በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ወልዋሎዎች ልምምድ የሚጀምሩበት ቀን ታወቀ
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲዎች ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ አዳዲስ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብሰባቸው መቀላቀል የቻሉ ሲሆን በክለቡ የሚገኙ ነባር ተጫዋቾችን ደግሞ ኮንትራት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆናቸውን ተከትሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከሱዳኑ አል ሂላል አል ሳህል ጋር መደልደል የቻሉ ሲሆን ለዚህም ጨዋታ እና ለ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ሁሉም የቡድኑ ተጫዋቾች ማክሰኞ ነሀሴ 12/2018 ከተሰባሰቡ በኋላ በማግስቱ ዕሮብ ነሀሴ 1372018 በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ሀትሪክ ስፖርት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ