አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን በቅርቡ በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት የጦና ንቦቹ ባሳለፍነው ሳምንት ለሙሉጌታ ምህረቱ ሀድያ ሆሳዕና ፈርሞ የነበረዉ አጥቂዉ ስንታየሁ መንግሥቱ ወደ ቡድናቸዉ መልሰዉ መቀላቀላቸው ታዉቋል።
ቁመተ መለሎዉ አጥቂ በዘንድሮዉ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለክለቡ ወላይታ ዲቻ አስር ጎሎችን ማስቆጠር ችሎም ነበር። ከዛም በዘለለ የኢትዮያን ከ23 አመት በታች ቡድን ተቀላቅሎ ልምምድ ሲሳራ ቢቆይም በአሰልጣኝ ዉበቱ አባተ አማካኝነት ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል።
ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ተፈራርሞት የነበረው የሁለት አመት ዉል በፌደሬሽኑ ባለመጽደቁ ምክንያት ወደ ወላይታ ዲቻ መመለስ እንደቻለ ተረጋግጧል።


