ወልዋሎ አዲግራት 4 ተጫዋቾችን በይፋ አስፈረመ !

በተቋረጠው የውድድር ዓመት ድንቅ ጅማሮን ማሳየት የቻሉት ቢጫ ለባሾቹ በዝውውር መስኮቱ ዘግየት ብለው ቢገቡም በዛሬው ዕለት አራት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸው ታውቋል ።

ወልዋሎች በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂውን ወንድወሰን አሸናፊን ከስሑል ሽረ ለሁለት ዓመታት ሲያስፈርሙ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ ተጫውቶ ማሳለፉ የሚታወስ ነው ።

 

ፎቶ- ወንደሰን አሸናፊ በግራ | አወት ገ/ሚካኤል በቀኝ

ሌላኛው ስሑል ሽረን በመልቀቅ ቡድኑን መቀላቀል የቻለው ተጫዋች ዓወት ገብረ ሚካኤል ሲሆን በተለይም በጅማ አባጅፋር ስኬታማ ጊዜን አሳልፎ ማለፉ ይታወሳል ።

ወደ ኢትዮጵያ ቡና ካቀና በኋላ በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት በተመልካቹ ልብ ውስጥ ገብቶ የነበረው ዳንኤል ደምሱ የቢጫ ለባሾቹ ሌላኛው ፈራሚ ሲሆን መቐለ 70 እንደርታ ጋር በይፋ በመለያየት ለሁለት ዓመታት በወልዋሎ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል ።

ፎቶ ከላይ – ዳንኤል ደምሱ | ከታች አስናቀ ሞገስ

አራተኛው የቢጫ ለባሾቹ ፈራሚ መሆን የቻለው ልምድ ያለው የመስመር ተጫዋቹ አስናቀ ሞገስ ሲሆን በተለይም የወልዋሎችን የመስመር ቦታ ክፍተት እንደሚሞላ ይጠበቃል ።

 

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor