 

ሀትሪክ፡- በ2ዐ14 በኦቷዋ ማራቶን 

ያስመዘገብከው 2፡ዐ6.54 ሰዓት እስካሁን 

በካናዳ ምድር ያልተደፈረ ሪከርድ ሆኖ 

የተመዘገበውን ውጤት በእልህ ያስመዘገብከው 

ውጤት ነው የሚል ነገር ሰምቻለሁ፤ እስቲ 

ስለዚህ ነገር አጫውተኝ….?

የማነ፡- (እንደ መሳቅ እያለ) እውነት 

ነው ትክክል ነው፤ በ2ዐ14 የኦቷዋ 

ማራቶን የውድድሩ ሪከርድ የሆነን ሰዓት 

ያስመዘገብኩት በውስጤ በተፈጠረ እልህ 

ተነሳስቼ ነው፡፡ በወቅቱ ከነበረው ማናጀሬ 

ጋር በገንዘብ ምክንያት ግጭት ውስጥ ገብተን 

ለውድድሩ ራሱ አልሄድም እስከ ማለት ደርሼ 

ነበር፡፡ በዚያን ወቅት የነበሩት አሰልጣኝ 

ናቸው ውድድሩን መሰረዝ የለብህም መሄድ 

አለብህ ብለው ገፋፍተው እንድሄድ ያደረጉኝ፡

፡ እዛ ከሄድኩ በኋላ በከፍተኛ እልህና ቁጭት 

ውጤታማ ሆኜ ማሳየት አለብኝ ብዬ ሮጬ 

ከማሸነፍ አልፌ የቦታው ሪከርድ ባለቤት 

መሆን የሚያስችል ውጤት አስመዘግቢያለሁ፡

፡ አንዳንዴ ለካ እልህ ጥሩ ነው፤ በእልህ ሮጬ 

በወቅቱ ፊት ለነሣኝ ማናጀር በቂ ትምህርት 

የሰጠ ውጤት አስመዘግቤያለሁ፡፡ አንዳንዴ 

ስትበደል እልህ ውስጥ ስትገባ የተሻለ 

ነገር እንድትሰራ ለሰከንድም እንዳትተኛ 

ያደርግሃል፤ እግዚአብሔር የተመስገን ይሁን 

በእልህ ስኬታማ ሆኛለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- እስከአሁን የኦቷዋ ማራቶን 

ሪከርድ በስምህ ተመዝግቧል፤ የቦታው 

ሪከርድ ባለቤት መሆንህ ምን ስሜት 

ይፈጥርብሃል…?

የማነ፡- የቦታው ሪከርድ ባለቤት መሆን 

ሁሌም ውድድር በመጣ ቁጥር ስለ ኦቷዋ 

ማራቶን ሲዘገብ የአንተም ስምና ውጤት ከፍ 

ብሎ የሚነሣበት ሁኔታ እንዲኖር ያደርጋል፡

፡ ይሄ ደግሞ ከፍተኛ ደስታ እንዲሰማህና 

ተቀባይነትህም ይበልጥ እንዲጨምር የራሱን 

የሆነ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ በውስጥህም 

የሆነ የተለየ ስሜት እንዲፈጠረም ያደርጋል፡፡ 

የተወዳዳሪዎች፣ የውድድሩ አዘጋጆች፣ የተመልካቾችና 

የሚዲያዎችም የትኩረት ማዕከል እንድትሆን 

ያስገድዳል፡፡ የውድድሩ አዘጋጆችም ባለ ሪከርድ 

በመሆንህ የተለየ ቦታ እንዲሰጡህም ያስገድዳቸዋል፡

፡ ሪከርዱ ይሄን ሁሉ ስለሚያመጣልኝ ልዩ የደስታ 

ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡ 

ሀትሪክ፡- ብዙውን ጊዜ የበርሊን ማራቶን 

ሪከርዶች በተደጋጋሚ ሲሰባበሩበት ይታያል፤ ኦቷዋስ 

ለሪከርድ የተመቸች ናት…?

የማነ፡- -የበርሊን ማራቶን ሲሰራም ራሱ ከአየር 

ንብረቱ፣ ከፔስ ሜከሮች (አሯሯጮች) ጋር ተዳምሮ 

ሪከርድ ለመስበር ነገሮችን ምቹ ያደርጋል፡፡ እኔ በርሊን 

ላይም ኦቷዋ ላይም ሁለቱም ላይ ሮጫለሁ፡፡ በርሊን 

ለሪከርድ ብዙ የተመቻቹ ነገሮች አሏት፤ ኦቷዋ ግን 

ለሪከርድ ምቹ ናት ብሎ ለመናገር ከባድ ነው፡፡ 

ሀትሪክ፡- ኦቷዋ ስምህን በታሪክ ያስመዘገብክባት 

ከተማ ናት፤ ለዚህ ያበቃችህን ከተማና በአጠቅላይ 

ካናዳን ግለፃት ብልህ እንዴት ነው የምትገልፃት…?

የማነ፡- ካናዳ በጣም ልዩና ደስ የምትል ሀገር 

ናት፤ በእርግጥ እኔ ቶርንቶን ወይም ሌሎች 

ከተሞችን አላየሁም ኦቷዋን ነው ያየሁት፡፡ በተለያየ 

መንገድ ካገኘሁት መረጃ ለመረዳት እንደቻልኩት 

ቶሮንቶ የቢዝነስ ከተማ ናት፤ ኦቷዋ ግን የፌዴራል 

መንግሥት መቀመጫና ዋና ከተማም ናት፡፡ 

የውድድሩን ሪከርድ የሰበርኩባት ከተማ ስለነሆነች ብቻ 

ሣይሆን ኦቷዋ በጣም ለመኖር የምትመች፣ በጣም 

ግርግር ያልበዛበት፣ ሠላም የሠፈነባትና የተረጋጋች 

በጣም ደስ የምትል ምርጥ ከተማ ሆና ነው ያገኘኋት፡፡ 


ሀትሪክ፡- የኦቷዋ ማራቶን ድባብስ…?የካናዳዊያን 

ድጋፍንስ እንዴት ነው የምትገልፀው…?

የማነ፡- የኦቷዋ ማራቶን ልዩ የሆነ ድባብ (ከለር) 

አለው፤ በጣም ደስ የሚል አደጋገፍ ነው የምታየው 

በጣም ደምቆ ተጀምሮ በድምቀት ነው የሚጠናቀቀው፡

፡ ከውድድርም በላይ የሆነ ልዩ ድባብ ያለው ለመሮጥ 

የምትጓጓበት ውድድር ነው፡፡ 

ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያዊያን ድጋፉስ እንዴት 

ትገልፀዋለህ?

የማነ፡- በ2ዐ14 ኦቷዋ ላይ ሮጬ እንዳየሁት 

በወንድም በሴትም ያደረግነው ውድድር በበርካታ 

ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የታጀበ ነው፤ ኢትዮጵያዊያን 

በነቂስ ሊባል በሚችል ደረጃ ወጥተው ነው ሲያበረታቱን 

ሲደግፉን የነበረው፡፡ ህዝቡ አስፓልቱ ላይ ወጥቶ 

ድጋፉን ሞራሉን ሲሰጠን ነበር፡፡ በየጊዜው በካናዳ ላይ 

ለሚመዘገበው ድል በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን 

ድጋፉ ትልቅ አተዋፅኦ አለው፡፡ኢትዮጵያዊያን የእኛን 

ተወውና የውድድሩ ድምቀቶች ናቸው፤ በዚህም 

ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡ አሁንም ያ ድጋፋቸው 

እንደማይለየን ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ 

ሀትሪክ፡– በዘንድሮው የኦቷዋ ማራቶን የአምናው አሸናፊ ኬንያዊው ኤልዩድ ኪፕታኑ 

አሸናፊነቱን ለማስጠበቅ ይሮጣል፤ የእሱ 

መኖር ማራቶኑን በአሸናፊነት እንዳላጠናቀቅ 

ሊያደርገኝ ይችላል የሚል ስጋት በውስጥህ 

እንዲፈጠር ያደርጋል… ?

የማነ፡- በፍፁም….! ማራቶን በባህሪው 

እከሌ ያሸንፋል ብለህ ቀድመህ የምትገምተው 

ውድድር አይደለም፤ አንዳንዴ ያልጠበቀው 

አንዳንዴ ደግሞ የተጠበቀው ሊያሸንፍ 

ይችላል፤ 42 ኪሎ ሜትሩን ሮጠህ ለመጨረስ 

ምን እንደሚያጋጥምህ መሀል ላይ ምን 

አይነት ብቃት እንደሚኖርህ አታውቀውም፡

፡ እየሮጥክም የማታውቀው የጤና መታወክ 

ሁሉ ይገጥመሃልና ማራቶን እንደ አጭር 

ርቀት የምትለካው ውድድር አይደለም፡፡ 

ስለዚህ የአምናው አሸናፊ ኬንያዊው መኖር 

አለመኖር ሣይሆን የሚያስፈራው ከላይ 

የጠቀስኩልህ ነው፤ ደግሞም እሱ አምና 

ስላሸነፈ ዘንድሮም ያሸንፋል ብሎ እርግጠኛ 

መሆን ከባድ ነው፤ ከእሱ ውጪ ለአሸናፊነት 

ትልቅ ቦታ የተሰጣቸው ኢትዮጵያዊያን አሉ፤ 

ሌሎች ኬንያዊያኖችም እንደዛው ይኖራሉ፡፡ 

ስለዚህ አምና ያሸነፈው ነው የሚያሸንፈው 

ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ 

ሀትሪክ፡- ከኬንያዊያን በተጨማሪ 

በኢትዮጵያዊያንን መካከል ማለትም በአንተ 

በድሪባ ቶላ፣ በኃይሌ ለሚና በአዱኛ መካከል 

የሚኖርው ፉክክርም እንዲሁ አጓጊ ይሆናል 

ተብሎ ከወዲሁ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል፡፡ 

አንተስ በዚህ ላይ ምን ትላለህ…?

የማነ፡- መጀመሪያ ከኬንያዊያን ጋር ያለን 

የሀገርን ስም የማስጠራት ፉክክር እንደተጠበቀ 

ሆኖ የመጨረሻው ፉክክር ወይም ውጤቱ ወደ 

እኛ እንደሚያደላ ተስፋ አለኝ፡፡ በጣም አቅም 

ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ስላሉ ከኬንያዊያን 

ባለፈው በመካከላችን ያለው ፉክክር ቀላል 

እንደማይሆን ነው የምንገምተው፤ ከመካከላችን 

ማንም ያሸንፍ ማን ብቻ ሀገራችን ታሸንፍ፡፡ 

ሀትሪክ፡- የፊታችን እሁድ የኦቷዋ 

ማራቶን ሲጠናቀቅ የየማነ ፀጋዬን ስም ስንተኛ 

ደረጃ ላይ ነው የምናገኘው…? 

የማነ፡- እንግዲህ መጀመሪያ ምኞቴም 

ፍላጎቴም አሸናፊ ለመሆን ነውና አሸናፊ 

የሚለው ጋ የምገኝይመስለኛል፤ ከዚህ 

ውጪ ከሆነ ደግሞ Top 3 (ምርጥ 3) ውስጥ 

የሚለውን በውስጤ ከእግዚአብሔር ጋር 

ይዤዋለሁ፡፡ 

ሀትሪክ፡- ባለፈው በእልህ ሮጠህ ሪከርድ 

ሰብረሃል ዘንድሮስ ስለ ሪከርድ ታስባለህ…. ?

የማነ፡- ከተገኘ ማን ይጠላል…?የአየር 

ሁኔታው ጥሩ ከሆነ፣እንደ ዝግጅቴ በጥሩ 

አቋም ከሮጥኩ፣ ጥሩ አሯሯጭ ካሉ አሁንም 

ስለ ሪከርድ ማለሜን አላቆም፤በድጋሚ ሪከርድ 

መስበርን አልማለሁ።

አቷዋ ላይ ከውድድሩ በኋላ ተገናኝተን 

በድል ዙሪያ እንደምናወራ ተስፋ አደርጋለሁ 

፤አሁን ግን ለጊዜው አመስግኜህ ከመለያየታችን 

በፊት በመጨረሻ ማለት የምትፈልገው ካለ…? 

የማነ፡- ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም 

አንድ የሚያሳስበኝን ነገር ብናገር በጣም ደስ 

ይለኛል፡፡ በተለይ በአትሌቲክሱ በስፖርቱ 

ዘርፍ ላይ እናንተም እንደሚዲያ ትልቅ 

ሚና ትጫወታላችሁ የሚል እምነት አለኝ፤ 

የሚዲያው ተሳትፎ በጣም ወሳኝነት አለው፡

፡ ወጣቶችን እየወረዳችሁ የማነሳሳትና 

የማበረታታት ሥራ እንድትሰሩ ነው 

የምጠይቀው፡፡ በቀጣይ ደግሞ በተለይ 

በማዘወተሪያ ሥፍራዎች ላይ ብዙ ነገር 

ከእናንተ ይጠበቃል፡፡ አሁን በጣም አስቸጋሪ 

እየሆነ ያለው የማዘውተሪያ ሥፍራ ነው፡

፡ ለፌዴሬሽኑ የምታስተላለፉኝ መልዕክት 

እንደ ድሮ በቀላሉ የሚሰራበት ጊዜ አይደለም፡

፡ የማዘወተሪያ ስፍራ ወደ ልማትና 

ኮንስትራክሽን ሥራዎች እየገቡ ነው፤ 

ስፖርት ለአንድ ሀገር ትልቅ የሥራ ዘርፉ 

፣ብቁ ዜጎች የሚፈሩበት ትልቅ እንደስትሪ 

በመሆኑ ትኩረት ተስጥቶት እንዲሰራ ነው 

የምጠይቀው፤ በተለይ አስቸጋሪ የሆነው 

የማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ብዙ እንዲሰራ 

ከፍተኛ ጥረት እንድታደርጉ ነው የማሳስበው፡፡

Offical ottawa marathon
“Run Ottawa 2018 Winter Course Highlights”
 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...