መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ተይዟል የተባለው አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪ/ማርያም ውሸት ነው ነጻ ነኝ” ሲል ይናገራል..
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በኮቪድ ተይዟል የተባለው አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪ/ማርያም ውሸት ነው ነጻ ነኝ” ሲል ይናገራል..

አጋራ
አጋራ

👉ወላይታ ድቻዎች ሁለተኛ ሆነው ጨረሱ

በደቡብ ደርቢ ያለ አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነ ማርያም ወደሜዳ የገባው ወላይታ ድቻ ወልቂጤ ከተማን በማሸነፍ ዙሩን ሁለተኛ ሆኖ አጠናቀቀ።

በኮቪድ 19 ፖዘቲቭ ነው በሚል በፕሪሚየር ሊጉ 15ኛ ጨዋታ ላይ ስታዲየም እንዳይገባ የታገደው አሰልጣኝ ጸጋዬ ሆቴል ውስጥ ሆኖ በተከታተለው ጨዋታ ስንታየው መንግስቱ ባስቆጠረው ግብ ወላይታ ድቻ 1ለ0 በማሸነፍ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ3 ነጥብ ዝቅ ብሎ አንደኛውን ዙር እንዲጨርስ አድርጎታል።

አሰልጣኝ ጸጋዬ ከድሉ በኋላ እንደገለጸው ” ጨዋታውን ጀግኖቹ ልጆቼ ስላሸነፉ ኮርቻለሁ ሙሉ ጨዋታዎች ላይ የሚችሉትን አድርገዋል ጀግንነት በሚጠይቀው በዚህ ጨዋታ ላይም ድል በማድረጋቸው ደስ ብሎኛል ቡድኔን ሳልመራ ግጥሚያ መከታተል ከባድ ነው”ሲል አስረድቷል።

በኮቪድ 19 ተጠቅቷል መባሉን ያልተቀበለው አሰልጣኙ “ደረጃውን በጠበቀ ትልቅ ሆስፒታል ምርመራ አድርጌ ነጻ መሆኔን አረጋግጫለሁ የህክምና ተቋሙን የምርመራ ውጤት አልተቀበልኩትም ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም አመራሮቹ ተነጋግረው መፍትሄ እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ብሏል።

ስለ 15ቱ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች የተጠየቀው
አሰልጣኙ” የመጀመሪያውን ዙር በሁለተኝነት ከመሪው በ3 ነጥብ ብቻ አንሰን በመጨረሳችን ተደስቻለሁ ጥሩ የውድድር ጊዜ ማሳለፋችንን አሳይቶኛል የአሁኑ ደስታ ለነገ ዝግጅት የሚጠቅም መሆን አለበት ሙሉ በሙሉ ደስታችንን የምናጣጥመው የአመቱ ደረጃችንን ስናይ ይሆናል ተጨዋቾቼ እንደማይዘናጉም አምናለሁ” በማለት ተናግሯል።

የሊጉ የመጀመሪያ ዙር ሲጠናቀቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ31 ነጥብና 18 ግብ በመሪነት ሲፈጽም ወላይታ ድቻ በ28 ነጥብና 4 ግብ ሁለተኛ ሀዋሳ ከተማ በ27 ነጥብና 5 ግብ ሶስተኛ ሆነው አንደኛውን ዙር ፈጽመዋል። አዲስ አበባ ከተማ በ14 ነጥብና 2 የግብ ዕዳ፣ ጅማ አባጅፋር በ11 ነጥብና 12 የግብ ዕዳ እንዲሁም ሰበታ ከተማ በ9 ነጥብና 14 የግብ ዕዳ ከ14-16 ያለውን የወራጅ ቀጠና ቦታውን ይዘው ፈጽመዋል። የቅዱስ ጊዮርጊሱ እስማኤል ኦሮ አጎሮ ደግሞ በ10 ግብ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን እየመራ ጨርሷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...