ሀትሪክ ስፖርትን በገበያ ላይ በጣም የሚወዷትን እና ሁሌም የሚያነቧትን ጋዜጣዎ ነገም በተለያዩ መረጃዎች ገበያ ላይ ያገኟቷል።

ሀትሪክ ስፖርትን በገበያ ላይ
በጣም የሚወዷትን እና ሁሌም የሚያነቧትን ጋዜጣዎ ነገም በተለያዩ መረጃዎች ገበያ ላይ ያገኟቷል።
ሀትሪክ በነገው እትሟስ ምን ይዛ ትቀርብ ይሆን?
በሀገር ውስጥ የአንደኛው ዙር መጠናቀቅን አስመልክቶ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አቤል ያለውና የፋሲል ከነማው ሱራፌል ዳኛቸው አስተያየትን ሰጥተዋል። ምን ብለው ይሆን?
ሀትሪክ ሌላው ከፍተኛ ተወዳጅነት ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷም ለኢትዮጵያ ቡና በተከላካይነት በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ ያለው ወንድሜነህ ደረጄም ስለ ኳስ ህይወቱ ስለ ክለቡ ስለ ቤተሰቦቹ ስለ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌና ሌሎች ጥያቄዎች ተጠይቆ አጥጋቢ ምላሽን ሰጥቷል።
ስለ ቤተሰቡ ከተናገረው ውስጥ በእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቴ ለእዚህ ደረጃ የበቃሁት ወላጅ እናቴ ጠላ ሸጣ እና ብዙም ለፍታ እንደ እናትም እንደ አባትም ሆና አሳድጋኝ ነው። የእሷ ውለታም በቀላሉ ተከፍሎ የማያልቅም ነው ብሏል።
ወንድሜነህ ሌላስ ምን ብሎ ይሆን? ነገ ጋዜጣውን አግኝተው ያንብቧት።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም በተለያዩ የአውሮፓ ሊጎች እየተከናወኑ ስላሉ ጨዋታዎች እና ቁልፍ ተጨዋቾቻቸው ስለሰጧቸው ቃለ ምልልሶች እንደዚሁም ደግሞ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ተጨዋቾች ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ እና አንዲ ሮበርትሰን ስለክለቡ ቆይታቸው የሚናገሩትን ዘገባን አቅርቦሎታለች።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪም ከፍተኛ መሻሻልን ባሳየውና በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ጎብኚዎች ባሉት በድረ-ገፅዋም hatricksport.net አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።
የሀትሪክ የፊት ለፊት ገጿም ይህንን ይመስላል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team