የኢትዮጵያ ተናፋቂው፣ አጓጊው እንደዚሁም ደግሞ በሁሉም የስፖርት ቤተሰቦችም ሆነ የቅ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ዘንድ እየተጠበቀ ያለው ታላቁ የሸገሩ ደርቢ ጨዋታ ዛሬ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ባለሜዳ በሆነበት በእዚህ ጨዋታ በርካታ ተመልካች ወደሜዳ ይመጣሉ ተብሎም ተጠብቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ዘንድሮ በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎች እየተከታተሉት እና ወደሜዳም እየጎረፉ ባሉበት ሰዓት የቅ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች አሁንም ለየት ያለን የአደጋገፍ ስርዓት በዛሬው የደርቢ ጨዋታም ላይ ይዘው ለመምጣት መሰናዶአቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን የሁለቱ ቡድን ተጨዋቾችም በደርቢው ፍልሚያ ለተመልካቹ ጥሩ የሆነን ጨዋታ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ለማሳየትም መዘጋጀታቸውን እና በዕለቱም ጨዋታ ቡድኖቻቸውንም ለአሸናፊነት ለማብቃትም ጥረትን እንደሚያደርጉ ለሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ አስተያየታቸውን ሊሰጡ ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስ ክለቦች በሸገሩ ደርቢ ጨዋታ በእስከዛሬ የእርስ በእርስ ከ1990 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ በአዲስ ፎርማት ከጀመረ ወዲህ 37 ግዜ ሲገናኙ፡ በግንኙነታቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ጊዜ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያ ቡና 8 ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፤ 11 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፤ በ2009 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ በመጀመሪያው ዙር ኢትዮጵያ ቡና 1-0 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ደግሞ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ግምታዊ አሰላለፍ
ኢትዮጵያ ቡና
99.ሀሪሰን ሄሱ
30.ቶማስ ስምረቱ
4.አክሊሉ አያናው
21.አስናቀ ሞገስ
20.አስራት ቱንጆ
19.አክሊሉ ዋለልኝ
9.ኤልያስ ማሞ
14.እያሱ ታምሩ
8.አማኑኤል ዮሀንስ
11.ሳሙኤል ሳኑሚ
18.በረከት ይስሀቅ
———————————
ቅዱስ ጊዮርጊስ
30.ሮበርት ኦዶንካራ
20.አብዱልከሪም መሀመድ
23.ምንተስኖት አዳነ
13.ሳላዲን ባርጌቾ
15.አስቻለው ታመነ
3.መሐሪ መና
20.ሙሉአለም መስፍን
27.አብዱልከሪም ኒኪማ
11.ጋዲሳ መብራቴ
25.አሜ መሀመድ
24.ኢብራሂማ ፎፋና
for ever saint george