መነሻ ገጽ አፍሪካ ”መንግስት ከጠየቅነዉ 51 ሚሊየን ብር 35 ሚሊየኑን ሰጥቶናል” የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን
አፍሪካአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

”መንግስት ከጠየቅነዉ 51 ሚሊየን ብር 35 ሚሊየኑን ሰጥቶናል” የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን

አጋራ
አጋራ

° ” መንግስት ከጠየቅነዉ 51 ሚሊየን ብር 35 ሚሊየኑን ሰጥቶናል” የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን

° ” በዝግጅታችን ወቅት ሶስት የሚሆኑ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነን ”

° ” ዋናዉ ዕቅዳችን ከተሳትፎ በዘለለ ከምድብ ማለፍ ነዉ ” የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ

የካሜሩኑን የአፍሪካ ዋንጫን ጉዞ በተመለከተ አስተዳደራዊ እና ቴክኒካዊ መግለጫዎች በዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ እና በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሀፊ በአቶ ባህሩ ጥላሁን አማካኝነት በኢሊሊ ሆቴል በዛሬው ዕለት መግለጫ ተሰጥቷል።

ከመግለጫው በፊት የካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫን አስመልክቶ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ፣ የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ጋዜጠኞች በተገኙበት ከረፋድ 3:00 ሰዓት ጀምሮ የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን ፤ ከዚሁ ጎን ለጎንም የፌዴሬሽኑ 13ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅትን በተመለከተም የተወሰነ ገለፃ የተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዉን እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል።

የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ከገለጿቸው ጉዳዮች መካከልም :-

የዋልያዎቹ ጉዞ በተመለከተ:-

° ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ከመንግስት 51 ሚሊዮን ብርን ጠይቀን የነበረ ቢሆንም መንግስት 35 ሚሊዮን ብር ፈቅዶልናል ለዚህም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምስጋናዉን ያቀርባል ።

° ለብሔራዊ ቡድኑ የፊታችን ቅዳሜ በስካይ ላይት ሆቴል ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል ለዚህም ልዪ ፕሮግራምም ከወዲሁ ዝግጅት ስለመደረጉ።

° ” የዋልያዋቹ አሻራ ” በሚል የተዘጋጀዉ ዶኪዮመንተሪ ፊልም ቅዳሜ ምሽት በሚኖረዉ የሽኝት ፕሮግራም ላይ ለዕይታ ይበቃል።

° ተጨዋቾች በያንዳንዱ ጨዋታ ምን ሲያደርጉ ምን ይደረጋል ስለሚለው ጉዳይ እና ተያያዥ ጎዳዮችን አቶ ባህሩ ገለፃ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ውበቱ ከተናገሯቸው ጉዳዮች መካከልም :-

°25 ተጫዋቾችን እና ሶስት ተጠባባቂዎችን መርጠናል ፤ መታወስ ያለበት ነገር የመረጥናቸው ተጫዋቾች ቶሎ የሚላመዱ ናቸዉ።

°ከሰዉነት ክብደት ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ተጨዋቾች ጋር ተነጋግረናል አላስፈላጊ የሰዉነት ዉፍረትንም እንዲቀንሱ እና አስፈላጊ ከሆነም እንዲጨምሩ እያደረግን ነዉ።

°ከሙጂብ ቃሲም እና ከሽመልስ በቀለ ውጪ የውጪ ተጨዋቾች አልጠራንም። በዚህ ጠባብ የዝግጅት ሰዓት ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾችን አካተን Risk መዉሰድ አንፈልግም።

° ከትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ተጫዋቾች ጋር ተያይዞ ዴቭድ በሻህ ጋር በደንብ አዉርተናል የላከልኝን ቪዲዮዎችም ተመልካቸቸዋለሁ ከኔ በዘለለም ከአሰልጣኝ አባላቶቼ ጋር አይተናቸዋል ብዙም አጥጋቢ አይደለም። እሱ መልምሎ የላከልንን ተጫዋቾች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ መቀላቀል ካለን ጠባብ ጊዜ አንፃር ከጥቅሙ ጉዳቱ ስላመዘነብንን ማካተት አልቻልንም።

°ምድባችን ጠንካራ ቢሆንም ዓላማችን በአፍራካ ዋንጫዉ ላይ ተሳትፎ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከምድባችን ማለፍን ዋነኛ ዕቅዳችን አድርገን ነው የምንጓዘው ።

°ብሔራዊ ቡድኑ በካሜሩን ያዉንዴ በሚኖረው ዝግጅቱ ወቅትም ሶስት ያህል የወዳጅነት ጨዋታዎችን ከሞሮኮ ፣ ሱዳን እንዲሁም ዙምባቡዌ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...