መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ “ከተከፈለኝ ገንዘብ ይልቅ የአል-አህሊና የዊዳድን ጨዋታ ለመምራት መሃል ሜዳ ላይ መገኘቴ ለራሴም ለሀገሬም ያስገኘልኝ በሚሊዮን ብሮች የማይተመን ክብር ይበልጣል”ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

“ከተከፈለኝ ገንዘብ ይልቅ የአል-አህሊና የዊዳድን ጨዋታ ለመምራት መሃል ሜዳ ላይ መገኘቴ ለራሴም ለሀገሬም ያስገኘልኝ በሚሊዮን ብሮች የማይተመን ክብር ይበልጣል”ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ

አጋራ
አጋራ

በይስሀቅ በላይ

ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ 
አሁንም አዳዲስ ታሪኮችን ማፃፉን ቀጥሏል፡
፡ ከደካማው እግር ኳስና ከደካማው ሊግ 
በግል ጥረቱ ነጥሮ የወጣው ኢንተርናሽናል 
አርቢትር በአምላ አሁንም የኢትዮጵያውያን 
ኩራት (The pride of Ethiopia) መሆኑን 
ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በህንድ በተካሄደው 
ከ17 ዓመት በታች የፊፋ የዓለም ወጣቶች 
ዋንጫ “ኢትዮጵያ” የሚለውን ታላቅ ስም 
አንግቦ በብቸኝነት በውድድሩ ላይ ተገኝቶ 
ሁለት ጨዋታዎችን የመራው የ36 ዓመቱ 
በአምላክ ተሰማ 2.5 ሚሊዮን ዶላር 
የሚያሸልመውን የአህጉሪቱን ትልቁን 
የቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ የመጀመሪያ 
ጨዋታና የአረቦች ደርቢ ለመጀመሪያ 
ጊዜ የዳኘ ኢትዮጵያዊ በመሆን አዲስ 
ወርቃማ ታሪክ አፅፏል፡፡


 ለሩሲያው 
የዓለም ዋንጫ ከተመረጡት ስድስት 
አፍሪካውያን ዳኞች ቀጥሎ በተጠባባቂነት 
በ7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው በአምላክ ተሰማ 
የእስካሁኑ ጥረቱና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ 
ደግሞ በአፍሪካም ሆነ በዓለም እግር ኳስ 
ላይ ያለው ተቀባይነት እያደገ መምጣቱ 
ኢትዮጵያዊ ዳኛ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 
የዓለም ዋንጫን ሲመራ ማየት ከህልምነት 
ወደ ዕውነትነት እንደሚቀየር ጠቋሚ ነው፡፡ 
ቁመተ መለሎውና መልከ መልካሙ፤ ፍፁም 
ትሁትና ለሰዎች የተለየ አክብሮት ያለውን 
ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማን 
ሁለቱን ታላላቅ አገራዊ ተልዕኮዎችን 
ማለትም በህንድ እና በአፍሪካ ቻምፒዮንስ 
ሊግ ፍፃሜ የአረቦች ደርቢን መርቶ 
ከተመለሰ በኋላ የሀትሪክ ማኔጂንግ 
ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ
“ጀግናችን ነህ” በማለት አወድሶ በቆይታው 
ዙሪያና የዚህ ታላቅ ዕድል ባለቤት ስለመሆኑ 
ስለተሰማው ስሜት አነጋግሮታል፡፡
ሀትሪክ፡- በቅርቡ የግብፁን አል-አህሊንና 

የሞሮኮውን ዊዳድ ካዛብላንካ ከለቦች የፍፃሜ 

የመጀመሪያው ጨዋታን በመምራት አዲስ ታሪክ 

በማስመዝገብህ እንኳን ደስ አለህ፤ አንተን 

የመጠየቅ እድሉን ካገኘሁ ይሄን ጨዋታ 

በመምራትህ ምን ያህል ዶላር አፈስክ ብዬ ነው 

መጠየቅ የምፈልገው?

በአምላክ፡- /በጣም ሳቀ/… ምን ያህል 

ዶላር አፈስክ ነው ያልከኝ…?…በጣም 

ቀልደኛ… ሰው ነህ…! …የሚታፈሰው እኮ… 

የሚታፈስ ነገር ሲኖር ነው… /አሁንም ሳቅ/

ሀትሪክ፡- …ለምን ይሄን ጥያቄ 

እንደጠየቅኩህ ታውቃለህ…? …የመጀመሪያው 

ምክንያቴ… ጨዋታው የአህጉሪቱ ክለቦች ትልቁ 

ጨዋታ በመሆኑ ክፍያው እንደሌሎች ጨዋታዎች 

አይሆንም ብዬ ነው፤ ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ 

ካፍ ይሄንን ውድድር ለሚያሸንፍ ቡድን 2.5 

የአሜሪካን ዶላር ሽልማትን ያፍሳል፤ አሸናፊው 

ይሄን ካገኘ ዳኛውስ ስንት ያገኝ ይሆን? በሚል 

ብዙዎች በጥያቄ ሲብሰለሰሉ ስለከረሙ ነው ይሄንን 

ጥያቄ ተንደርድሬ ያነሳሁልህ?

በአምላክ፡- /አሁንም መሳቁን አላቋረጠም/ 

…ያልከው በሙሉ ልክ ነው፤ ከእነሱ እኩል 

ነው የሚከፈለው ብለህ አስበህ ከሆነ በጣም 

ተሳስተሃል….በዚህ ጉዳይ ላይ ግን አንድ 

እውነት ልንገረህ…

ሀትሪክ፡-…/ድንገት አቋረጥኩትና/…አዎን… 

በአምላክ…ንገረኝ…?

በአምላክ፡- /አሁንም እየሳቀ/ …

የተከፈለኝን ገንዘብ ለማወቅ በጣም የጓጓህ 

ትመስለለህ፤ ግን አንድ እውነት ልንገርህ 

ይሄንን ትልቅ ጨዋታ በመምራቴ ምንም 

የተለየ ክፍያ አላገኘሁም፤ ያው ሌሎች የአፍሪካ 

ውድድሮችን ስንመራ ካፍ የሚሰጠንን ገንዘብ 

(ዶላር) ነው ያገኘሁት፡፡ ግን አንድ ሳልደብቅ 

የምነግርህ ነገር በገንዘብ በኩል የተለየ ነገር 

ባላገኝም በገንዘብ የማይታመን ትልቅ ሽልማት 

እንዳገኘሁ ግን ልደብቅህ አልፈልግም፡፡ 

ሀትሪክ፡-…ምን አይነት… ሽልማት…

አገኘህ…እስቲ…ሳትደብቅ…ንገረኝ…?

በአምላክ፡- አውቃለሁ አንተ በጣም 

ለመስማት የጓጓኸው የዶላር ቁጥሩን ነው፤ 

እኔ ግን የሁለቱን የአህጉራችን ኃያላን ክለቦች 

የሆኑትን አል-አህሊንና ዊዳድ ካዛብላንካን 

ለማጫወት መሃል ሜዳ ላይ ስቆም ያገኘሁት 

ደስታና ክብር በሚልዮን ብሮች የማይገመት 

ነው፤ ጨዋታውን በመምራቴ ከተከፈለኝ 

ገንዘብ በላይ አገኘሁት የምለው አንድ 

ኢትዮጵያዊ ዳኛ ይሄን ትልቅ ጨዋታ 

እንዲመራ እምነት ሲጣልበትና ጨዋታውን 

ሲመራ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ምን አይነት 

ክፍያ አለ? ሚልዮን ብሮችስ ይሄን እድል 

ይገዙታል? አይገዙትም፤ ለእኔ ትልቁ ክፍያና 

አገኘሁት የምለው ትልቁ ዶላሬም ይሄ ነው፡

፡ከዚህ ውጪምንም የተለየ ክፍያ የለውም፤ 

ከትልቅ ክብርና ታሪክ ውጪ ካፍ በሌሎች 

ውድደሮች ላይ የሚከፍለውን ክፍያ ነው 

የከፈለን፤ በነገራችን ላይ ዳኝነት ሃብታም 

አያደርግም፡፡ እዚህ ሙያ ላይ ለማጫወት 

የሚጠይቀው መውደድና ፍቅር ብቻ ነው፡

፡ በየትኛውም አለም በፕሮፌሽናል ሊግም 

ሆነ በአማተር ሊግ የሚታየው ይሄው ነው፡

፡ ለምሳሌ በአለም በርካታ ፕሮፌሽናል ዳኞች 

ያሉበት አገር እንግሊዝ ነው፡፡ የእንግሊዙን 

አንድ ዳኛ ማይክል ኦሊቨርን ብትወስድ 

የሚከፈለው ክፍያ ከሌሎች የተሻለ ነው፡

፡ ምክንያቱም ስራው ዳኝነት ብቻ 

ስለሆነ፤የእሱን ክፍያና የፖል ፖግባን 

ክፍያ ብታነፃፅረው አይገናኙ፤ም ፍፁም 

የተለያየ ነው፡፡ ወደ አፍሪካም ብትመጣም 

ተጨዋቾች የሚያገኙት ገንዘብና ለዳኞች 

የሚከፈለው ገንዘብ በጣም የተራራቀ ነው፡፡ 

ለእኔ ዳኝነት ከገንዘብ በላይ የፍቅርና የሆቢ 

ጉዳይ ነው፤ በአል-ሂላልና የዊዳድ ጨዋታ 

ለእኔ የሰጠኝ ከፍተኛ ገንዘብ ሳይሆን 

በሚሊዮን ብሮች የማይተመን ክብርንና 

እርካታን ለራሴም ለአገሬም አግኝቼበታለሁ፡

፡ ይህ ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ፋይናልንና 

የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን ከመሩ 

ከአገሬ ታላላቅ ዳኞች ጎራ የመገኘት ህልሜን 

ያሳካ ነው፡፡ በአጭሩ ለእኔም ለአገሬም 

ገንዘብ የማይገዛው ክብርን አገኝቼበታለሁ 

እንጂ የተለየ ክፍያ አልተፈፀመልኝም፡፡ ይሄ 

ትልቅ እድል እኮ በእግዚአብሄር ቸርነት ብቻ 

የምታገኘው ዕድል ነው ማለት እችላለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-ይሄንን የአህገሪቱን ትልቁን 

የፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ግጥሚያ፣ ይሄንን 

የአረቦች የደርቢ ትልቅ ጨዋታን እንድትመራ 

የተነገረህ እንዴት ነው…? ስትሰማስ በውስጥህ 

ምን አይነት ስሜት ተፈጠረ?

በአምላክ፡- እውነት ለመናገር የብዙ 

ጊዜ ምኞቴ ነበር እንደዚህ በአጭር 

ጊዜ እጄ ውስጥ ገብቶ አገኘዋለሁ ብዬ 

ባላስብም፤ ከዚህ በፊት በእርግጥ የተለያዩ 

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግና የኮንፌዴሬሽን 

ትልልቅ ጨዋታዎችን የመምራት እድል 

አግኝቻለሁ፡፡ የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ 

ጨዋታ የመጀመሪያ ግጥሚያን ከመመኘት 

በዘለለ ያውም እንዲህ በቅርቡ አመራለሁ ብዬ 

ግን አስቤ ስለማላውቅ የተለየ የደስታ ስሜት 

ነው የተሰማኝ፡፡ እውነት ለመናገር ይሄን 

እድል ማግኘት ለእኔ አንድ ጨዋታን ብቻ 

የመምራት ያህል አይደለም ትርጉሙ ከዚህም 

ከፍ ያለ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ጨዋታውን እንድትመራ መመደብህ 

እንዴትና የት ሆነህ ሰማህ? የሚለውን ጥያቄዬን 

ግን ዘለልከው ?

በአምላክ፡- ለዚህ የአህገሪቱ ትልቅ 

ጨዋታ መመደቤን የሰማሁት ለፊፋ የሀ-

17 ጨዋታ ወደ ህንድ ተጉዤ የብራዚልንና 

የሁንድራንስ ጨዋታ ከመራሁ በኋላ ከሌሎች 

ዳኞች ጋር ሆኜ ነው፡፡ ካፍ አሁን ባለው 

የአሰራር ሂደት የጨዋታ ምደባ ሲኖር 

ጨዋታውን የሚያሳውቅበት ሲስተም አለው 

/CAF SMS/ የሚባል ይሄንን አካውንት 

ከፍተህ በዚህ ሲስተም ያሳውቅሃል፤ በዚህ 

በኩልም እንዲሁም ከካፍ ስልክ ደውለው 

ጨዋታ እንዳለብኝ አሳውቀውኛል፡፡


ሀትሪክ፡- ጨዋታው የአህጉሪቱ ክለቦች 

ትልቁ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ገንዘብን 

የሚያስገኝ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግን ስምንት 

ጊዜ የወሰደውን የግብፁን አል-አህሊንና አንድ ጊዜ 

የወሰደውን የሞሮኮውን ዊዳድ ካዛብላንካ ጨዋታ 

የአረቦች ደርቢ ከመሆኑ አንፃር የተለየ ዝግጅት 

አላደረግክም?

በአምላክ፡- እውነት ነው ይሄ የሁለቱም 

ቡድኖች ጨዋታ ትልቅ ዋጋ /haigh profile/ 

ያለው፣ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያሽልም ፣ በርካታ 

ተመልካቾች የሚከታተሉት በአህጉሪቱ ውስጥ 

ያሉ ሚዲያዎችና የስፖርት ቤተሰቦች ብቻ 

ሳይሆን በመላው አለም የሚገኙ ሁሉ ትኩረት 

ሰጥተው የሚከታተሉት በጨዋታ በመሆኑ 

ምንም እንኳን ጨዋታውን እንድመራ 

የተነገረኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቢሆንም እንኳን 

ራሴን በአካል ብቃት፣ በአዕምሮ፣ በስነ-ልቦና 

በደንብ አዘጋጅቼ መቅረብ እንዳለብኝ ከራሴ 

ጋር ተማከርኩ፤ እንደ አጋጣሚ የፊፋ የአለም 

ከ17 ዓመት በታች ውድድርን ለመምራት 

ህንድ ስለነበርኩ የአካል ብቃትና የተለያዩ 

ትምህርቶች ይሰጡ ስለነበር አጋጣሚው 

ረድቶኛል፡፡ ከዚህ በዘለለ የራሴን የተለያዩ 

ዝግጅቶችን ማድረግ ነበረብኝ፤ ማለትም 

ስለሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ፣ስለተጫዋቾቹ 

የግል መረጃ፣ ስለአረቦች ደርቢ በፊት 

ከማውቀው በተጨማሪ የተለያዩ መረጃዎችን 

በቪዲዮ የተደገፈ ጭምር ለመከታተል ሞከርኩ፡

፡ በዚህም ከአካል ብቃትና ከትምህርት ዝግጅቱ 

በተጨማሪ ራሴን በመረጃ በአዕምሮ በደንብ 

አዘጋጀሁ፡፡ ያው ሁላችሁም እንዳያችሁት 

በእኔ እምነት ጥሩ መርቻለሁ ብዬ በምገልፀው 

መልኩ ጨዋታውን አጠናቅቄ ወጥቻለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- የአል-አህሊንና የዊዳድ ካዛብላንካ 

ጨዋታ የአረቦች ደርቢ፣ጨዋታው በግብፅ መሆኑ 

ስቴዲየሙ 70 ሺህ ተመልካቾችን የማስተናገድ 

አቅም እያለው ለደህንነናትና ለፀጥታ ሲበል 50 

ሺህ ተመልካቾችን ብቻ እንዲያስተናግድ የተደረገን 

ጨዋታ መምራት ጫናው ቀላል አይደለም የሚል 

ግምቱ አለኝና… እንደው በአምላክ ከጨዋታው 

በፊት ከሜዳ ውጪና በጨዋታው ጊዜ በሜዳ ውስጥ 

የነበረው ድባብ እንዴት ነበር?

በአምላክ፡- እውነት ለመናገር እስከዛሬ 

ካጫወትኳቸው ጨዋታዎች አንተ እንዳነ 

ሳኸው በበዙ መልኩ የተለየ ጨዋታ ነበር፤ 

ድባቡ ፍፁም ያልተለመደ የሚመስል ነገር 

ነው፡፡ የሚገርመው ደግም የጨዋታው 

ድባብ በሜዳ ውስጥም ከሜዳ ውጪም ነው፤ 

እኛ ከጨዋታው በፊት ሁለት ሰአት በፊት 

ቀድመን ወደ ሜዳ በመምጣታችን ከሜዳ 

ውጭም ሜዳ ውስጥ ያለውን አስገራሚ 

ድባብ የሚጠበቅ ቢሆንም አይተን በጣም 

ነው የተገረምነው፡፡ ከስቴድየሙ ውጪ ብዙ 

ህዝብ ለመግባት ተሰልፏል፤ ግርግሩ ልዩ 

ነው፤ ውስጥ ስንገባ ደግሞ ስቴድየሙ ጢም 

ብሎ ሞልቷል፡፡ ለሴኩሪቲ (ለደህንነት) ሲባል 

የተመልካቹ ቁጥር ከ70 ወደ 50 ሺህ ዝቅ 

ቢልም ስቴድየሙ በሰው ተሞልቷል፡፡ በሰሜን 

አፍሪካ በተለይ በአረቦች ደርቢ ላይ የተለመደ 

የሚመስለው ከፍተኛ ጢስ፣ ተቀጣጣይ 

ነገሮች የስቴድየሙን ድባብ አንዳች የተለየ 

ነገር አላብሰውታል፡፡ ያለአፍታ የሚደመጠው 

ዝማሬና ጩኸቱ ስቴድየሙን አነቃንቆታል፡፡ 

አይን ላይ የሚያበራ ሌዘር (ጨረር) ነገርም 

ይጠቀማሉ፡፡ በስነ-ልቦናው ጠንካራ ዝግጅት 

አድርገህ ካልቀረብህ በአካልም በአዕምሮም 

ካልጠነከርክ ድባቡ ይፈታተንሃል፤ እኔ ግን 

በእነዚህ ነገሮች ከመረበሽ ይልቅ ጨዋታውን 

ያለ ችግር እንዴት ነው ዳኝቼ የአገሬንና የራሴን 

ስም የማስጠራው? እንዴት ነው መዳኘት 

ያለብኝ? በማለት ከራሴ ጋር እማከር ነበር፡

፡ ራሴን በሁሉም ነገር አጠንክሬ ለወጭያዊ 

ነገር ሳይሆን ለህጉ ተገዢ ሆኖ ጨዋታውን 

እንደ አንድ ጅማሪ የፍፃሜ ጨዋታ አጫዋች 

ዳኛ በአግባቡ መርቼ ወጥቻለሁ፡፡ ምስክርነቱን 

የሚሰጠው አካል ሌላ እንደሆነ ባውቅም ለእኔ 

ለራሴ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ የፍፃሜ ጨዋታን 

እንድመራ ሰው መልካም ነው የሚል እምነት 

አለኝ፡፡ 
ሀትሪክ፡- ሜዳ ውስጥ ገብተህ ስትመራስ 

ከጨዋታው በፊት እንደገመትከው እንደ አንድ 

የአረቦች ደርቢ እንደ አንድ የፍፃሜ ጨዋታ 

እንዴት አገኘኸው? የነበረውን ፈታኝነትስ እንዴት 

ነው የምትገልፀው?

በአምላክ፡- እውነት ለመናገር ይሄ 

ጨዋታ በጣም የተለየና ትልቅ ጨዋታ 

ነው፤ የተለየ የሚያደርገው ደግሞ የሁለቱም 

ቡድኖች ደረጃና የተጨዋቾች ፕሮፌሽናል 

ሜንታሊቲ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑ 

ነው፡፡ አልፎ አልፎ የሚሰራቸው ፋውሎች 

በጣም ውስብስብና ታክቲካል በመሆናቸው 

የዳኛን እይታ መፈታተናቸውና በጣም የቅርብ 

ክትትልን መጠየቃቸው፣ ለመለየትም አስቸጋሪ 

እስከመሆን መድረሳቸው፣ ከዚህ ውጪ 

ቶሎ ቶሎ የመጠቃቃት ሁኔታ (ካውንተር 

አታኮች) የሚበዛባቸው መሆኑ ጨዋታውን 

የተለየ ያደርገዋል፡፡ በጣም የሚገርመው 

የፕሮፌሽናልነታቸውን ያህል አስመስሎ 

መውደቅን በመካን የዳኛን ውሳኔ ለማስቀየር 

መቅረባቸውና የረቀቁ ጥበቦች የታዩበት 

መሆኑ ከዚህ ውጪ ከዚህ በፊት ከነበረው 

በተለየ ብዙ መሮጥን የሚጠይቅ ለአፍታም 

ቢሆን ትኩረትህን /Concentration/ ማጣት 

የሌለብህ ጨዋታ ሆኖ መገኘቱ ጨዋታውን 

የተለየ ያደርገዋል፡፡ 

ሀትሪክ፡- ከላይ ምላሽህን ስትሰጠኝ 

ጨዋታውን በመልካም ሁኔታ ሰርቼ እንደወጣሁ ነው 

የሚሰማኝ ብለሃል፡፡ የግብፁ አል-አህሊ አሰልጣኝ 

ሆሳም አል-ባድሪ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት 

መግለጫ ላይ ግን “የ36 አመቱ በአምላክ ተሰማ 

የጨዋታውን ውጤት ማስቀየር የሚችል የፍፁም 

ቅጣት ምት የሞሮኮው ባዳር ጋድሪን የቡድናችን 

ተጨዋች የሆነው ዋሊድ አዛሮ ላይ ፋውል ሰርቶ 

ከልክሎናል” ብለው በሚዲያዎች ፊት ወቅሰውሃል፤ 

ይሄን አስተያየት እንዴት ነው የምታስተናግደው?

በአምላክ፡- ጥያቄህን እንድትጨርስ ነው 

ዝም ያልኩህ እንጂ አንድ ዳኛ በጨዋታው 

ላይ ስለተከናወኑት ነገሮች ከጨዋታው በኋላ 

አስተያየት እንዳይሰጥ የካፍም የፊፋም ህግ 

ያግዳል፡፡ እኔም የዚህ ህግ ተገዢ በመሆኔ 

በዚህ ጉዳይ ላይ ልክ ነው አይደለም ብዬ 

ምንም የምሰጥህ ምላሸ የለም፡፡ 

ሀትሪክ፡- እሺ በዚህ ላይ ምላሽ አትስጠኝ፤ 

ብዙውን ጊዜ ግን ጨዋታ ከጨረሳችሁ በኂላ 

ስለዳኝነታችሁ የሚሰጣችሁ ነጥብ አለና አንተ ለዚህ 

ጨዋታ ስንት ነጥብ ተሰጠህ? ወይም ጨዋታውን 

ተከትሎ ምን አይነት አስተያየት አገኘህ?

በአምላክ፡- በጨዋታው ላይ 

ዝርዝር ነገር እንዳላወራ ህጉ ያግደኛል፡

፡ ግን አጠቃላይ የሆነ ነገር ልነግርህ 

እችላለሁ፡፡ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን /

CAF/ ውድድሮችን ስንመራ ሁለት 

አይነት የነጥብ መስጫ ወይም የውጤት 

መገምገሚያ ዘዴዎች አሉት፡፡ አንደኛው 

የግምገማ ዘዴ የጨዋታ ታዛቢ መምህር 

ወይም /Game Accessor/ የሚባል 

አለ፤ ይሄ ጨዋታህን የሚያይ ተከታትሎ 

ውጤት የሚሰጥ ነው፤ ሁለተኛው 

የግምገማ መንገድ ደግሞ አፍሪካ 

ውስጥ ያሉ የካፍ የዳኞች ኮሚቴ ውስጥ 

ያሉም የሌሉም ይሄንን ጨዋታ በሜዳ 

ውስጥ በቴሌቭዥን (በስክሪን) አይተው 

ግምገማ የሚያካሂዱ አሉ፡፡ በዚህ 

መንገድ ነው ውጤት የሚገለፀው፤ ይሄ 

ጨዋታ ከፍተኛ ግምት /High profile/ 

የሚሰጠው ጨዋታ በመሆኑ ውጤቱ 

ወዲያውኑ አይገለፅም፡፡ በዚህ ምክንያት 

እኔም ውጤቱን እየተጠባበቅኩ ነው፡

፡ ገና ስላልደረሰኝ እንዲህ ነው ለማለት 

ይቸግረኛል፡፡ በአብዛኛው ግን ከተሰጡኝ 

አስተያየቶች መልካም ነው ማለት 

እችላለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- የሁለቱን ጨዋታ ኢትዮጵያዊ 

ዳኛ እንደሚመራው ከታወቀ በኋላ በተለይ 

በግብፅ የማህበረሰቡ ትስስር ሚዲያዎች 

ጉዳዩን ወደ ፖለቲካና በተለይ ከአባይ ግድብ 

ጋር በማያያዝ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ 

እንደነበር ነው የተሰማው፡፡ እውነት እንደዚህ 

አይነት ነገሮች ስለመኖቸራቸው ታዝበሃል?

በአምላክ፡- ይሄ የምትለው ነገር ለእኔ አዲስ 

ነገር ነው፤ ከጨዋታው በፊትም ሆነ በኋላ 

በዚህ ዙሪያ የሰማሁትም ያየሁት ነገር የለም፤ 

በጨዋታው ድባብ ላይም ይሄን የሚያንፀባርቅ 

ነገርም አላስተዋልኩም፤ በጨዋታው ወቅትም 

በኋላም ነገሮች ሁሉ በጣም ሰላማዊ እንደሆኑ 

ብቻ ነው የማውቀው፡፡

ሀትሪክ፡- የአህጉሪቱ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያሸ 

ልመውንና ትልቁን ጨዋታ በአምላክ ተሰማ 

መምራቱ በራሱ እንደ አገርም በግልም የሚሰጠውን 

ጠቀሜታ እንዴት ነው የምትገልፀው?

በአምላክ፡-ጥቅሙ በግልም በተለይ ደግሞ 

እንደ አገር በጣም ከፍተኛ ነው፤ እኔ ወደዚህ 

ደረጃ ከመምጣቴ በፊት የአገራቸውን ስም 

ባንዲራቸውን ከፍ አድርገው ያስጠሩ በርካታ 

ስመ ጥር ዳኞች ነበሩ፡፡ በሆነ አጋጣሚና 

ምክንያት ይሄ ነገር የተቋረጠበት ሁኔታ 

ነው የነበረው፡፡ እኔ እንደ አንድ ዳኛ ይሄንን 

የተቋረጠውን ነገር የማስቀጠል ሁኔታ ነው 

የእኔ ድርሻ የሚሆነው፡፡ ዳኝነት የጋራ ስራ 

ነው፡፡ ብቻዬን የሰራሁት ስራ የለም፡፡ እዚህ 

ያሉ በጣም ብቃት ያላቸው ዋናና ረዳት ዳኞች 

አሉ፡፡ እኔ በዚህ አጋጣሚ እዚህ ነገር ውስጥ 

ስለተገኘሁ ነው እንጂ አንዳንዶች እንደውም 

ከእኔ በተሻለ ሀኔታ አቅም (ታለንት) ያላቸው 

አሉ፡፡ በአጠቃላይ ግን የእኔ በዚህ መድረክ 

ላይ መገኘት በግልም በተለይ እንደ አገር 

ትልቅ ጥቅም ያስገኛል የሚል እምነቱ ነው 

ያለኝ፡፡ የእኔ በዚህን መሰሉ እድል መገኘት 

ብቻ ሳይሆን ጨዋታዎችን በአግባቡ መወጣት 

ማለት ለአገራችን ዳኝነት ያለውን አመለካከት 

ከመቀየር ባለፈ ተቋርጦ የነበረውን የዳኝነት 

ሁኔታ በማስቀጠሉ በኩል ትልቅ ሚናን 

ይጫወታል፤ አመለካከትን ወደተሻለ ነገር 

ይቀይራል የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡

ሀትሪክ፡- ግን እኮ በአምላክ ብቻውን ነው 

ጎልቶ የወጣው፤ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያዊያን ረዳት 

ዳኞች አብረውት ይሰሩ ነበር፤ አሁን በዚህ የፍፃሜ 

ጨዋታ የእነሱ አለመኖር ምክንያት ከምን ጋር 

ይያያዛል?

በአምላክ፡- እውነት ነው ከዚህ በፊት 

የተለያዩ ትልልቅ ጨዋታዎችን የምንመራው 

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች አንድ ላይ ነው፤ በአሁኑ 

ጨዋታ ግን ይሄ አልሆነም፤ ይሄ ያልሆነበት 

ምክንያት ብሎ ካፍ ያስቀመጠው ደግሞ 

በካፍ የዳኞች ደረጃ የፍፃሜና የዓለም ዋንጫ 

የማጣሪያ ጨዋታዎችን የሚመሩት Elite A 

ውስጥ ያሉ ረዳት ዳኞች ብቻ ናቸው ይሄንን 

ጨዋታ እንዲመሩ የሚደረገው፤ በአገራችን 

ደግሞ በ Elite A ውስጥ ረዳት ዳኞች 

የሉንም፡፡ በዚህ ምክንያት ነው እንደ ከዚህ 

ቀደሙ ከኢትዮጵያዊያን ረዳት ዳኞች ጋር 

ይሄን ጨዋታ ያልመራሁት፤ ይሄ እኔንም 

የሚያስቆጭ ነው፤ ምክንያቱም ከአገርህ ረዳት 

ዳኞች ጋር ስትመራ ብዙ ጥቅም አለው፡

፡ ተግባብተህ ተናብበህ ጨዋታው ቀሎህ 

ትመራለህ፡፡ አሁን ይሄ ባይሆንም በአጭር 

ጊዜ ውስጥ በጣም በአጭር ቀናቶች ዉስጥ 

በካፍ Elite A ረዳት ዳኞች ውስጥ የሚገቡ 

ዳኞች ስለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች በአንድ 

ላይ ሆነን ጨዋታ የምንመራበት አጋጣሚ 

እንደሚኖር እምነቴ ከፍተኛ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- በአምላክ ከደካማ እግር ኳስ፤ 

ከደካማ ሊግ ውስጥ ነጥሮ የወጣው በግል ጥረቱ 

ነው፤ ሊጉ ጠንካራ እግር ኳሳችን የተሻለ ቢሆን 

ከዚህ በበለጠ ብዙ ርቀት ይጓዝ ነበር የሚል 

አስተያየት የሚሰጡ በርካቶች ናቸው፤ በዚህ 

አስትያየት ትስማማለህ?

በአምላክ፡- በፍፁም በዚህ ሃሳብ 

አልስማማም፤ ምክንያቱም እኔን አሁን 

ለምገኝበት ደረጃ ያደረሰኝ የኢትዮጵያ እግር 

ኳስና ሊግ ነው የሚል የጠነከረ እምነት 

አለኝ፡፡ ይሄንን አባባሌን በምሳሌ ባሳይህ 

አሁን በቅርቡ ህንድ ላይ በተካሄደው የፊፋ 

ከ17 አመት በታች የዓለም ዋንጫ ውድድር 

ላይ የብራዚልና የሁንዱራስን ጨዋታ 

የመምራት እድል አጋጥሞኛል፡፡ የሁለቱ 

ቡድኖች ጨዋታ የኢትዮጵያውያንን እግር 

ኳስ አጨዋወትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ 

ኳስን ተቆጣጥሮ የመጫወት ወይም ኳሊቲ 

ነው ያላቸው፤ ይህ መሆኑ ደግሞ በኢትዮጵያ 

ሊግ ውስጥ ማጫወቴ ጨዋታውን በብቃት 

ተቆጣጥሬ እንድወጣ ጠቅሞኛል፡፡ ከዚህ 

መነሻነትም በጨዋታው ከፍተኛ የግምገማ 

ውጤት ማግኘቴን ስታይ የአገሬ ሊግ 

እንደጠቀመኝ እንጂ እንዳልጎዳኝ ትረዳህለህ፤ 

ከዚህ ውጭ አልፎ አልፎ የሌሎች የአፍሪካ 

አገሮችን ስታጫውት ፍጥነት የበዛበት 

ጨዋታ ያጋጥምሀል፡፡ በዚህን ጊዜ በዚህ 

መልኩ ትዘጋጅተህ መቅረብም ይጠበቅብሃል፡

፡ ብዙ ጊዜ ይሄን በአገር ቤት ስለማታገኝ 

ለዚህ የሚጠቅም ስራን መሰራት ግድ 

ይልሀል፤ ይሄንን ደግሞ ከጓደኞቼ ጋርም 

በግሌም የተለያዩ ልምምዶችን እሰራለሁ፡

፡ ከዚህ በተጨማሪም የክለብና የብሄራዊ 

ቡድን የአጭር ርቀት አሰልጣኞችን ተጨማሪ 

ስልጠናዎችን በመውሰድ ክፍተቶችን 

ለመሸፈን እንሞክራለን፡፡ እንደ አጠቃላይ 

ጉዳት ሳይሆን ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው፡

፡ የሌለው ነገር ላይ መጨመር ብቻ ነው 

የሚያስፈልገው፡፡

ሀትሪክ፡- ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፊት 

የፊፋን ከ17 አመት በታች የዓለም ዋንጫን 

ውድድርን ለመምራት ህንድ ነበርክ፤ የህንድ 

ቆይታህ እንዴት ነበር? ስንት ጨዋታዎችን 

የማጫወት ዕድልስ አገኘህ?

በአምላክ፡- በአለም ዋንጫ የማጫወት 

ሚናን አላገኘሁም፤ አሁን ግን በእግዚአብሄር 

ቸርነት ይሄ ታሪክ በህንድ ተቀይሯል፡፡ 

በህንድ ከ17 አመት በታች የዓለም ዋንጫ 

ውድድር ላይ የዋና ዳኝነት ሚናን አግኝቼ 

በጣም ተደስቻለሁ፡፡ በምድበ ጨዋታ 

5ለ2 ያለቀውን የፓራጓይና የኒውዝላንድን 

እንዲሁም 16 ውስጥ ደግሞ የብራዚልና 

የሁንድራስን ጨዋታ በብቃት መርቼ 

ወጥቻለሁ፡፡ በአጠቃላይ በህንድ የፊፋን 

ውድድር የማጫወት ዕድል ማግኘቴ ብቻ 

ሳይሆን የነበረኝ ቆይታዬ የተሳካና ውጤታማ 

ነበር ማለት እችላለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፈሃል፤ 

የቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታውን መርተሃል፤ 

በህንድ ደግሞ ከ17 አመት በታች ውድደር ላይ 

ሁለት ጨዋታዎችን በመሃል ዳኝነት መርተሃል፡፡ 

እነዚህ ነገሮች በአምላክን ወደ ሩሲያው የአለም 

ዋንጫ ያሸጋግሩታል ብሎ መናገር ይቻላል? ከዚህ 

በመነሳሳት በአምላክ ሩሲያን አሻግሮ እያለመ ነው?

በአምላክ፡- እ… (ረጅም ዝምታ) ማለት 

የምችለው ህልም እንደነበረኝ ብቻ ነው፡

፡ ምንያቱም በሩሲያው አለም ዋንጫ ላይ 

የሚያጫውቱ ስድስት አፍሪካውያን ዳኞች 

ተመርጠው አልቋል፡፡ እኔ ከስድስቱ ዳኞች 

አንዱ ባልሆንም በሰባተኛ ደረጃ በተጠባባቂ 

ዳኝነት ተይዣለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ስለዚህ ከስድስቱ ዳኞች አንዱ ላይ 

ችግር ከተፈጠረ በአምላክ በፑቲን አገር በሚካሄደው 

የአለም ዋንጫ ላይ በመዳኘት የመጀመሪያው 

ኢትዮጵያዊ ዳኛ ሊሆን ነው ማለት ነዋ?

በአምላክ፡- እንደዛ ብሎ ማሰብ ከባድ 

ነው፤ እንዳልኩህ በዓለም ዋንጫ ላይ የሚዳኙ 

ስድስቱ አፍሪካዊያን ዳኞች ተመርጠው 

አልቋል፡፡ እኔ የምገኘው በ7ኛ ደረጃ በተጠባባቂ 

ዳኛ ዝርዝር ውስጥ ነው፡፡ መጀመሪያ 10 

ነበርን ሁለቱ በተለያዩ ምክንያቶች ወጡ፡፡ 

መጨረሻ ላይ የተጨመረውን ዳኛ ጨምሮ 

ስምንት ቀረን፡፡ እኔ በ7ኛ ደረጃ ላይ ነው 

የምገኘው፡፡ ይሄ ቢሆንም እንደ እኔ እንደ 

ዕኔ ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡ ደግሞም ፊፋ 

የራሱ የሆነ አሰራር አለው፤ ያንን አሰራርም 

ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ በተጠባባቂ ዳኝነት ላይ 

ብኖርም እድሉን እንደማላገኝ አይጠፋኝም፡፡ 

ከዚህ ይልቅ ይሄንን እድል ለማግኘትና እዚህ 

ውስጥ ለመግባት ሳደርገው የነበረውን ጥረት 

አጠናከሬ መቀጠልና በቀጣይ ውድድሮች 

አገሬን ወክዬ ለመሳተፍ ነው ጥረት 

የማደርገው፡፡ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ላይ 

ተጠባባቂ ብሆንም በህንዱ የአለም ከ17 አመት 

በታች ውድድር ላይ መመረጤን በራሱ እንደ 

ትልቅ ስኬት ነው የማየው፡፡ በዘህ ውድድር 

ላይ መሳተፍና ጨዋታ መምራት ብቻ ሳይሆን 

በአምላክ ምን አይነት ዳኛ ነው? የሚለውን 

በተግባር የማሳይበትን እድልም ስለፈጠረልኝ 

የሁሉም ነገር ምክንያት የሆነውን አምላኬን 

ከልብ ነው የማመሰግነው፡፡ 

ሀትሪክ፡- ከመለያየታችን በፊት ማመስገን 

ወይም ማለት የምትፈልገው ነገር ካለ ለጊዜህ ከፍ 

ያለ ምስጋና አቅርቤ ብንለያይስ?

በአምላክ፡- በቅድሚያ ሀትሪኮች ዕድሉን 

ስለሰጣችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ፤ የእግር 

ኳስ ዳኝነት የቡድን ስራ በመሆኑ በእኔ 

ስኬት ውስጥ ከእግዚአብሄር ቀጥሎ የብዙ 

ሰዎች እጅ ስላለ እድሉን ከሰጠኸኝ እነሱን 

ባመሰግን ደስ ይለኛል፡፡ ቅድሚያውን ያለስስት 

የምሰጠው ለቤተሰቦቼ ነው፡፡ በመቀጠል ከታች 

ጀምሮ እኔ አሁን ለምገኝበት ደረጃ እንድደርስ 

ያስተማሩኝ፣ ያበረታቱኝ ኢትዮጵያዊ 

መምህሮች አሉ እነዚህን ሰዎች ከፍ አድርገህ 

ብታመሰግንልኝ ደስ ይለኛል፡፡ በመቀጠል 

አብረውኝ የሚሰሩ ኢንተርናሽናል የሆኑም 

ያልሆኑም ዳኞች የምንሰራው በጋራ በመሆኑ 

ድርሻቸው ከፍተኛ ነውና ምስጋና ይገባቸዋል፡

፡ በጣም ጨዋውና ጥሩ ስንሰራ እያበረታታ 

ስናጠፋ እየመከረ እንድናድግ ጉልበት ለሆነን 

የኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰብ ለተመልካቹም 

ክብርም ምስጋናም አለኝ፡፡ ሌላው ሳላነሳው 

የማላልፈው የምሰራበት ድርጅቴን (አርማውር

ሀንሰን የምርምር ማዕከልን) ነው፡

፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን 

በአፍሪካ ውስጥ ዳኝነት የአማተርነት 

ስራ ነው፤ ከመደበኛው በተጨማሪ 

የምትሰራው ስራ ነው፤ በሙያዬ 

የራሴንም የአገሬንም ስም እንዳስጠራ 

ድርጅቴ (አርማውር ሀንሰን የምርምር 

ማዕከልን) ለሚያደርግልኝ ድጋፍና 

ትብብር ሳላመሰግን ባልፍ ውለታቸውን 

እንደመካድ ይቆጠራልና እባክህን 

እነሱንም በወፍራሙ አመስግንልኝ፡፡ 

መጠቀስ ካለበኝ የምጠቅሰው የኢትዮጵያ 

ሚዲያዎችን በአጠቃላይ ኤሌክት 

ሮኒክሱንም የህትመት ሚዲያውንም 

ነው፡፡ እነዚህ የሚዲያ አካላት ለዳኝነት 

እድገት ሚናቸው ከፍተኛ ነውና 

ባመሰግናቸው ያንሳቸው እንደሆነ 

እንጂ አይበዛባቸውም፡፡ ሚዲያዎች 

ሁሌም ለእኛ ራሳችንን የምናይባቸው 

መስተዋቶቻችን ናቸው፡፡ ለሚሰጡን 

ድጋፍ ምክርና ማበረታቻ ሁሉንም 

ሚዲያዎች በጣም አመሰግናለሁ፡፡ 

በመጨረሻ የማመሰግነው የኢትዮጵያ 

ክለቦችን በአጠቃላይ ነው፡፡ ከላይም 

ከታች ያሉትም በሙሉ ለኢትዮጵያ 

ዳኞች እምነትና ምግባር ሰጥተው 

ለዚህ ስላደረሱንና ስላሳደጉን እነሱንም 

አመሰግናለሁ፡፡ እኛ ዳኞችም ክለቦች 

እንዳላቸው ተጨዋቾች ነን ብለን ነው 

የምናስበው፡፡ የምንለብሰው ማሊያችንና 

ሙያችን ነው የሚለያየን እንጂ 

ደማችንም እስትንፋሳችንም አንድ 

ነው፤ ምግባርና እምነት ሰጥተው 

ስላሳደጉን ለእነሱ ከልብ የመነጨ 

ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...