መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርትን ነገ በማለዳ  ይጠብቋትዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ በማለዳም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ስፖርት ዘገባዎችን ለንባብ ታቀርብሎታለች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

ሀትሪክ ስፖርትን ነገ በማለዳ  ይጠብቋትዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ በማለዳም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ስፖርት ዘገባዎችን ለንባብ ታቀርብሎታለች

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ ስፖርትን ነገ በማለዳ  ይጠብቋት ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ በማለዳም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ስፖርት ዘገባዎችን ለንባብ ታቀርብሎታለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ከሀገር ውስጥ ነገ ይዛሎት የምትቀርበው በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የውድድር ተሳትፎ አገራችንን በመወከል ስለሚሳተፈው የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ነገ  ከኡጋንዳው ካምፓላ ሲቲ ጋር ስለሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታና ከክለቡ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ከቡድኑ ተከላካይ አስቻለው ታመነ ጋር ቆይታን ያደረግን ሲሆን ከእዚያ ውጪም በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ነገ በሐዋሳው ኢንተርናሽናል ስታዲየም የግብፁን ዛማሊክ ስለሚፋለመው የወላይታ ድቻ ክለብም እያደረገ ስላለው ዝግጅትና ጨዋታውን አስመልክቶ እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ ጥያቄዎች ዙሪያም አሰልጣኙን ዘነበ ፍስሀን አናግረነው ምላሹን ሰጥቶናል፡፡

የሀትሪክ ስፖርት ሌላው የሀገር ውስጥ መረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በወቅታዊ ምርጫ ዙሪያ ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ይስሃቅ በላይ ለቀረበላቸው አነጋጋሪና ድፍረት የተሞላበት ጥያቄ እሳቸውም ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ ምላሽን ሰጥተዋል፡፡

የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ሌላው የነገ መረጃ የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ላይ  በእንግድነት  ይዘነው የቀረብነው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ የሐዋሳ ዱቄት፣ የአየር መንገድና የቅ/ጊዮርጊስ ተደናቂ ተጨዋች የነበረውን ይልማ ተስፋዬን /ካቻማሌ/ ሲሆን ተጨዋቹን ነዋሪነቱን ካደረገበት ደቡብ አፍሪካ ለእረፍት ወደዚህ ከመጣ በኋላ አግኝተነው በኳስና ባለው ህይወቱ ዙሪያ ጣፋጭ ቃለ-ምልልስን አድርገንለት ምላሹን ሰጥቷል፤ የነገው ሀትሪክ እንዳታመልጥዎ፡፡ሃትሪክ ስፖርት በውጪ ዘገባዋ ኔይማርን ስላጣው የፒ ኤስ ጂና ሪያል ማድሪድ ትንቅንቅ ፣የተጠናቀቀ ጨዋታ ነው ስለተባለው  የሊቨርፑልና ፖርቶ የሻምፒየንስ ሊግ ፍልሚያ እንዲሁም በአንፊልድ ስለነገሰው የፈርኦኖቹ ኮከብ መሃመድ ሳላህ ምርጥ ምርጥ ዘገባዎች ይዛላችሁ ትቀርባለች፡፡

በሌሎች የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች፤ የስፔን ላሊጋና የሌሎች ሊጎችንም አስመልክተን ከመዝናኛ አምዶቻችን ጋር ለእናንተ ሰፋ ያሉ መረጃዎችን አቅርበናል፡፡

በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት ስለተካሄዱ የውስጥ ውድድሮችም መረጃዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ ሀትሪክ የእናንተ ናት ይወዷታል፤ ያንብቧት

ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፡፡

በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

መልካም ንባብ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...