መነሻ ገጽ ወልዋሎ ወልዋሎ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ
ወልዋሎዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ወልዋሎ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ

አጋራ
አጋራ

 

የአሰልጣኝ ግርማ ታደሠው ወልዋሎ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክለው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር በመፈፀም ከእዮብ አለማየሁ ቀጥሎ የአዳዲሶቹን ቁጥር ወደ ሦስት አድርሷል።

ሁለገቡ ተጫዋች ካርሎስ ዳምጠው የቀድሞው ክለቡን ከአመታት በኋላ ተቀላቅሏል። የቀድሞው የነገሌ አርሲ ፣ መቻል ፣ መቐለ 7ዐ እንደርታ ፣ ጅማ አባቡና ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ድሬዳዋ ከተማ አጥቂ ላለፉት ሁለት አመታት ካሳለፈበት ወላይታ ድቻ ከአመታት በፊት ተጫውቶ ወዳሳለፈበት ወልዋሎ አምርቷል።

ሌላኛው የክለቡ ፈራሚ የመሐል ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል ነው። የቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋቹ አራት የውድድር ዘመናትን ከሀዋሳ ከተማ ጋር ከቆየ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው ወልዋሎ ሆኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...