” አጭር ነክ ልጅ ነክ ተብዬ ከ እግር ኳስ ተቀንሻለው ” የድሬደዋ ከተማ ተስፈኛ ወንድወሰን ደረጀ

የቡርትካናማዎቹ የመሀል ሜዳ ታዳጊ ተጫዋች ወንድወሰን ደረጄ በስድስተኛው ሳምንት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ተቀይሮ በመግባት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ማድረግ ሲችል ከ ሀትሪክ ስፖርት ጋር አጭር ቆይታን ሲያደርግ እንደሚከተለው ይቀርባል ።

እግር ኳስን መጫወት ሲጀምር ተምሳሌት ስላደረገው ተጨዋች እና ከውጪ ስለሚያደንቀው ተጨዋች

እግር ኳስን አንድ ብዬ ስጀምር ተምሳሌት ያደረኩት ተጫዋች አዲስ ህንፃ ይባላል ። ሲጫወት ሳየው በጣም ደስ ይለኝ ነበር ፣ በጣም እንደሱ ለመሆን ከመመኘቴ የተነሳ እንዳውም ለጓደኞቼ አዲስ ህንፃ ብላቹ ጥሩኝ እል ነበር ። ከዉጪ ደግሞ የሊዮኔል ሜሲ አድናቂ ነኝ እሱን ሳይ እግር ኳስ በጣም ቅልል ይለኛል ።

በዲ ኤስ ቲቪ የሊጉ ጨዋታዎች መተላለፍ ስለመጀመሩ

በዲኤስ ቲቪ የሀገራችን እግር ኳስ መተላለፉ ጠቀሜታዎች አሉት ። የመጀመሪያው የሀገራችን እግር ኳስ ያድጋል ፣ ሁለት ደግሞ ኳሳችን በአለም ላይ ይታያል ፣ መታየቱ ደግሞ ብዙ በዉጪ ሀገር ለመጫወት እድል ይከፍታል ። ይሄ ደግሞ የሀገራችንን የኳስ እድገት ያሳያል በጣም ትልቁ ነገር ደግሞ ለኛ ለታዳጊዎች በጣም ብዙ የመታየት እድል ይኖረናል ፣ የተሻለ ነገር እንድናገኝ ይረዳናል ብዬ አስባለሁ ።

የእግር ኳስን ተጫውቶ ስለመጣበት መንገድ

እግር ኳስን አጀማመሬ ሰፈር ውስጥ በመጫወት ነው የጀመርኩት ከዛ አሰልጣኝ “አንበስ” ወይም (ብስራት ሀብቴ ) የሚያሰለጥነውን ድሬ ተስፋ የሚባል ቡድን ውስጥ መጫወት ጀመርኩ ። ቡድናችን በጣም ጠንካራ እና ስኬታማ ስለነበረ እና አሰልጣኛችን ጥሩ ከሰዎች ጋር ግንኙነት ስለነበረው ብዙ ውድድሮች ላይ የመሳተፍ እድል እናገኝ ነበር ። ለምሳሌ እዛው ድሬዳዋ ላይ ከዛ አልፎ የይድነቃቸው መታሰቢያ ውድድር ላይ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ የመሄድ እድል አግኝተን ነበር ። ከዛ እንዳውም ውድድሩ ላይ ለጊዮርጊስ አካዳሚ ተመርጬ ነበር ፣ ከዛ 2008 ላይ ድሬደዋን ወክዬ ከ 17 አመት በታች ፕሮጀክት አዳማ ላይ ሄድኩኝ ከዛ እንደመጣው ድሬዳዋ ከነማ 17 አመት በታች ለ አንድ አመት ተጫወትኩኝ ከዛ 2009 ላይ በድጋሚ ለፕሮጀክት ውድድር ድሬን እንድወክል ተመረጥኩኝ ። ውድድሩ ላይ ጥሩ ስለነበርኩ አዲስ አበባ ወጣቶች ስፓርት አካዳሚ እና ለ ኢትዮጲያ ቡና ብመረጥም ወደ ቡና የመግባቱ ነገር በዶርም ምክንያት አልተሳካም ። ወደ አካዳሚ ገባው አካዳሚ ላይ አንድ አመት በ 17 ዓመት በታች ተጫወትኩ 2 አመት ከ 20 አመት በታች ተጫወትኩ ከዛ ቀጥታ በዉሰት ድሬን ተቀላቀልኩ ።

በፕሮጀክት ኳስ ለመጫወት ብዬ ትምህርቴን ትቼያለው ። በእግር ኳስ ብዙ ነገር ሆኛለሁ አጭር ነክ እንዲሁም ልጅ ነክ ተብዬ ተቀንሻለሁ ። በአጠቃላይ እግር ኳስ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው ብዙ መስዋት ከፍዬበታለሁ ብዬ አስባለሁ ከፈጣሪ ጋር እርሱ ፈቅዶ ለእዚህ ደረጃ ደርሻለሁ ከዚህ በኋላ እሱ ያውቃል ፣ ከእኔ የሚጠበቀው ፈጣሪን ከፊት አስቀድሞ ሁሌ ጠንክሮ መስራት ነው ።

ከሽመልስ በቀለ የሚያመሳስላችሁ ብዙ ነገር አለ ከማልያ ቁጥር ጀምሮ የአካል ብቃት አቋማችሁ የአንተ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴዎች ከእርሱ ጋር የመመሳሰል ነገር አለው ይህን እንዴት ታየዋለክ ?

አዎ ከደጅ ለሚያይ ሰው የኔ እና የ ሽመልስ በቀለ አጨዋወት አንድ ሊሆን ሊመሳሰል ይችላል ። እሱ ትልቅ ተጫዋች ነው ፣ ለእኔ እና ለእኔ አይነት ጓደኞቼ ትልቅ አርአያ ተምሣሌት ነው ። ከእርሱ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን በዛ ቁመት በዛ ሰዉነት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ የት እንዳለ መመልከት በቂ ነው ። እንደ እርሱ መጫወት መታደል ነው ስለ ማልያው ቁጥር እንኳን አስቤበት አይደለም አጋጣሚ እኔ እንዲፃፍልኝ ያዘዝኩት 77 ነበር አጋጣሚ ሲታተም ለኔ 18 ተብሎ ታተመልኝ ። ማለቴ ከጓደኛዬ ጋር በስህተት ተቀያየረ አንዳንዴ አጋጣሚዎች ወደ ትክክለኛው መንገድ ያመጣሉ ብዬ አስባለሁ ።


በድሬድዋ ቆይታህ ምን ነገሮችን ታልማለህ? የጨዋታ ጅማሬህስ…

እግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆነ ድሬደዋ ክለብ ውስጥ እስካለሁ ድረስ በጣም ጠንክሬ ሰርቼ ለ ድሬዳዋ ዋና ቋሚ ቁልፍ ተፅእኖ ፈጣሪ ተጫዋች ከዛም አልፎ ፈጣሪ ከፈቀደ እኔ እና ጓደኞቼ ሆነን ደግሞ በጣም ጠንክረን ሰርተን የቀደመውን ክብሯን ታሪኳን ወደ ነበረበት ቦታ መመለስ እናልማለን ።

ስለ አሰልጣኝ ፍሰሀ ፆመልሳን …

አሰልጣኝ ፍሰሀ ፆመልሳን በጣም ጥሩ እና ጠንካራ አሰልጣኝ ነው ። በእግር ኳስ ህይወት ብዙ ለፍቷል ብዙ ስራ ሰርቷል ። ብዙ ነገሮች ይገባዋል ፣ በዉድድሩ ላይ ከዚህ የተሻለ ውጤት እንዳያመጣ የተጫዋቾች ጉዳት እና ኮቪድ ወረርሽኝ ተፅእኖ ፈጥሮበታል ። ትንሽ ደግሞ የዳኞች ስህተት እንግዲህ ፈጣሪ ከ ፈቀደ ጅማ ላይ በተሻለ ጤንነት በተሻለ ወኔ በተሻለ ሞራል በተሻለ ተነሳሽነት ቡድኑን ይዞ ይቀርባል ብዬ አስባለሁ ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor