መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ተወዳጇ፣ ተናፋቂዋ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ ስፖርት ተወዳጇ፣ ተናፋቂዋ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ ስፖርት፣ ሀትሪክ ስፖርት፣ ሀትሪክ ስፖርት
ተወዳጇ፣ ተናፋቂዋ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን? በጣም አነጋጋሪ የሆነ ቃለ-ምልልስን ‘‘ዘ ቢግ ኢንተርቪው”በሚለው አምዷ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተርና እንደዚሁም ደግሞ ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ ከቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ የአዳማ ከነማ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና በፕሮፌሽናል ተጨዋችነትም በደቡብ አፍሪካ ሊግ፣ በህንድ ሊግ፣ በባንግላዴሽ ሊግ ከተጫወተው ፍቅሩ ተፈራ ጋር በኳስ ሕይወቱ ዙሪያና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርጎ ድፍረት የተሞላበትን ምልልሶች አድርገዋል፤ ለመሆኑ ፍቅሩ ተፈራ ለሜሳ የነገው እትም ላይ ምን ብሎ ይሆን? ለጋዜጣው ከሰጣቸው ቃለ-ምልልሶች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፡፡
“አንዳንድ አሰልጣኞች ሌቦች
ናቸው፤ ኪሳቸውን እያደለቡ እግር
ኳሱን ገደል እየከተቱት ነው”
– “ከውጪ በመጡ ተጨዋች ተብዬዎች የሀገሬ
ተጨዋች በገዛ ሀገራቸው ሁለተኛ ዜጋ እየሆኑ ነው”
– “በህንድ የሪከርድ ማህደር ላይ ስሜንና የሀገሬን
ባንዲራ በማስፈሬ ኩራት ይሰማኛል”
በሚል ምላሾቹን ሰጥቷል፤ ሌላ ብዙ ነገሮችንም በምላሹ ሰጥቷል፤ የነገ እትሟን ሀትሪክ አንብቧት፤ በፍፁም አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ሌላ መረጃዋ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አልቢትር በአምላክ ተሰማ ስለመራው እና ከፍተኛ አድናቆትን ስላተረፈበት የቶታል የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዙሪያ ስለ በአምላክ ምን ተብሎ ይሆን በሚል ዘገባ ይዛ የምትወጣ ሲሆን ሌላው መረጃችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋናን የፊታችን እሁድ ስለሚፋለምበት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዙሪያ አስቻለው ታመነን አናግረን ምላሾቹን ሰጥቶናል፡፡
ሀትሪክ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ሶስተኛው ቤተሰባዊ ሩጫም ከክለቡ ደጋፊ ማህበር አመራሮች አንዱ የሆነውን ሰለሞንን አናግራም ምላሽን አግኝታለች፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ነገ ከምታስነብቦት መረጃ መካከል የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ፉልሃምን
ያሸነፍነው“ጠንክረን ስለሰራን ነው ስላሉበት ጨዋታ እንደዚሁም ደግሞ ማንቸስተር ሲቲና ማንቸስተር ዩናይትድ ስላደረጉት እና በሲቲ አሸናፊነት ስለተጠናቀቀው የደርቢ ጨዋታ የምናስነብባችሁ መረጃ አለን፡፡ ከእነዚህ መካከልም አሰልጣኝ ጆሴ ሞውሪኖ“ለሽንፈት የተዳረግነው ተጋጣሚያችን
ስህተታችንን በመጠቀሙ ነው”ስላሉበት ሁኔታ አስተያየታቸውን እንዲያነቡት ጋብዘንዎታል፤ ሀትሪክ ሌላ በርካታ መረጃዎችም የነገው እትሟ ላይ አላት፤ ሀትሪክ ምርጫዎ ትሁን፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገ እትም የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...